Get Mystery Box with random crypto!

Doctor M nursing Home care

የቴሌግራም ቻናል አርማ doctormhomecare — Doctor M nursing Home care D
የቴሌግራም ቻናል አርማ doctormhomecare — Doctor M nursing Home care
የሰርጥ አድራሻ: @doctormhomecare
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.49K
የሰርጥ መግለጫ

በሙያቸዉ በተካኑ የጤና ባለሙያወች 24ሰአት ቤትወ ድረስ መጥተን የነርሲንግ አገልግሎት እንሰጣለን።
ይደውሉ
0920108524
0923284867

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-08 06:40:56
949 views03:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 13:30:29
8ቱ ደም የመለገስ የጤና ጥቅሞች

1. አዲስ የደም ሴል ምርትን ያነቃቃል
2. የልብ ድካምን እና የደም ቧንቧ በሽታዎችን ለመቀነስ ይረዳል
3. የካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል
4. የደም ኮሌስትሮል መጠንን ይቀንሳል ፤ እንዲሁም ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል
5. ጤናማ ጉበት እንዲኖረን ይረዳል
6. የደም ውስጥ የ iron መጠንን በመቆጣጠር Hemochromatosisን(ጤናማ ያልሆነ የ iron ክምችትን) ይከላከላል
7. ነፃ የጤና ምርመራ ያገኛሉ
8. Psychologically speaking, የለገሱት ደም የሌሎችን ህይወት ለማዳን እንደሚውል ባሰቡ ጊዜ በራስ የመተማመን ስሜትዎን ይጨምራል ፡፡

የሰውን ሕይወት ለማዳን ግዴታ የጤና ባለሙያ መሆን የለብዎትም!

470 ሚ.ሊ(ml) ደም መለገስ የ 3 ሰዎችን ህይወት ሊያድን ይችላል!

አሁኑኑ ደም ይለግሱ ፤ ሕይወትን ያድኑ!

Dr. Eyob Dagnew

@Doctormhomecare
2.1K viewsedited  10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 11:15:00 የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን

የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን እጅግ በጣም የተለመደ እና ከአራት ሴቶች በሶስቱ ላይ በዕድሜ ዘመናቸው ቢያንስ አንዴ የሚከሰት የሕመም ዓይነት ነው፡፡
የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን ከአባለዘር በሽታዎች ውስጥ የማይመደብ ሲሆን ቀላል በሚባል ሕክምና ሊድን የሚችል ነው፡፡ በዓመት ውስጥ ከ4 እና ከዛ በላይ የሚከሰት ከሆነ ግን ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ሕክምና ያስፈልገዋል፡፡
የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን የሚከሰተው ካንዲዲያ (Candidia) በሚባል ፈንገስ ምክንያት ነው፡፡

በሴቶች ማህፀን በተፈጥሮ የሚገኙ የፈንገስ እና የባክቴሪያ ሕዋሳት አሉ፡፡ ሁለቱም በተመጣጠነ ሁኔታ የሚገኙ ሲሆን ባክቴሪያው አሲድን በማመንጨት የፈንገስ መብዛትን ይከላከላል፡፡ ይህን ተፈጥሮአዊ መመጣጠን የሚያዛባ ሁኔታ ለፈንገስ መባዛት (yeast overgrowth) ስለሚዳርግ የማህፀን ማሳከክ፣ማቃጠል እና ሌሎች ምልክቶችን ያስከትላል፡፡

የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን በምን ምክንያት ይከሰታል?

- ፀረ ባክቴሪያ(Antibiotic)መውሰድ ወይም በማንኛውም ዓይነት ሁኔታ በማህፀን ውስጥ የሚገኘውን የባክቴሪያ መጠን ሲቀንስ
- እርግዝና
- በሕክምና ያልተስተካከለ የስኳር ሕመም
- በሽታ የመከላከል አቅም ሲዳከም
- የኤስትሮጂን ሆርሞን መጠን መጨመር
የኤስትሮጂን መጠኑ ከፍተኛ የሆነ የወሊድ መቆጣጠሪያ

የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን ምልክቶች ምንድን ናቸው?

