2022-05-30 20:21:31
የትግራይ ክልል መንግሥት የኤርትራ ሠራዊት ትናንት እና ከትናንት ወዲያ የሽራሮ ከተማን በከባድ ጦር መሳሪያ ደብድቧል ሲል ዛሬ ማምሻውን በኮምንኬሽን ቢሮው በኩል ባወጣው መግለጫ ከሷል።
በሽራሮው የከባድ መሳሪያ ድብደባው በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል ያለው መግለጫው፣ የትግራይ ኃይሎች በሰጡት የአጸፋ ምላሽ አንድ የኤርትራ ጦር ብርጌድ አዛዥ እና ሦስት የሻለቃ አዛዦች የሚገኙባቸው 120 ወታደሮችን ገድለው 195 ያህሉን እንዳቆሰሉ እና አራት ወታደሮችን እንደማረኩ ገልጧል። በውጊያው አንድ ድሽቃ፣ አምስት የወታደራዊ ሬዲዮ መገናኛዎች እና በርካታ የጦር መሳሪያ መማረካቸውን ጨምሮ አውስቷል።
የክልሉ መንግሥት መግለጫ ባለፉት ሁለት ቀናት የኤርትራ ጦር በሽራሮ በኩል ጥቃት የከፈተው፣ ባለፈው ግንቦት 16 በምዕራብ ትግራይ ዓዲ አውዓላ አካባቢ የከፈተው ጥቃት የትግራይ ኃይሎች በወሰዱት አጸፋ ከሽፎ ጦሩ ክፉኛ በመመታቱ ነው ብሏል።
የክልሉ መንግሥት በዚሁ መግለጫው፣ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ የኤርትራን መንግሥት ድርጊት በቃ ለማለት እጅጉን ቢረፍድበትም፣ ፈጽሞ ግን አልመሸበትም በማለት መግለጫውን ቋጭቷል።
ዋዜማ ራዲዮ
2.5K views17:21