2022-05-26 16:48:48
የመጅሊስ ሙሉ መግለጫ
====================
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
በጠቅላላ ጉባኤ አባላት የተሰጠ መግለጫ
ግንቦት 18/2014
ከዛሬ 3 አመት በፊት በዚሁ መድረክ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በደስታ ሲቃ እንባ የተራጩበትና ለተቋማዊ ግንባታ በአንድነት ትልቅ ተስፋ ሰንቀው ያከበሩት ታሪካዊ ክስተት ነበር። ይኸውም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን በጊዜያዊነት ለመምራት በሚያዚያ 23/2011 በሸራተን ጉባኤ በአዲስ መልክ የተቋቋመው 26 ዑለሞችን እና 7 የስራ አመራር ቦርድን ያቀፈ አደረጃጀት መሆኑ ይታወቃል።
ይህ የሸራተን ጉባኤ ለጊዚያዊ መጅሊሱ ያሸከመው አማና:-
• የመጅሊሱን መተዳደሪያ ደንብ፣ የዑለሞች የአንድነትና የትብብር ሰነዶችን ለባለ ድርሻ አካላት በማቅረብ ማፅደቅ፤
• የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በአዋጅ የተረጋገጠ ህጋዊ እውቅና እንዲያገኝ ክትትል ማድረግ፤
• ምርጫ በማድረግ ተቋሙን የሚመሩ የህዝበ ሙስሊሙን ተመረጮች በማስመረጥ ተቋሙን ለተመራጮች ማስረከብ መሆኑ ይታወሳል።
ይሁን እንጂ ከአዋጁ በስተቀር የስራ አስፈፃሚው አንዱንም ተግባራዊ ማድረግ ሳይችል ሶስት አመታትን አስቆጥሯል።
ጉባኤው በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካኝነት በተቋቋመው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የጋራ ኮሚቴ (በ9ኙ ኮሚቴ) የተጠራና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የከፈቱትን፣ የሰላም ሙኒስትር ሚኒስትርም በታዛቢነት የታደሙበት እና ከተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የተወከሉ ከ500 በላይ የሚሆኑ ዑለሞች፣ምሁራን፣ዱአቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ታዋቂ ግለሰቦች የተገኙበት ታላቅ ሀገራዊ ሸንጎ ነበር።የዚህ ሸንጎ ውጤት የሆኑት 26 ዑለሞች እና 7 የስራ አመራር ቦርድ አባላት ለጉባኤው ተሳታፊዎች መጅሊሱን በጊዚያዊነት እንዲመሩ በጋራ ኮሚቴው የተመረጡ መሆናቸው ተነግሮና በጉባኤ ፊት እንዲቀርቡ ከሆነ በኃላ በሙሉ ድምፅ (በኢጅማእ) የተመረጡ ነበሩ።
ውሳኔውም በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ከፍተኛ ደስታን የፈጠረ ከመሆኑም ባሻገር ተቋሙም ለውጡ መስመር ይዟል የሚል ከፍተኛ ተስፋ እንዲሰንቅ አድርጎት ነበር።
ሆኖም ጊዚያዊ ስራ አስፈፃሚው አመራር የተሰጠውን ኃላፊነት መወጣት ሳይችል ይባስ ብሎ
– የሸራተኑን ጉባኤ ውሳኔ በመጣስ
– በዱባይ የተደረገውን ስምምነት በመጣስ
– የሹራ (የውይይት) አደብን በመጣስ
– የክልል መጅሊሶችን እንዳይደራጁ በግራ ስምምነት የተደራጁትንም እንዲፈርሱ የአስተዳደር ስርአት በመጣስ ጣልቃ መግባት
-ከሁሉም በላይ የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት ከፍተኛ አደጋ ላይ በመጣል---
በማን አለብኝነት ስሜት በጉባኤው የተሾሙትን በርካታ ዑለሞች እና የስራ አመራር ቦርዱን ህገ ወጥ በሆነ መልኩ በማገድና በማባረር ተቋሙ የጥቂት ግለሰቦች መፈንጫ እንዲሆን አድርገውታል። በዚህም ድርጊታቸው ህዝበ ሙስሊሙ ሀገራዊ ሚናውን በተገቢው መልኩ እንዳይወጣ አድርገዋል።
ጊዚያዊው የስራ አስፈፃሚው የህዝብ አማናን ካለመወጣቱ ባሻገር በርካታ ህገ-ወጥ ተግባራትን ሲፈፅም በመቆየቱ በህገ-ወጥ መልኩ የተባረሩ ዑለሞች እና የስራ አመመራር ቦርዱ እንዲሁም ህዝበ ሙስሊሙ ሲታገላቸው ቆይቷል።እየታገላቸውም ይገኛል።
ከዚህ ሁሉ አፍራሽ ተግባራቸው ጀርባ መንግስት እንዳለና ማንም የሚነቀንቀን የለም በሚል የሚያስተላልፋት መልእክት በመንግስትና በህዝበ ሙስሊሙ መካከልም ከፍተኛ የሆነ ቅሬታ እንዲፈጠር ምክንያት ሆነዋል።