- በማህፀን አካባቢ ማሳከክ
- ሽንት በሚሸናበት ጊዜና በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት የማቃጠል ስሜት
- የማህፀን አካባቢ መቅላትና ማበጥ
- የማህፀን ሕመም
- ነጭ፣ወፍራም እና ሽታ አልባ የማህፀን ፈሳሽ መኖር ናቸው፡፡

ከባድ የሆነ የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን መኖሩን የሚያመለክቱ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?

- ከፍተኛ የሆነ የማህፀን ማሳከክ፣ማበጥ እና መቅላት
- በዓመት ውስጥ አራት ጊዜና ከዚያ በላይ የሚከሰት የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን
- ነፍሰጡር ሴት ላይ የሚከሰት የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን
- በሕክምና ያልተስተካከለ የስኳር ሕመም መኖር
- ከተለመደው የፈንገስ ዓይነት ውጪ የፈንገስ ዓይነቶች የሚከሰት ኢንፌክሽን

የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽንን እንዴት መከላከል ይቻላል?

- የማያጠብቁ (ዘና የሚያደርጉ) የውስጥ ሱሪዎችን መልበስ
- ከጥጥ የተሠሩ የውስጥ ሱሪዎችን መልበስ
- ዕርጥበት ያላቸውን የውስጥ ሱሪዎች ለብሰው አለመቆየት ለምሳሌ የዋና ልብስ
- በጣም በሚሞቅ ውሃ አለመታጠብ ወይንም አለመዘፍዘፍ
- የግል ንጽህናን በሚገባ መጠበቅ

ሐኪምዎን ማማከር ያለብዎት መቼ ነው?

- በሕመሙ ሲጠቁ የመጀመሪያዎ ከሆነ
- በማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን መያዝዎን እርግጠኛ መሆን ካልቻሉ
- የሕመሙ ምልክቶች ሐኪምዎ በሚሰጥዎት መድኃኒት ካልጠፋ
- ሌሎች ተጨማሪ ምልክቶችን ካስተዋሉ

የሕመሙን ምልክቶች እንዳስተዋሉ ታክመው መድኃኒት በመውሰድና በሚገባ በመጠቀም ከሕመሙ ነፃ መሆን ይችላሉ፡፡

@Doctormhomecare
2.2K views08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 11:14:44
1.5K views08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 19:48:11 በሰባት የአፍሪካ አገራት ከ1 ሺህ 400 በላይ በዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

በቫይረሰ መያዛቸው ሙሉ በሙሉ የተረጋገጡት ግን 44ቱ ብቻ ናቸው። ቫይረሱ ካሁን ቀደምም የተለመደባቸው እና አሁንም የተገኘባቸው አገሮች፣ ካሚሮን፣ ማዕከላዊ አፍሪካ፣ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ፣ ላይቤሪያ፣ ናይጀሪያ፣ ኮንጎ እና ሴራሊዮን ናቸው። ሆኖም ከእነዚህ አገራት ውጭ እስካሁን ቫይረሱን ሪፖርት ያደረገ የአፍሪካ አገር እንደሌለ ድርጅቱ አመልክቷል።

@Doctormhomecare
2.0K views16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 09:23:34
#ጤናመረጃ

ቲማቲም ለፊት ጥራት ያለው አስደናቂ ጥቅም!!

