Get Mystery Box with random crypto!

#ሱዳን የሱዳን የጦር ኃይል “አማፂ” ቡድን ብሎ በቅርቡ የፈረጀውን የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ልዩ ኃ | ebstv worldwide📡☑️

#ሱዳን
የሱዳን የጦር ኃይል “አማፂ” ቡድን ብሎ በቅርቡ የፈረጀውን የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ልዩ ኃይል ወታደሮች በአስቸኳይ እጅ እንዲሰጡ ጥሪ ማቅረቡ ተሰማ፡፡

የሱዳን የመከላከያ ሰራዊት፣ መንግስት ከልዩ ኃይሉ ጋር አንዳች ድርድር እንደማያደርግ ሲገልፅ የልዩ ኃይሉ ወታደሮችም በአስቸኳይ እጅ እንዲሰጡ አዟል ተብሏል፡፡
የሀገሪቱ ጦር ያሳለፈው ውሳኔ የተኩስ አቁም በሱዳን እንዲደረግ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የተጀመረውን ጥረት እንዳይጐዳው መሰጋቱ ነው እየተነገረ ያለው፡፡
በመዲናዋ ካርቱም በተለያዩ አካባቢዎች የከባድ መሳሪያዎች ድምፅ እንደሚሰማ እና ውጊያው ተባብሶ መቀጠሉ እየተዘገበ ነው ።
ዘገባው የአሶሼትድ ፕሬስ ነው ።

#የተናጠል የተኩስ አቁም
የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ልዩ ኃይል ለ 72 ሰአታት የሚዘልቅ የተናጥል የተኩስ አቁም ማድረጉን አስታወቀ ።

በሀገሪቱ እየተባባሰ የመጣውን ግጭት ለማቆም የፈጥኖ ደራሽ ልዩ ኃይሉ ለ72 ሰአታት የሚፀና የተናጥል የተኩስ አቁም ማወጁን ይፋ ሲያደርግ የሱዳን የጦር ኃይል ግን የተኩስ አቁሙን ለማድረግ አለመስማማቱ ነው የተዘገበው ።
ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የተኩስ አቁም ቢያወጅም በአገሪቱ ዛሬም ውጊያው ተባብሶ መቀጠሉ ነው የተነገረው፡፡
የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለኢድ አልፈጥር በዓል ሲባል ተፈላሚ ኃይላቱ የሰብአዊ ድጋፍ መስጫ የግጭት ማቆም እንዲደረስ ተማጽነዋል ተብሏል።
ዘገባው የሲ ኤን ኤን ነው፡፡

#የአሜሪካ የመከላከያ ሰራዊት በጅብቲ
በሱዳን የቀጠለውን ቀውስ ተከትሎ የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር ተጨማሪ ወታደሮችን በጅቡቲ ሊያሰማራ እቅድ መያዙ ተነገረ፡፡

የመከላከያ ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ በሱዳን በቀጠለው ግጭት ሳቢያ በካርቱም ያሉ የአሜሪካ ኤምባሲ ሰራተኞችን ለማውጣት ሲባል የአሜሪካ ወታደሮች በጐረቤት አገር ጅቡቲ ሊሰማሩ መሆኑን ነው ይፋ ያደረገው፡፡
የአሜሪካ የብሔራዊ ደህንነት ቃለ አቀባይ ጆን ኪርቢ ለአልጀዚራ እንዳሉት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የአሜሪካ ጦር በጀቡቲ ለሚኖረው ስምሪት ዝግጁ እንዲሆን ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፕሬዚዳንት ባይደን አስተዳደር በሱዳን ግጭት እየተፋለሙ ባሉት የሱዳን ጦር እና የልዩ ኃይሉ አመራሮች ላይ ማዕቀብ ሊጥል እያቀደ መሆኑ ነው የተሰማው፡፡
ዘገባው የአልጀዚራና ፎሪን ፖሊሲ ነው።

#ሕንድ
የሕንዱ የሴረም ተቋም ተስፋ የተጣለበትን አዲሱን 20 ሚሊዮን ብልቃጥ የ"R 21" የተሰኘውን የወባ ክትባት ለአፍሪካ ሀገራት ማቅረብ እንደሚችል አስታውቋል።

የሴረም ተቋም ለአፍሪካ 20 ሚሊየን የ “R 21” የተሰኘውን የወባ ክትባት በ2 ወራት ውስጥ ማቅረብ እንደሚችል የተነገረው 10 የአፍሪካ አገራት ለወባ ክትባቱ ፈቃድ ሊሰጡ በዝግጅት ላይ መሆናቸው እየተነገረ ባለበት ጊዜ ነው ።
ዘገባው የሮይተርስ ነው፡፡