Get Mystery Box with random crypto!

ጅማ አምባሳደሯን ተነጠቀች የ2009 የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ አድማቂ የነበረው ጅማ አባ ቡና ወደ | @አባ ቡና ነው 🎤🎤 @ABA BUNA NEW

ጅማ አምባሳደሯን ተነጠቀች

የ2009 የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ አድማቂ የነበረው ጅማ አባ ቡና ወደ አንደኛ ሊግ ወርዷል።

ይህ ክለብ ለጅማና አካባቢዋ ህዝብ ከክለብም በላይ ነበር። በስሟ ላላደረችው ጅማ የብርሀን ጮራ ያፈነጠቀላት: ከምንም በላይ አበቃለት: አከተመ ለተባለው ለጅማ እግር ኳስና እግር ኳሰኛ አዲስ ብስራትን ያበሰረ ነበር። ጅማ ከ21 ወረዳዎች በላይ ያላት የተፈጥሮ ሀብትም ሆነ የህዝብ ብዛት ችግር የሌለባት ዞን ናት። እኔ ተወልጄ ባደኩበት ወረዳንኳ (ሊሙ ኮሳ) 44 ቀበሌዎችና 3 ከተማ መስተዳድሮች አሉ። ክለቡ የ2009 የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ተሳታፊ መሆኑን ካረጋገጠ ግዜ ጀምሮ የእያንዳንዱ ቀበሌና ከተማ መስተዳድር ታዳጊዎች ነገን ተስፋ ሰንቀው ባለማቋረጥ እየሰሩ ያሉትን ብዛት ቤት ይቁጠረው። የ21ንዱን ወረዳና የተቀሩትን ከተማ መስተዳድር ታዳጊዎችን ከላይ ባስቀመጥኩላችሁ የ1 ወረዳ ቀበሌዎችና ከተማ መስተዳድሮች ብዛት አስሉት። ዛሬ የእነዚህ የ100 ሺህዎች ህልም በግማሽ ወደ ቅዠት ተቀይሯል። በሚሊየን የሚቆጠር የክለቡ ገንዘብ በግለሰቦች ተዘርፏል። ከገብረመድህን ሀይሌ ውጭ የመጣው አሰልጣኝ ሁሉ የጅማ ክለቦችን እንዳልነበሩ አድርገዋቸው የራሳቸውን ጥቅም ግን አስከብረው ወጥተዋል። የዞኑም ሆነ የከተማው መስተዳድር አመራሮች እግር ኳሱን ገድለውታል። ዛሬ ጅማ አባ ቡናን ገንዘውታል ነገ ጅማ አባ ጅፋርን ይገድሉትና ግብዓተ መሬቱን ይፈፅማሉ።
አለቀ የጅማ እግር ኳስ እንደ ታሪክ ሊወሳ የወራት ዕድሜ ብቻ ቀርተውታል።
ቀድመን ጮህን: ሰው እስኪሰለቸን ፃፍን ምንም የለም ድካም ብቻ
ክለቡን ለመታደግ የደከማችሁ ተጨዋቾችና የክለቡ ደጋፊዎች መፅናናትን ይስጣችሁ
ክለቡ እንዲወርድና ግብዓተ መሬቱ እንዲፈፀም ቀን ከሌት የተጋችሁ አመራሮች ታሪክ የማይሽረው አሻራ አሳርፋችሁዋልና እኔም ስማችሁን ከምግባራችሁ እያጣቀስኩ ለትውልድ የማስተላለፍበትን መፅሐፍ በቅርቡ አስመርቃለሁ።

ምንጭ ዞላ ኤፍቢ

@Deposta
@Deposta
@ABBuna2005