ቲማቲም ለቆዳችን እጅጉን ጠቃሚ ነው፡፡ ቲማቲም ከፍተኛ መጠን ያለው ቤታካሮቲን፣ ላይኮፔን እና ፍላቮኖይድስን አለው፤ ይህን ንጥረ ነገር ደግሞ ለፊት ጥራት ተብለው በውድ ዋጋ የሚሸጡ መዋቢያዎች ይጠቀሙበታል፡፡

በቀላሉ የምናገኘው ቲማቲምን በመጠቀም ቡጉርን፣ የቆዳ ጥቁረትንና ጥቁር ነጠብጣቦችን ከፊታችን ላይ ለማጥፋት ይረዳናል፣ በተጨማሪም ቲማቲም የቆዳን እርጅና እና መሸብሸብ ፍጥነትን የመቀነስ ችሎታ አለው፡፡

ለማዘጋጀት አስፈላጊ ነገሮች -

- 1 ቲማቲም
- 2 የሻይ ማንኪያ ስኳር
- 2 የሻይ ማንኪያ ማር
- 1 መለስተኛ የቡና ሲኒ >>

አዘገጃጀት

1) በመጀመርያ የፊታችን የቆዳችን ቀዳዳዎች መከፋፈት ስላለባቸው ፊታችንን በሙቅ ውሀ እንፋሎት መታጠን፡፡

2) ቲማቲሙን ይቆርጡና በሲኒ ላይ ይጨምቁታል፡፡
3) ጭማቂው ላይ ቅድሚያ ስኳሩን ቀጥሎ ማሩን ይጨምሩና ያዋህዱታል፡፡

4) ውህዱን ፊትዎ ላይ በስሱ ይቀቡታል ፡፡
5) ለ 2 ደቂቃ በዝግታ ያሹታል፡፡
6) ለተጨማሪ 2 ደቂቃ ደግሞ ባለበት ይተውታል፡፡

7) ባጠቃላይ ከ 4 ደቂቃ በኋላ በ ቀዝቃዛ ውሀ ይታጠቡታል፡፡ ማስጠንቀቂያ:- ለቲማቲም ሆነ ከላይ ለተጠቀሱት ውህዶች አለርጂክ ከሆኑ እንዲጠቀሙት አይመከርም፡፡ 
......
በተጨማሪም ቲማቲም ለቆዳ ጤንነት ያለውን ጥቅም በቀላሉ ሞክሮ ማየት ካስፈለገ የሚከተለውን ማድረግ ይቻላል።

ከ8 እስከ 12 የሚሆኑ ቲማቲሞችን ልጦ የልጣጩን የውስጠኛ ክፍል ፊት ላይ መለጠፍ፡፡ ቢያንስ ከ10 ደቂቃዎች በኋላ ልጣጮቹን አንስቶ ፊትን መታጠብ፡፡ ከዛም ይህንን በተደጋጋሚ በማድረግ ለውጡን ማስተዋል እንችላለን።

ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!

@Doctormhomecare
22.5K views06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 22:48:55 በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ግፊት (Hypertension in pregnancy)

ይህ የእርግዝና ጊዜ ግፊት 10% የሚሆነው እርግዝና ላይ የሚከሰት ሲሆን

እርጉዝ እናት ላይ ከፍተኛ ችግር ከሚፈጥሩት እና ለሞት በመዳረግ ከሚታወቁት ከማህፀንና እንግዴ ልጅ ደም መፍሰስ እና ኢንፌክሽን ቀጥሎ በሶስተኛነት የእናት ሞትን በማምጣት ይታወቃል።

አንዲት እርጉዝ እናት መቼ ነው ግፊት አለባት የሚባለው?

አንዲት እርጉዝ እናት ግፊት አለብሽ የምንለው ግፊቷ ከ 140 በ 90 በላይ ሲሆን ይህም ማለት የላይኛው ግፊት(systolic) ከ 140 እና ከዛ በላይ የታችኛው(Diastolic) ከ 90 እና ከዛ በላይ ከሆነ ፤ ይህም በአንድ ጊዜ ሳይሆን በሁለት ጊዜ ልኬት በ4 ሳዓታት ልዩነት መሆን አለበት።

የእርግዝና ጊዜ ግፊት ለመባል ግፊቱ የተከሰተው ከ 20 ሳምንት(ከ 5 ወር) በውሀላ መሆን ይኖርበታል።

አንዲት እርጉዝ ሴትን በእርግዝና ጊዜ ለግፊት የሚያጋልጧት ነገሮች ምንድን ናችው?

