ረድኤት አስረሳኸኝ በካፍ የኮከቦች ሽልማት በምርጥ ወጣት ተጫዋቾች ዘርፍ እጩዎች ውስጥ ተካተተች የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ባለ ድል እንዲሆን እና በዓለም ዋንጫ ማጣርያ እስከ መጨረሻው ዙር በዘለቀ አስደናቂ ጉዞ ላይም 7 ጎል በማስቆጠር ትልቅ ድርሻ የተወጣችው ረድኤት አስረሳኸኝ በካፍ የዓመቱ ምርጦች ሽልማት ላይ በወጣቶች ዘርፍ 10 እጩዎች ላይ መካተት ችላለች። በሀዋሳ ከተማ እየተጫወተች የምትገኘው ወጣቷ አጥቂ ረድኤት በሽልማቱ ላይ በእጩነት በመካተቷ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተሰማውን ደስታ እየገለፀ በምርጫው መልካም ዕድል እንዲገጥማት ይመኛል። 1.2K views13:17