Get Mystery Box with random crypto!

#ሱዳን የሱዳን ጦር እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ለሁለተኛ ጊዜ የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸውን | ebstv worldwide📡☑️

#ሱዳን
የሱዳን ጦር እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ለሁለተኛ ጊዜ የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸውን አስታወቁ ።

የሱዳን ጦር እና የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ለሁለተኛ ጊዜ የግጭት ማቆም ለማድረግ ፈቃደኛ መሆናቸውን ነው በተናጥል ባወጡት መግለጫ ያስታወቁት ።
የዋይት ሐውስ የፕሬስ ጉዳዮች ኃላፊዋ ጂያን ፒሬ የጦር መሪዎቹ ለሁለተኛ ጊዜ ይፋ ያደረጉትን አበረታች የተኩስ አቁም ስምምነት ለማስከበር ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡
ዘገባው የአሶሺየትድ ፕሬስ ነው።

#ሕንድ
የመንግስታቱ ድርጅት ሕንድ በአውሮፓውያኑ 2023 አጋማሽ አመት በሕዝብ ብዛት ቁጥር ቻይናን በልጣ የአንደኛነት ደረጃን እንደምትይዝ በትንበያው ይፋ አደረገ፡፡

ሕንድ አሁን ካላት ከ 1.4 ቢሊዮን ሕዝብ በላይ ከወራት በኋላ አዲስ 2.9 ሚሊዮን ሕዝብ በመጨመር በሕዝብ ብዛት ከቻይና በልጣ የዓለም ቀዳሚዋ ሀገር እንደምትሆን ነው የመንግስታቱ ድርጅት ያስታወቀው ።
ዘገባው የሮይተርስ ነው፡፡

#ስፔን
የስፔን ተመራማሪዎች በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ በሮቦት የታገዘ ውጤታማ የቀዶ ጥገና ህክምና ለአንድ የሳንባ ነቀርሳ ታማሚ ማካሄድ መቻላቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

የስፔን ተመራማሪዎች ለ65 አመቱ የሳንባ ነቀርሳ ታማሚ በሮቦት ያካሄዱት ቀዶ ጥገና ከዚህ ቀደም የተለመደውን የጐድን አጥንት በመስበር የሚካሄደውን ቀዶ ጥገና ያስቀረ እና ለቀዶ ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚው ፍቱን እና ህመምን ያስወገደ ነው ተብሏል፡፡

“ዳ ቪንቺ” በተባለችው ሮቦት ለአዛውንቱ የሳንባ ነቀርሳ ታማሚ ቀዶ ያደረጉት የህክምና ቡድኑ መሪ ዶ/ር አልበርት ጃውሬጊዮ ይሄው መላ አዲስ ፣ ፍቱን እና የቅድመ እና ድህረ ቀዶ ህክምና ህመመምን ሁሉ የሚቀንስ ነው ብለዋል ።
የቀዶ ህክምና የተደረገላቸው አዛውንቱ በአገልግሎቱ ከህመማቸው የተሻላቸው መሆኑን እና አሁን ደስተኛ ነኝ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዘገባው የቲ አር ቲ ወርልድ ነው፡፡