በቤተሰብ የደም ግፊት ከነበረ በእናት ወይም በእህት
በልጅነት እድሜ የተከሰተ እርግዝና ከ 20 አመት በታች
እድሜ ገፍቶ የተከሰተ እርግዝና ከ 40 አመት በላይ
ባለቤቷን ከቀየረች ይህም ማለት በፊት ሌላ ባል ኖሯት አሁን ደግሞ አዲስ ባል ካገባች በተለይ አሁን ያገባችው ባለቤቷ በፊት የነበረው ሚስት እርግዝና ላይ ግፊት ኖሯት ከነበረ
ከእርግዝና በፊት ግፊት ከነበረ
በበፊት እርግዝና ግፊት ከነበረ
ከፍተኛ የሰውነት ውፍረት
ሌሎች የስኳር እና የኩላሊት ህመሞች ከመፀነሷ በፊት ከነበረ
መንታ እና ከዛ በላይ እርግዝና ካለት ተጠቃሽ ናቸው።

በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የደም ግፊት መጨመር ምልክቶች ምንድን ናቸው?

ከፍተኛ የሆነ የራስ ምታት, ይህም በራስ ምታት መድሀኒት የማይመለስ እና የማይቆራረጥ
አይን ብዥ ማለት፣ መጨለም
ጨጓራ በሚያመን ቦታ እና በላይኛው ቀኝ የሆዳችን ክፍል ከፍተኛ የሆነ ህመም
የሰውነት ማበጥ በተለይ በፊታችንና በአይናችን ዙሪያ ፣ ሆዳችን እና እግራችን
በላብራቶሪ የሚታዩ የላብራቶሪ ችግሮች በተለይ የደም ውጤት ላይ፣ የጉበት ምርመራዎች ላይ፣ እና የኩላሊት ምርመራዎች ላይ መጨመር ካለ
የሽንት መጠን መቀነስ ካለ እና ላብራቶሪ ላይ የኘሮቲን መጠን ከጨመረ
ከላይ ላሉት ስሜቶች የህክምና እርዳታ ካላገኘሽ
እራስን መሳት
አረፋን መድፈቅ ፣ ማንቀጥቀጥ
እስከ ህይወት ህልፈት

በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ግፊትን እንዴት መከላከል ይቻላል?

ቅድመ ወሊድ ክትትል:- ይህም ግፊቱን በቶሎ እንዲገኝ እና መድሀኒትም ካስፈለገ ለመጀመር፣ ክትትልም መጨመር ካስፈለገ እንዲጨመር፣ ሀኪም ቤትም ገብተሽ ተኝተሽ መታከም ካስፈለገሽ ለመወሰን ይረዳል።

የበፊት እርግዝናሽ ላይ ግፊት ተከስቶ ከነበረ እና በዚህኛው ላይ ግፊቱ ከፍተኛ እንዳይሆን ወይም ቀድሞ ከዘጠኝ ወር በፊት በመምጣት ፅንሱ ላይ እና እናትየው ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ገና ከ3 እስከ 4 ወር አካባቢ ሊጀመርልሽ የሚችል መድሀኒት ይኖራል።

ከላይ የተዘረዘሩትን የግፊቱን ምልክቶች በማስተዋል እና ቶሎ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ችግሩ ወደ ከፋተኛ ደረጃ ደርሶ እናትም ላይ ፅንሱም ላይ ችግር ሳያደርስ ቶሎ መከላከል ይቻላል።

ህክምናው

ህክምናው የሚሆነው እንደተከሰተው የእርግዝና ላይ ያለ የግፊት አይነት ሲሆን፤

ከዘጠኝ ወር በፊት ከሆነ እንደየ ግፊቱ አይነት በጣም አጭር የቅድመ ወሊድ ክትትል ቀጠሮዎችን በመስጠት እና ለደም ግፊት የሚሆኑ መድሀኒቶችን በመስጠት ወይም ደግሞ ሆስፒታል በመግባት አልጋ ይዘሽ ፅኑ የሆነ ክትትል ላንቺም ለፅንሱም እየተደረገ ህክምናው ሊሰጥሽ ይችላል።

