2021-11-27 14:05:07
loading……
እነዚህን መጻህፍት ያነበባችሁ ለሌሎች አስነብቡ:: ከልሱትም!
ያላነበባችሁ አራቱንም ቅጾች አንብቡዋቸው...
ማንበብ የማትፈልጉና የማትወዱ ካላችሁ ደግሞ የመጽሃፍቱን ከቨሮች ልብ ብላችሁ ተመልከቱዋቸው...
ከ 7 እና ከ 8 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ የ G 20 እና የ G 8 አገራት ዋና አጀንዳ ትሆናለች ብሎ ማን አስቦ ነበር? ማንም!
በኢትዮጵያ ምድር ለውጡም ነውጡም እንደሚመጣ, ሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የትርምስ ቀጠና እንደሚሆን,ሲቪል ዋር እንደሚከሰት, ኅያል አገራትና ዓለም አቀፍ ተቁዋማት "ረጅም" "አራጅም" ሆነው ጣልቃ እየገቡ እንደሚፈተፍቱ,አገሪቱም የሃያል አገራት ዋና አጀንዳ እንደምትሆን ከመሆኑ በፊት "ይሆናል" ተብሎ የተገለጸበትን መጽሃፍት ነው ስንጋብዛችሁ የቆየነው:: ምክንያቱም አንባቢው ይመንም አይመንም እውነታው የግድ መገለጽ ስለነበረበት ነው::በዚያ ምንም ፍንጭ ባልነበረበት ወቅት እንዲህ ያሉትን እውነታዎች ይሆናሉ ብሎ መግለጽ እብድ ያሰኝ የነበረ ቢሆንም ጸሃፊው ግን በድፍረት ጽፎታል::
"....ምናልባት ወደፊት የምዕራባውያኑ ዕቅድ ወደተግባር ሲለወጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ማመኑ አይውቀርምና ይጻፍ.." ባይ ነበርና ጽፎታል...::
እውነታው ይታመንም አይታመንም ይተግበርም አይተግበርም የግድ ነውና ዕቅድና ፍላጎታቸው ምን እንደሆነ ቀድሞ መገለጽ ነበረበት!እናም ተገልጾዋል!
ስለዚህ እየሆነ ያለው ነገር ብቻ ሳይሆን ገና ያልሆነውም ይሆናል ተብሎ ተግልጾዋልና አንዳንድ አስፈሪ እውነታዎችን ቀድሞ ማወቅ መልካም ነው::
የችግሮች መፍትሄ የችግሩን ምንጭ ከማወቅ ይመነጫልና አንዳንድ "ኢትዮጵያ ነክ" ነገሮችንና ሰቆቃዎችን ቀድማችሁ እወቁዋቸው ተዋወቁዋቸው ለማለት ነው...::
በ 1 ሺ ገጾች (በ አራቱም ቅጾች) ውስጥ የሰፈሩትን እውነታዎች በተግባር እየሆነ ካለው ነገር ጋር እያመሳከራችሁ በማረጋገጥ ወደ ዋናው መፍትሄ አማትሩ ለማለት ነው...::
ሰላም ለኢትዮጵያ::
https://youtube.com/channel/UCpNPc78FhPGSXhAVVh_jQuA
1.9K views11:05