Get Mystery Box with random crypto!

ሕይወተ ወራዙት / የወጣቶች ሕይወት (በቀሲስ ሕብረት የሺጥላ) መግቢያ ወጣቶችና ፆሮቻቸው (የ | አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር

ሕይወተ ወራዙት / የወጣቶች ሕይወት
(በቀሲስ ሕብረት የሺጥላ)

መግቢያ

ወጣቶችና ፆሮቻቸው (የወጣቶች ፈተና
በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አስተምህሮ መሰረት ምእመናን በ#5 መደብ ይመደባሉ ። ይህም መደብ "ፆታ ምዕመናን "ይባላል ። 5ቱ ፆታ ምዕመናን የሚባሉት ካህናት ፣ መነኮሳት ፣ አዕሩግ (አረጋውያን) ፣ ወራዙት (ወጣት ወንዶች ) እና አንስት (ሴት ወጣቶች) ናቸው ። አምስቱም ፆታ ምእመናን በየራሳቸው የሚቸገሩበት ዓቢይ ፈተና አለ

"ፆር " በመባል የሚታወቀው ይህ ዓቢይ ፈተና ነው ።የካህናት ፆራቸው ትዝህርት (ትዕቢት) ነው ፤ የመነኮሳት ፆር ስስት ሲሆን ፤ የአረጋውያን ፆራቸው ደግሞ ፍቅረ ንዋይ ነው ። ቀሪዎቹ ወጣት ወንዶች ሲሆኑ ዐቢይ ፆራቸው ዝሙት ነው ። የወጣት ሴቶች ዓቢይ ፆር ደግሞ ትውዝፍት (የምንዝር ጌጥን መውደድ ) ነው ። ይህ ማለት ግን ዋና ዋና ፈተናቸውን አንጓሎ ለመናገር ነው እንጂ እያንዳንዱ ፆታ ምዕመን የሚፈተነው በአንድ ነገር ብቻ ነው ማለት አይደለም ።" ሰውነቱ በደዌ የተጠቃን ሰው ጉንፋን እንኳን እንደሚያይልበት " እንዲሁ በዋና ፈተናው ድል የተደረገ ምዕመን ሌሎች ጥቃቅን ፈተናዎች ይረባረቡበታል

ነገር ግን ዋናውን ፆሩን ድል ካደረገ የሚመጡበትን ሌሎች ፈተናዎች በቀላሉ ድል ለማድረግ ይቻለዋል ። ወጣቶች ልዩ ልዩ ፆር (ፈተና) እንዳለባቸው ነገር ግን ዕድሜያቸው እየገፋ በመጣ ቁጥር ወጣትነታቸው ሲያልፍ የወጣትነት ፈተናቸውን አብሮ እንደሚያልፍ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ሲል ተናግሯል ። "ሥጋን ንዳድ ሌላም ልዩ ልዩ ደዌ በያዘው ጊዜ ምንም ብርቱ ቢሆን እንደሚደክምና ከበሽታው በዳነ ጊዜ ግን ኃይሉ እንደሚመለስለት እንደዚሁ ነፍስም በወጣትነት ወራት በደዌ ኀጢአት ትያዛለች

ትዕቢተኛነት ፣ ሥጋዬ ይድላው ማለት ፣ በፆታ መፈላለግና ይህን የመሳሰለ ብዙ የምኞት ጣዕም ያድርበታል ። የእርጅና ወራት በደረሰ ጊዜ ግን ፈቃደ ሥጋ ፈፅሞ ከሰውነት ይርቃል " ብሏል ። ስለዚህ ወጣትነታችንን በጥበብ እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ ሁኔታ ልናሳልፍ ይገባል ። የዚህ ፅሁፍ አላማም ፈተናዎቹን አውቀን እንዴት ማለፍ እንዳለብን መንገድ ማመላከት ነው ።

... ይቀጥላል ...

https://t.me/dnhayilemikael
https://t.me/dnhayilemikael
https://t.me/dnhayilemikael