ሀኪምሽ ከፍተኛ የግፊት ደረጃ ላይ ከሆንሽ እና ከላይ የተጠቀሱት የግፊት ምልክቶች ካሉሽ በመድሀኒት ግፊትሽን በማስተካከል ሊከሰቱ የሚችሉትን አደጋዎች ባንቺ ላይ( ደም መፍሰስ፣ ማንቀጥቀጥ፣ እራስ መሳት እና ሞት ሳይከሰት) በፅንሱም( ውሀው ማነስ፣ ፅንስ መቀንጨር፣ ህይወት ማለፍ) ሳይኖር መቆጣጠር ይቻላል።

ሀኪምሽ አሁንም እርግዝናው ላይ እንደተከሰተው የግፊት አይነት በመለየት ፣ እንዳሳየሽው የግፊት ምልክት እና የላቦራቶሪ ውጤቶች መሰረት መቼ እንደምትወልጂ ይወስናል።

አስተውይ:- ይህ በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ግፊት እድሜ ሲገፋ ከሚከሰተው ግፊት በዋነኝነት የሚለየው ግፊቱ የሚገናኘው ከእንግዴ ልጁ ጋር ስለሆነ ነው። ስለዚህ ግፊቱ የሚጠፋው ልጁ ሲወለድ እና እንግዴ ልጁ ሲወጣ ብቻ ነው!

ለተከታታይ የጤና ነክ መረጃዎች
https://t.me/Doctormhomecare
1.8K views19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 16:46:11 የዴፖፕሮቨራ ጥቅም እና ጉዳት

በመርፌ መልክ የሚሰጥ የወሊድ መከላከያ ነው፡፡ ይህ የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴ በአስተማማኝነቱ እና አዋጭነቱ ይታወቃል፡፡
በየ 3 ወሩ በህክምና ባለሙያ በመርፌ ተወግቶ የሚሰጥ ነዉ፡፡

ጥቅም
ከፍተኛ ውጤታማነት ያለው ወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴ ነው
ኢስትሮጂን ሆረሞን የማይጨምር ዘዴ ነው
የደም ዑደት ችግር አያስከትልም
ከማህጸንና ከእንቁላል ማህደር ካንሰር የመከላከል ሁኔታ አለው
ጡት የምታጠባ ሴት በወተቱ መጠንና ይዞታ የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም
በየቀኑ መከታተል የሚፈልግ አይደለም
ለማስገባትም ሆነ ለማስወጣት ቀዶ ጥገና የሚፈልግ አይደለም

ጉዳት
በአማካይ ከ 6 እስከ 12 ወር ለሚያክል ጊዜ መርፌዉን አቋርጠው ለመውለድ በሚወሰንበት ጊዜ የመዘግየት ሁኔታ ያሰከትላል
የወር አበባ ቋሚ ጊዜ አለመያዝ
የጡት ካንሰር
ክብደት መቀነስ
ድብርት

ለተከታታይ የጤና ነክ መረጃዎች
https://t.me/Doctormhomecare
1.3K views13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 07:14:52 የጆሮ ኢንፌክሽን ምልክቶች

የጆሮ ኢንፌክሽን (otitis media) ማለት የመሀለኛው የጆሮ ክፍል በኢንፌክሽን ሲጠቃ ነው፡፡ ይህ ህመም ብዙውን ጊዜ ህጻናትን ያጠቃል ሆኖም ግን አዋቂወችንም ሊያጠቃ ይችላል፡፡
በአብዛኛው በባክቴሪያ ይመጣል ነገር ግን በሌሎች ተዋስያንም ሊመጣ ይችላል፡፡

