Get Mystery Box with random crypto!

#ትንሳኤሽ_ሳይሆን_ሞትሽ_ይደንቀናል! 'የህይወት እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትንሳኤሽ ሳይሆን ሞት | ⛪️🇪🇹@የራማው ልዑል🇪🇹 ⛪️

#ትንሳኤሽ_ሳይሆን_ሞትሽ_ይደንቀናል!

"የህይወት እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትንሳኤሽ ሳይሆን ሞትሽ ይደንቀኛል፤ እርገትሽ ሳይሆን ወደ መቃብር መውረድሽ ይገርመኛል። የብርሃን እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትወጂኛለሽን? ብየ አልጠይቅሽም! ፍቅርን የወለድሽ አንቺ ለዓለሙ ሁሉ ፍቅርሽ የበዛ ነውና፤ አትናፍቂኝምን? ብየም አልጠይቅሽም! ዘወትር እኔን ለመጠበቅ ከጎኔ እንደማትለይ አውቃለሁኝና።

#እመቤቴ_ሆይ እንደ ቶማስ አይሽ ዘንድ በእጅጉ እጓጓለሁ የቶማስ ንፅህናና ቅድስና ግን የለኝም፤ እንደ ዮሐንስ ከጎንሽ ልሆን እጓጓለሁ፤ የዮሐንስ ፀጋ ግን የለኝም!

#እናቴ_ሆይ እንደ ኤልሳዕ የልቦናዬ ዓይን በርቶ ሰማያዊ ክብርሽን ላይ አልተቻለኝምና፤ አዝናለሁ! ኤልሳዕ በፀሎት ኃይል የግያዝን ዓይን እንዳበራ፤ አንቺም ዓይኔን ታበሪልኝ ዘንድ ኃይልሽን በእኔ ላይ አበርቺ፡፡

#ድንግል_ሆይ ይህን የምል የእምነት ማረጋገጫ ፈልጌ አይደለም፤ በልጅሽ መሠረትነት የታነፅኩኝ፤ በልጅሽ ስምም የተጠመቅኩኝ ነኝና፤ ነገር ግን ስለምትናፍቂኝ ይህን አልኩኝ። ስለዚህም ነይ ነይ እምየ ማርያም እያልኩኝ እንደ እናቶቼም እለምንሻለሁ፡፡ የብርሃን ልብስሽን ለብሰሽ ነይ!! የክብር አክሊልሽን ደፍተሽ ነይ አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ነይ እናይሽ ዘንድ ነይ፡፡"

“የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።” 2ኛ ቆሮ 13፥14


መልካም ምሽት

            #ዲ ን እሱባለው (ሥሙር)


የራማው ልዑል  ሚዲያ የሁሉም ለሁሉም!
ቤተሰብ ይሁኑ በቴሌግራም ቻናላችን
Join https://t.me/+VgSv2n8UfePFOYVr
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924