Get Mystery Box with random crypto!

የወጣቶች ሕይወት (ሕይወተ ወራዙት) በቀሲስ ሕብረት የሺጥላ #ክፍል_1 ሕልመ ሌሊት ምንድነው ? | አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር

የወጣቶች ሕይወት (ሕይወተ ወራዙት)

በቀሲስ ሕብረት የሺጥላ
#ክፍል_1


ሕልመ ሌሊት ምንድነው ?

በዐፍላ የጉልምስና ወቅት አባለ ዘርዕ ወደ ሙሉ የዕድገት ደረጃ መድረስ ብቻ ሳይሆን መስራትም ይጀምራል ። በዚህ ጊዜ ከኀፍረተ አካል ዘርዐ ብእሲ (የወንድ ዘር ) ይወጣል ። ወንድና ሴት ግንኙነት በሚያደርጉበት ጊዜ ወደ ሴቲቱ ማኀፀን በመግባት ፅንስ እንዲፈጠር የሚያደርገው ይህ ፈሳሽ ንጥረ ነገር ነው ። ለዘር የበቁ ወጣቶች ዘር የሚወጣቸው በተለያየ መንገድ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ግን ተኝተው ሳለ በጠለቀ እንቅልፍ ሆነው ሕልም በሚያልሙበት ወቅት ነው ። ይህ ሲሆን በሳይንስ እንደ ጤናማ የተፈጥሮ ሂደት ይቆጠራል ። የዚህ አይነቱን ሕልም መፅሐፈ መነኮሳት በአንድ ስፍራ #ሕልመ_ጽምረት በሌላ ቦታ ደግሞ #መስቆርርተ_ሕልም ሲለው ይገኛል። ሕልሙን ያየው ሰው ደግሞ #ዝንየት መታኝ ወይም #ሕልመ_ሌሊት አገኘኝ ይላል

ሕልመ ሌሊት ኃጢአት ነውን ?

በጠለቀ እንቅልፍ ላይ ሳሉ የሚከሰት ሕልመ ሌሊትን እንደ ኀጢአት እንዲቆጠርና እንዳይቆጠር የሚያደርጉ የተለያዩ ሁኔታዎች አሉ ።ስለዚህ ሕልመ ለሊትን በጥቅሉ ኃጢአት ነው ወይም አይደለም ማለት አይቻልም ። እንደ ኃጢአት እንዲቆጠር የሚያደርጉ ሁኔታዎችን በጥቂቱ ለማየት ያህል

ሀ. አጋንንት የሰው ልጆችን በልዩ ልዩ መንገድ ክፋኛ ይዋጓቸዋል ። የሰው ልጆች ሲያንቀላፉ አጋንንት ግን ለቅጽበት እንኳን አያሸልቡም ። ያንቀላፋው ሰው እስኪነቃ ድረስ እንኳን አይጠብቁም ። አጋንንት የሰውን ልጅ በተኛበት ክፋ ክፋ ሕልም በማሳየት ይፈትኑታል ። አንድ ጊዜ የተራቆተ የሴት ገላ ፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ወንድና ሴት ግንኙነት ሲያደርጉ በምትሐት ያሳዩታል። በዚህ ጊዜ እርሱም በዝሙት ሐሳብ ይሳብና በሕልሙ ዝሙት ሲፈፅም ያድራል ። መፅሐፈ መነኮሳት "ሰይጣናት የሰውን ልጅ ቀን ቀን ክፋ ሐሳብ በማሳሰብና በማሰራት በሌሊት ደግሞ ዝሙት የሞላበት አስጸያፊ ሕልም በማሳየት ይዋጉታል " ይላል። በዚህ ጊዜ ሰይጣናት ያቀረቡለትን ረቂቅ ፈተና ከመቃወም ፣ ከመፀፀትና ከመቆጨት ይልቅ ደስ እያለው የሚያጣጥም ከሆነ ፤ በደስታ ስለ ዝሙት የሚያሰላስል ፣ የሚዳራ ፣ የሚዛለል ፣ ወደ ዝሙት ከሚያመሩ ማናቸውም ነገሮች የማይሸሽ ሰው እነዚህን ነገሮች ነቅቶ ሳለ ያልተቃወማቸውን ተግባራት በሕልሙ በፈፀማቸው ጊዜ በተግባር እንደ ፈፀማቸው ይቆጠራል ።ሌላው ከሥራ ብዛት ሕልም እንዲታይ ጠቢቡ ሰሎሞን[ " ሕልም በሥራ ብዛት ይታያል " በማለት የተናገረው ያስረዳል (መክ5:3) እንደዚሁም ሁሉ ከምኞት ብዛትም ሕልም ሊከሰት ይችላል። ክፋ ምኞት በሕልምም ማርከሱ አይቀርም ። ሐዋርያው ይሁዳ " እያለሙ ሥጋቸውን ያረክሳሉ " ያለው ለዚህ ይጠቀሳል ። (ይሁዳ 1:8) እንደሚታወቀው ነፍስ አትተኛም ። ስለዚህ ነፍስ በእንቅልፍ ልቤ ነው ብላ ማመካኘት አትችልም ። ነፍስ በረከሰ ሕልም ምክንያት ከተጠያቂነት ነጻ መሆን የምትችለው ሥጋ ከእንቅልፍ ውጭ በሚሆንበት ጊዜ ተግባረ ዝሙትን በመቃወምና በመጥላት ከእግዚአብሔር ጋር መሆኗን ስታስመሰክር ብቻ ነው ። ሌላው ሕልመ ለሊትን እንደ ኀጢአት የሚያስቆጥረው ሁኔታ አብዝቶ መመገብ ነው ። ጾም ለፅድቅ ስራ ሁሉ መሰረት እንደሆነው እንደዚሁም አብዝቶ መመገብ የኀጢአት ሁሉ መሰረት ነው ። "እህል ጉልበትን ያጠነክራል ተብሏልና ።ሰው ሁሉ ለቁመተ ስጋ ያህል ብቻ መመገብ ያሻዋል ። ከዛ ውጭ ግን አብዝቶ መመገብ "ሆዳቸው አምላካቸው " እንደ ተባለው ለህልመ ለሊት ያጋልጠናል ።
... ይቀጥላል ...

@dnhayilemikaelb
@dnhayilemikael
@dnhayilemikael