2020-11-03 03:37:07
ፓስፖርት በ‘ኦንላይን’ እንዴት ማደስ/
ማውጣት ይቻላል?
01-11- 2020
የኢሚግሬሽን ዜግነትና የወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ተጠቃሚዎች በድረ-ገጽ
አማካኝነት አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት እና ለማደስ ቀጠሮ ማስያዝ
የሚያስችል ድረ-ገጽ ይፋ አድርጓል።
https://www.ethiopianpassportservices.gov.et/#/Information
በሚለው የኤጀንሲው ድረ-ገጽ ላይ አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት፣ ጊዜው ያበቃ
ወይም የተበላሸ ፓስፖርት ለማሳደስ፣ የጠፋ ወይም የተሰረቀ ፓስፖርትን በአዲስ
ለመተካት እና ፓስፖርት ላይ የተመዘገበ መረጃ ለመቀየር አገልግሎት የሚፈልግ
ወደ ድረ-ገጹ መሄድ ይችላል።
የአገልግሎት ፈላጊዎች ቁጥር ከፍ ያለ ሊሆን ስለሚችል የሚፈልጉትን
አገልግሎት በወቅቱ ለማግኘት ቀድመው ቀጠሮ ይያዙ። ለምሳሌ ዛሬ ላይ
ሆነው ለነገ ቀጠሮ ማግኘት ላይችሉ ይችላሉ።
አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት በቅድሚያ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ያዘጋጁ። የታደሰ
የቀበሌ መታወቂያ እና የልደት ሰርተፊኬት ያስፈልጋል። እነዚህን መረጃዎች ድረ-
ገጹ ላይ ስለሚጫኑ ሰነዶቹ ‘ስካን’ መደረግ ይኖርባችኋል።
ወደ ድረ-ገጹ ያምሩ። ቅጾቹን በጥንቃቄ ይሙሉ፤ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ እና
የልደት ሰርተፊኬት የሚጠይቀው ቦታ ላይ ‘ስካን’ ያደረጉትን ሰነድ ይጫኑ።
ከሚቀርቡት ሁለት የክፍያ አማራጮችን አንዱን ይምረጡ። ማመልከቻዎን
ካስገቡ በኋላ በስልክዎ ላይ በሚላከው አጭር የጽሑፍ መልዕክት ወይም
በኢሜል የሚወጣውን ኮድ ተጠቅመው ክፍያዎን ይፈጽሙ።
አዲስ ባለ 32 ገጽ ፓስፖርት 600 ብር የሚከፈልበት ሲሆን፣ ለ ባለ 64 ገጽ
ፓስፖርት ደግሞ 2186 ብር ይጠየቃሉ። የቀጠሮዎ ቀን እና ሰዓት የተጠቀሰበትን
የማመልከቻዎን የመጨረሻ ገጽ አትመው ይያዙ።
በቀጠረዎ ዕለትም የቀጠሮ ወረቀትዎን፣ አስፈላጊ የሆኑ ዋና እና ኮፒ ሰነዶችን
ይዘው ይገኙ። ፓስፖርት ለማውጣትና አገልግሎቱ ያበቃ ፓስፖርት ለማሳደስም
ተመሳሳይ ቅደም ተከተሎችን ይከተላሉ።
በተጨማሪም ፓስፖርትዎን ለማሳደስ አገልግሎቱ ያበቃው ፓስፖርት
“ኢንፎርሜሽን ፔጅ” ተብሎ የሚጠራውን አንጸባራቂ ገጽ ፎቶ ኮፒ ያድርጉ።
የፓስፖርት “ኢንፎርሜሽን ፔጅ” ማለት ፎቶ ግራፍዎ የታተመበት ገጽ ማለት
ነው።
በተመሳሳይ ፓስፖርት ለማሳደስ የሚጠየቁት እንደየ ገጹ ብዛት 600 ብር እና
2186 ብር ነው። የጠፋ ወይም የተሰረቀ ፓስፖርትዎን በአዲስ ለመተካት ወደ
ኤጀንሲው ድረ-ገጽ በማምራት ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ።
ፓስፖርትዎን በአዲስ ለመተካት
ፓስፖርትዎን በአዲስ ለመተካት አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት እንደሚያደርጉት
ተመሳሳይ ቅድመ ተከተሎችን ይከተላሉ። ፓስፖርትዎ ለመጥፋቱ/ለመሰረቁ ግን
ከፖሊስ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርብዎታል።
የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ እና የፓስፖርቱ ኮፒ ካለዎትም ዝግጁ ያድርጉ።
በተመሳሳይ በድረ-ገጹ ላይ የሚቀርብልዎትን ቅጽ ይሙሉ። ከፍያውን ይፈጽሙ።
በቀጠርዎ ቀን ሰነዶችን ያቅረቡ።
የመረጃ ለውጥ
በፓስፖርትዎ ላይ ተመዝግቦ የሚገኝ፣ ለምሳሌ የስም፣ የትውልድ ቀን ወይም
የትውልድ ስፍራ፣ መረጃ እንዲቀየር ከፈለጉ፤ የፍርድ ቤት ወረቀት
ያስፈልግዎታል።
በመቀጠል አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት እንደሚያደርጉት ተመሳሳይ ቅድመ
ተከተሎችን ይከተላሉ። አስቸኳይ አገልግሎት ለማግኘት ከላይ የተጠቀሱትን
አገልግሎትን በአስቸኳይ ማግኘት ከፈለጉ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት አንዱን
ማቅረብ ይኖርብዎታል።
ከአገር ውጪ ወጥተው መታከም እንደሚኖርብዎ የሚያስረዳ የሐኪም ደብዳቤ
(የሕክምና ቀጠርዎ ሊሆን ይችላል)፣ ከተፈቀደላቸው ተቋማት የድጋፍ ደብዳቤ፣
የውጪ አገር መኖሪያ ፍቃድ፣ የግብዣ ደብዳቤ፣ አስቸኳይ የሥራ ጉዞ፣
የትምህርት ዕድል ወይም ዲቪ ሎተሪ እድለኛ መሆንዎን የሚያሳይ ማስረጃ፣
በሃዘን ወይም ደስታ የሚደረግ ጉዞ መሆኑን የሚያሳይ ሰነዶች ሊሆኑ ይችላሉ።
አስቸኳይ አገልግሎት ተጨማሪ ክፍያ ይጠየቅበታል። የሚጠየቁትን ተጨማሪ
ክፍያ ለመክፈል ዝግጁ ይሁኑ። ያስታውሱ ከላይ የተጠቀሱ አገልግሎቶችን
ለማግኘት በአካል መቅረብ ግዴታ ነው።
ይህ መረጃ ያገኘነው ከኤጀንሲው ድረ-ገጽ ነዉ
35.3K views00:37