የጆሮ ኢንፌክሽን (otitis media) አይነቶች
1 አጣዳፊ የጆሮ ኢንፌክሽን (acute otitis media) ማለት በ 15 ቀን ውስጥ የሚፈጠር የመሀል የጆሮ ክፍል ኢንፌክሽ ሲሆን የጆሮ የመሀለኛውን ክፍል ያጠቃል፡፡
2 የጠና የጆሮ ኢንፌክሽን (chronic otitis media) ማለት ከ 15 ቀን በላይ የቆየ የጆሮ ኢንፌክሽን ሲሆን ብዙውን ጊዜ መግል የመያዝ ነገር ይኖራል ::
3 ኢፊውዥን የጆሮ ኢንፌክሽን (otitis media with effusion) ይህ ከአጣዳፊ የጆሮ ኢንፌክሽን በሆኋ ወይም የህመሙ ምልክቶች ከጠፉ በሆኋ ፈሳሽ እዛው የመሀል የጆሮ ክፍል ሲቀር ነው፡፡

ምልክቶች ህጻናት ላይ
ማልቀስ ከወትሮ በተለየ
መነጫነጭ
እንቅልፍ ማጣት
የጆሮ ህመም
ራስ ምታት
የአንገት ህመም
ከጆሮ ፈሳሽ መውጣት
ትኩሳት
ማስመለስ
ተቅማጥ
የመስማት ችሎታ መቀነስ
የሰውነት ሚዛንን መጠበቅ አለመቻል

ምልክቶች አዋቂ ሰዎች ላይ
የጆሮ ህመም
ከጆሮ ፈሳሽ መውጣት
ለመስማት መቸገር

ምክንያቶች
አለርጂ (allergy)
ጉንፋን
የሳይነስ ኢንፌክሽን (sinus infection)
የሳንባ ምች (pneumonia)
ማጂራት ገትር (meningitis)

አጋላጭ ሁኔታዎች
ከ6 ወር እስከ 3 አመት እድሜ ክልል ውስጥ የሆኑ ህጻናት
ጡጦ መጠቀም
ለተበከለ አየር መጋለጥ
በተደጋጋሚ ለሲጋራ ጭስ መጋለጥ
ቀዝቃዛ የአየር ንብረት

መፍትሄ
ማንኛውንም ኢንፌክሽን ሲኖር ቶሎ መታከም በተለይ የመተንፈሻ
አካል ህመም ሲኖር
አጋላጭ ሁኔታዎችን መቀነስ
የህመሙ ምልክቶች ሲኖሩ ቶሎ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ፡፡

ለተከታታይ የጤና ነክ መረጃዎች
https://t.me/Doctormhomecare
1.4K views04:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-30 15:32:49 የደም አይነት እና የአመጋገብ ስርአት
**

የሰ
ው ልጅ ደም በቀይ የደም ሕዋሳት ላይ ያሉትን ንጥረ ነገሮች መሠረት በማድረግ ኤ (A) ፣ ቢ (B) ፣ ኤቢ (AB) እና ኦ (O) ተብሎ በአራት ይከፈላል፡፡ የተመገብነው ምግብ በአንጀታች ውስጥ ከተፈጨ በኋላ በደማችን አማካኝነት ወደተለያዩ የሰውነታችን ክፍሎች ይሠራጫል፡፡ በዚህም ሂደት ውስጥ ምግባችን ውስጥ ያሉ የተለያዩ ንጥረ ነገሮች ከደማችን ጋር ኬሚካላዊ ግንኙነትና ውሕድ ይፈጥራሉ፡፡ ይህንንም ተከትሎ ከደማችን ዓይነት ጋር የሚስማማ ምግብ ከተመገብን የምግብ የመላም ሂደት ሊፋጠን፣ አላስፈላጊ ክብደት ልንቀንስ፣ የላቀ ጉልበት ሊኖረን እንዲሁም የበሽታ የመከላከል ዓቅማችንም ሊዳብር ይችላል፡፡ከዚህ በመቀጠልም ከእያንዳንዱ የደም ዓይነቶች ጋር የሚጣጣሙ የምግብ ዓይነቶችን እንጠቅሳለን፡፡