የዑለማዕ ም/ቤቱ የሀገራችንን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነገሮችን በስክነት እና በከፍተኛ ትእግስት ሲከታተል ቆይቷል። በመጨረሻም 25 ዑለማዎች ከ መጋቢት 17 እስከ 24/2014 በመተዳደሪያ ደንቡ ዙሪያ የመንግስት ታዛቢዎች ባሉበት ጥልቅ ውይይት ተደርጎበታል። ከውይይቱ በኃላም ለህዝበ ሙስሊሙም በመንግስት ሚዲያ ሸዋል 10 ከተለያዩ አካላት 105 ዑለሞች፣ ሙህራንና ዳዒዎችን በማሳተፍ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ ተጨማሪ ረቂቅ ሰነዱን የሚያዳብሩ አስተያየቶች ከተሰበሰቡ በኃላ በ25 በሸራቶን በተመረጡ ዑለሞች እንደሚፀድቅ በሙሉ ድምፅ ስምምነት ላይ የተደረሰ መሆኑን በፊርማቸው ጭምር አረጋግጠዋል።
በዚሁ መሰረት የዑለማእ ም/ቤቱ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ ጥልቅ ውይይት ከተደረገና ተገቢ የሆኑ ማሻሻያዎች ከተካተቱበት በኃላ ውይይቱ ላይ የተገኘን የዑለማዕ ም/ቤት አባላት መተዳደሪያ ደንቡን በሙሉ ድምፅ አፅድቀነዋል። ሆኖም ለውጡ እውን እንዲሆን ያልፈለጉና ቃላቸውን ያጠፋ ጥቂት የዑለማዕ ም/ቤት አባላት ከውይይቱ ወደ ኃላ ያሉ መሆናቸውን ለህዝበ ሙስሊሙ ማሳወቅ እንወዳለን።
በመሆኑም ብዝኋኑ የጠቅላላ ጉባኤው አባላት ስብሰባዎችን በመቀጠል
1. የመተዳደሪያ ደንቡን አፅድቋል።
2. የምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስይሟል።
3. የምርጫ መረሃ ግብር ተቀምጧል።
4. አላግባብ ታግደው የነበሩት የዑለማ እና ስር አመራር ቦርድ አባላት ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ተወሰኗል።
5. በሙስሊሙ አንድነት እና ተቋማዊ ሂደት ላይ ከፍተኛ እንቅፋት የነበሩትን አመራር በመቀየር ካሉት የጠቅላላ ጉባኤ አባላት መካከል አዳዲስ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን ሰይሟል። እንዲሁም የሙስሊሙን መንፈሳዊና ሐይማኖታዊ ጉዳዮች የሚመራ ራሱን የቻለ አካል ተቋቁሟል።
እነዚህን ዋና ዋና ውሳኔዎች መሰረት በማድረግ ከአራት ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ መጅሊስ ለማቋቋም የሚደረገውን ሂደት ተጨባጭ ማሳያዎች እንደሚሆኑ ከፍተኛ እምነት አለን።
በመሆኑም ይህንን ሂደት እስካሁን ድረስ ከ3 አመታት በላይ ሳይሳካ በመዘግየቱ ህዝበ ሙስሊሙን ይቅርታ እየጠየቅን አሁን በተፈጠረው ዳግማዊ ዕድል በመጠቀም ማሳካት ይቻል ዘንድ ይህ ባለ 6 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል።
1· የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ጠቅላላ ጉባኤ የተቋሙ የበላይ አካል እንደመሆኑ መጠን መተዳደሪያ ደንብ በተሰጠው ስልጣን የወሰናቸውን ውሳኔዎች በመተግበር መንግስት ኃላፊነቱን እንዲወጣ አበክረን እንጠይቃለን
2. የሙስሊሙን አንድነት የማይሹ ከመጅሊሱ አመራር ድረስ በተቆናጠጡት ስልጣን እና በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች ለሃገር ሰላም እና አንድነት ሲባል ለአመታት በትዕግስት እና በመቀራረብ ሲደረግ የነበረው ጥረት ካሁን በኋላ ሙስሊሙ እንደማይታገሳቸውና ከድርጊታቸው የማይታቀቡ ከሆነ ለህግ እንደሚያቀርባቸው አጥብቀን እናስገነዝባለን፣
3. የተቋም ግንባታ ሂደት አላማውን ለማሳካት በቆረጡ አካላት ካልተመራ ትርፉ ከፍተኛ የሃገር ሃብት ብክነት ብቻ ሳይሆን የተቋም ብሎም የህዘብና የሃገር ሰላም እስከማወክ እንደሚደርስ የመጅሊሳችን ያለፉት 3 አመታት ጉዞ አሳይተውናል። በመሆኑም ይህ ዳግም እንዳይከሰት ህዝበ ሙስሊሙ፣ የክልል መጅሊስ ተወካዮች እና የሚመለከታችሁ አካላት ይህንን ሽግግር በማሳካት ረገድ የበኩላችሁን ሚና እንድትጫወቱ ከአደራ ጭምር እናሳስባለን።
4. በፀደቀው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን እስከ መስከረም 30 ምርጫው እንዲደረግ የወጣውን መርኃ ግብር ለማሳካት ህዝበ ሙስሊሙ በንቃት እንዲከታተል እና እንዲሳተፍ ጥሪ እናቀርባለን።
1.4K viewsᴇᴅƦɪS ɴᴀᴡҒᴀʟ, 13:48