Get Mystery Box with random crypto!

#ሱዳን የዓለም የጤና ድርጅት በሱዳን ለ6ኛ ቀን በቀጠለው ግጭት በትንሹ 296 ንጹሃን ዜጎች መሞ | ebstv worldwide📡☑️

#ሱዳን
የዓለም የጤና ድርጅት በሱዳን ለ6ኛ ቀን በቀጠለው ግጭት በትንሹ 296 ንጹሃን ዜጎች መሞታቸውንና 3ሺ የሚበልጡ ንፁሃን ሰዎች መቁሰላቸውን አስታወቀ።

በሱዳን ዋነኛ የጦርነቱ አውድማ ከሆነችው መዲናዋ ካርቱም በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን መሸሽ መጀመራቸው ተነግሯል፡፡
"ዶክተርስ ሲንዲኬት" የተባለ የጤና ባለሙያዎች ቡድን ካርቱም እጅግ ከባድ ውጊያ ፣ ዘረፋ እና ሌሎች ወንጀሎች አየተፈፀመባት መሆኑን ነው ያስታወቀው::
የሱዳን ጦር በካርቱም እና በኦምድሩማን ከተማ በጦር አውሮፕላን በሚያካሂደው ድብደባ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የሚጠቀምባቸውን የጦር ሰፈሮች መቆጣጠር መቻሉን ነው የተሰማው፡፡
ዘገባው የአሶሺየትድ ፕሬስ ነው፡፡