1) የ ኦ (O)ደም ዓይነት የአመጋገብ ስርዓት

ይህ የደም ዓይነት ከሌሎች ቀድሞ የነበረ ጥንታዊ ሲሆን ከእንስሳት አዳኞች የተወረሰ የደም ዓይነት ነው፡፡ የዚህ ደም ባለቤቶች ዓሣ፣ የባህር ምግብ፣ ቀይ ስጋ፣ ጨው፣ ዶሮ፣ ሲኳር ድንችና የመሳሰሉትን ምግቦች እንዲያዘወትሩ ይመከራል፡፡በዚያውም ልክ እንቁላል፣ የእንስሳት ተዋጽኦዎች፣ ስንዴና ባቄላን ከገበታቸው ማራቅ አለባቸው፡፡

2) የ ኤ (A) ደም ዓይነት የአመጋገብ ስርዓት

ይህ የሰው ልጆች ወደ እርሻ ሲገቡ በተፈጠረው የአመጋገብ ለውጥ ምክንያት የተከሰተ የደም ዓይነት ነው፡፡ በዚያ ዘመንም የሰው ልጆች ለመኖነት ፊታቸውን ወደ አትክልቶች በማዞራቸው ምክንያት በጊዜ ሂደት እጅግ የዳበረ የምግብ ማላም ስርዓትን አዳበሩ፡፡ በአንጀታችው ውስጥ የሚገኙት የባክቴሪያዎች ዓይነትና ቁጥርም እጅግ ተበራከተ፡፡ የዚህ ደም ባለቤቶች ፖም፣ አቮካዶ፣ ሰላጣ፣ ካሮት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ባቄላ፣ እርጎ፣ የስንዴ ዳቦና ፓስታ እንዲመገቡ ይመከራል፡፡ ነገር ግን እንቁላል፣ ስጋ እና ሌሎች የእንስሳት ተዋጽኦዎችን በተገቢው መንገድ ለማብላላት አንጀታቸው አልዳበረም፡፡

3) የ ቢ (B) ደም ዓይነት የአመጋገብ ስርዓት

የጥንቶቹ አዳኞች ወደ ሒማሊያስ ተራሮች በመሰደድ እንስሳትንም በማላመድ የአርብቶ አደር ሕይወትን መምራት ሲጀምሩ የተፈጠረ የደም ዓይነት ነው፡፡ ቀይ ስጋ፣ ዓሣ፣ እርጎ፣ ዓይብ፣ ወተት፣ ሙዝ፣ አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶች፣ ወይንና አናናስ ተስማሚ ከሚባሉት ምግቦች መካከል ሲጠቀሱ ዶሮ፣ ስንዴ፣ ቲማቲም እንዲሁም ለውዝ እንዳይመገቡ ይመከራል፡፡

4) የ ኤቢ (AB) ደም ዓይነት የአመጋገብ ስርዓት

ኤቢ የደም ዓይነት በቅርብ ጊዜ የተከሰተ ሲሆን ከዓለም ህዝብም በአምስት ፐርሰንቱ ውስጥ ብቻ ይገኛል፡፡ የዚህ ደም ባለቤቶች ስጋንና ሌሎች የእንስሳት ተዋጽኦዎችን መፍጨት ቢችሉም የጨጓራቸው አሲድ መጠን ዝቅተኛ በመሆኑ ምክንያት የተመገቡት ምግብ በስብ መልክ ይከማቻል፡፡ ፍራፍሬዎችና አረንጓዴ አትክልቶች፣ ሀብሀብ እና ወይን፣ እንደ ቱና እና ሰርዲን ያሉ የባህር ምግቦችን ማዘውተር ተገቢ ሲሆን ከበቆሎ፣ የበሬና አሳማ ስጋ እነዲሁም ከአልኮሆልና ቡና መራቅ ያስፈልጋቸዋል፡፡

(የወዳጅዎን የደም አይት ያውቃሉ? እንግዲያውስ ሼር ያድርጉት)

@Doctormhomecare
2.0K viewsedited  12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