Get Mystery Box with random crypto!

ነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) ሰውባን (ረዲያለሁ ዐንሁ) የተባለ ባልደረባቸውን «ያሰውባን ገጽታህን የቀየረው | ቢስሚከ ነሕያ✿⁠ ⁠♡

ነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) ሰውባን (ረዲያለሁ ዐንሁ) የተባለ ባልደረባቸውን «ያሰውባን ገጽታህን የቀየረው ምንድን ነው ?» በማለት በጠየቁት ጊዜ «በሽታም ሆነ የስቃይ ስሜት አጋጥሞኝ ሳይሆን እርሰዎን ባላየሁ ጊዜ እስከማገኝዎት ድረስ ውስጤ በጥልቅ ሀዘን ስለሚናጥ ነው» በማለት መለሰላቸው።

በዱንያ ውስጥ በነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) እና በሰዉ ልጆች መካከል ከተዘረጉት የግንኙነት መስመሮች አንድ መስመር ብቻ ሲቀር ከነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) ህልፈት በኋላ አላህ ሁሉንም መስመሮች አቋርጧቸዋል። የተረፈው የግንኙነት መስመር በነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) ላይ «የአክብሮት እዝነት እና ሰላምታ» ማውረድ ብቻ ነው። ስለዚህ በነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) ላይ የአክብሮት እዝነት እና ሰላምታህን መልዓክት እንዲያደርሱልህ ካሻህ ይኸው አሁን መፈጸም ትችላለህ

اللهم صّلِ وسَلّمْ عَلۓِ نَبِيْنَا مُحَمد ﷺ
اللَّهُــــــــمّے صَــــــل على مُحمَّــــــــدْ ¸ و علَےَ آل محمد كما صَــــــلٌيت علَےَابراهيم ¸ و علَےَ آل إِبْرَاهِيمَ ¸ و بارك علَےَ مُحمَّــــــــدْ و علَےَ آل مُحمَّــــــــدْ كما باركت علَےَ إِبْرَاهِيمَ و علَےَ آل ابراهيم فى الْعَالَمِينَ انَّك حَمِيدٌ مَجِيدٌ