Get Mystery Box with random crypto!

#ድንግል_ሆይ_የአንቺ_ሥጋ_ይገርመኛል!! #ድንግል_ሆይ የአንቺ ሥጋ ይገርመኛል ከሔዋን ተገኝቶ ከ | ⛪️🇪🇹@የራማው ልዑል🇪🇹 ⛪️

#ድንግል_ሆይ_የአንቺ_ሥጋ_ይገርመኛል!!

#ድንግል_ሆይ የአንቺ ሥጋ ይገርመኛል ከሔዋን ተገኝቶ ከመላእክት ይልቅ ንፁህ ሆኗአልና፣ አፈር ነህ ከተባለው ከአዳም ተወልደሽ በሰማይ በአባቱ ቀኝ በተቀመጠው ንጉሥ በክርስቶስ ክቡር ሰውነት ላይ በተለየ ክብር ሆኖ በሰማያት ታይቷልና። ባለ ራዕይው ዮሐንስ ከአንቺ በነሳው ሥጋ  ከተወጋው ቁስለቱ ጋር ወደ ሰማይ እንደወጣ  ቢያየው እንዲሁ ይመጣል ብሎ በመፅሐፍ ነገረን። የወጉትም ሁሉ ያዩታል ተብሎ ተፃፈ። የታናሿ የአንቺ ገላ ሰማይ ለሚጠበው አምላክ ልብስ ሆነ። መሰወሪያው ከዚህ ነው የማይባለው ልዑል ሥጋሽን ለብሷልና ሥጋ ሆነ ተባለለት። ከባሕሪው እሳት የሆነውን እርሱን ሁሉ ዳሰሰው ሁሉ አቀፈው። መለኮታዊ ክብሩን በአንቺ ሥጋ ውስጥ ቢሰውረው የወደቀው ሰውም አምላክ ሆነ ተባለ፤ ይደንቃል።

#ደንግል_ሆይ መላእክት በቤተልሔም በአንቺ ላይ የሆነውን ቢመለከቱ ስብሐት ለእግዚአብሔር አሉ። ሌላ ምን ይባላል? የማይወርደው ከከፍታው ወርዶ ሲታይ በአድናቆት ስብሐት ነው እንጂ። ሰማይ ከክብሩ የተነሳ የምትጠበውን በአንቺ ክንድ ላይ ሲያዩት ምን ይበሉ? ኦ ማርያም በአንቺ የሆነውን ለመፃፍ የሚያስብ ቃለ ፀሐፊ ከፍቅሩ የተነሳ ብዕሩ በእንባ ስለሚርስ ስለ አንቺ እንዲህ ነው ለማለት ቃልና እቅም በማጣት ሠአሊ ለነ ብሎ ጽሑፉን  ይዘጋዋል፤ አይችልምና።

#ልዑሉን_የወለድሽ_ልዕልት_ሆይ የአንቺ ሥጋ ከአቤል ይልቅ ተወደደ፤ ከደገኛው አብርሐም ይልቅ ከፍ አለ፤ ከንጉሱ ከዳዊት ይልቅ ሥጋሽ የተለየና የተመረጠ ሆነ ...ዳዊትም፦ ንጉስ ደም ግባትሽን ወደደ ብሎ ፃፈልሽ። ከእስራኤላውያን አባት ከያዕቆብ ድንኳን ይልቅ  የአንቺ ሥጋ ተመረጠ። ሎጥ፦ መላእክትን  ወደ ቤቴ ግቡ ቢላቸው በአደባባይህ እንሆናለን እንጂ አንገባም አሉት። ድንግል ሆይ የአንቺ ሥጋ ግን መላእክትን ለፈጠረ ጌታ ማደሪያ ሆነ።  ለዚህ ቃል የለም ዝምታና  አንክሮ እንጂ..

#ድንግል_ሆይ የአንቺን ሥጋ በመቃብር የለም በአብ ቀኝ እንጂ። አንዳንዶች ተነስታለች ለማለት ከበዳቸው። ለመሆኑ ልጅሽ አልዓዛርን ከመቃብር ያስነሳ መሆኑን አላነበቡ ይሆንን? የኢያዒሮስ ልጅን ታሪክ አልተመለከቱ ይሆን አንቺ ግን ወደ ሰማያት ከተነጠቁት ከሄኖክና ከኤልያስ ትበልጫለሽ። ትንሣኤሽን የሚያምን ሁሉ አሜን ይበል።

ምልጃሽ ኢትዮጵያን ይታደግ፤ ለዓለም ምህረት ይሁን!!!

መልካም ዕለት

            #ዲ ን እሱባለው (ሥሙር)


የራማው ልዑል  ሚዲያ የሁሉም ለሁሉም!
ቤተሰብ ይሁኑ በቴሌግራም ቻናላችን
Join https://t.me/+VgSv2n8UfePFOYVr
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924