2022-05-28 19:26:53
«እኔ ስልጣን አልፈልግም» እያሉ በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚናገሩት ሐጅ ዑመር እድሪስ ተስማምተው ለፈረሙበት ቃላቸው ጭምር የማይታመኑ፣ ሕግና መመሪያን ሲጥሱ ጭራሽ ማፈርም ሆነ መሳቀቅ የማያውቁ፣ የመጅሊስን ችግር በመነጋገርና በሽምግልና ለመፍታት ስድስት የተለያዩ የሽማግሌ ቡድኖች ተቋቁመው ሁሉንም ሙከራ አድረገው በርሳቸው አምብተኝነት የከሸፉ ናቸው።
በእስቴ መስጊዶች ሲቃጠሉ ዝምታን መርጠው፣በቢቸና መሰጊድ ላይ ቦንብ ተወርዉሮ ሙስሊሞች ሲገደሉ ባለየ አልፈው፣በሞጣ ሙስሊሞች ላይ ሽብር ሲፈጸም ድምጻቸውን አጥፍተው፣ነጃሺ መስጊድ ሲጠቃ በተአቅቦ አልፈው፣በወሎ ያሁሉ የሱፊያ ሀሪማ ሲወድም ሱፍይነት ትዝ ብሏቸው እንድረስላቸው ሳይሉ፣ ሰበጎንደር ሙስሊሞች ሲገደሉና የሽብር ጥቃት ሲፈፀምባቸው እንደመሪ ተቆጥተው ፍትህ መጠየቅ ሲገባቸው «የጎዳና ላይ ኢፍጣር በእስልምና የለም» ብለው ለከሳሾቸ ዋቢ ምስክር የሆኑት ሰው፣ የመጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤ ከመሪነት አንስቶ በፈትዋ ዘርፍ ሲመድባቸው ለኢስላምና ለሙስሊሞች መብት ተቆርቁረው ለመናገር ምላሳቸውን የያዛቸው በስልጣኔ መጡ ስሜት ተሞልተው «ተነሱ።ለትግል ተዘጋጁ።» ብለው ወደ ደም መፋሰስ ሀጂ ዑመር የቀሰቀሱት «አላህ ሽቶባቸው ነው እንጂ ለስልጣን ብለው እይደለም እኮ።» ብሎ የሚያስብ የዋህ አይጠፋም።
ያም ሆኖ ተቋሙ የሕዝበ ሙስሊሙ እንጂ የእርሳቸው የግል ርስት ስላልሆነ የመጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤ በድምጽ ብልጫ እሳቸውና ሌሎች 3 ዑለሞች ወደፈትዋ ክፍል እንዲዛወሩ ውሳኔ አሳለፈ። ይህንን የወሰኑት ዑለሞች ናቸው።
ሙፍቲ ይህን ሁሉ ሲያደርጉ የቆዩት በሕግም በሸሪዓውም የሌሎችን ዑለሞች የአብላጫ ውሳኔ የመሻር ቬቶ ስላላቸው ሳይሆን በተግባር ለአንድነት እየተባለ እየታለፉ፣ በተጨማሪም እርሳቸውን "አይዞህ" በሚላቸው ስውር አካል እየተደገፉ ነው ያሻቸውን ሲፈጽሙ የቆዩት። በተደጋጋሚ መመሪያ ተጥሷል። ስምምነት ተሽሯል። እርሳቸው የሚፈልጉት ካልሆነ እንደማይስማሙ እየታወቀ በስምምነት እንጂ በድምጽ ብልጫ አትወስኑ እየተባለላቸው የህዝበ ሙስሊሙ መብትና ጥቅም ላይ እንዲረማመዱ ተፈቅዶላቸዋል።
እርሳቸው አሁንም ከሕግም ከመመሪያም በላይ ሆነው ለመቀጠልና «ደም ይፈሳታል እንጂ» እንዳሉት ሁሉ ሙስሊሞችን ለማበጣበጥና ደም ለማፋሰስ ጥረታቸውን ቀጥለዋል። ይህ ግን በዝምታ ሊታይ አይገባም።
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የእነርሱ የሆነና ለእነርሱ የቆመ፣ በሕግ የበላይነት የሚመራ ጠንኳራ ተቋም ባለቤት የመሆን መብታቸውን በተግባር መጎናጸፍ ከፈለጉ ጠንክረው መቆም አለባቸው። የየትኛውንም ግለሰብ ማስፈራሪያ በመስማት ከህግ የበላይነት ይልቅ ግለሰቦችን ኡሹሩሩ ማለት መቆም አለበት። ይህን እሹሩሩ ሳያቆሙ የታሰበው የሕዝበ ሙስሊሙ ተቋም ፈጽሞ እውን ሊሆን አይችልም።
1.7K viewsᴇᴅƦɪS ɴᴀᴡҒᴀʟ, 16:26