Get Mystery Box with random crypto!

ሃፍረተ ቢሱ የአብይ መንግስት.... አገርና ህዝብ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በውል ሳትገነዘብ | Daniel Tomas ኢትዮጵያዊ

ሃፍረተ ቢሱ የአብይ መንግስት....
አገርና ህዝብ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በውል ሳትገነዘብ ገና በጮርቃ እእምሮህ የበትረ-መንግስት ስልጣን ስትይዝ.... የማይመጥንህን የመሪነት ስልጣን ድንገት ስትጨብጥ....ስራህ ሁሉ እንደ አብይ አህመድ የተልፈጨፈጨ ሆኖ ይገኛል:: ህዝቡ ሁሉ እንዳንተ ደደብ ይመስልህና ነውሩን ጌጥ አድርገህ ትደሰኩረዋለህ! የተዋጣልህ ሃፍረተቢስ መንግስት ትሆናለህ! የያዝከው ድንገተኛ ስልጣን ትርጉሙ ይጠፋባሃል!
ዜጋ ማለት አንተና በዙሪያህ ያሉት አጫፋሪዎችህ ብቻ እንጂ ሌላው ማህበረሰብ ስለ አገሩ የማይመለከተውና የማያገባው ይልቁንም ላንተ ወንበር ሲባል በየተራ ሊማገድ የተከመረ የማገዶ እንጨት አድርገህ ትቆጥራለህ!
አብይ አህመድ የተዋጣለት የዓለማችን ሃፍረተ ቢስ መሪ ነው! የሚመራትን አገር ሊያፈርስ የሚመራውን ህዝብ ሊጨርስ የተነሳ ሃፍረተ ቢስ መሪ!
እና... እንደ አብይ አህመድ ሃፍረተ ቢስ መሪ ስትሆን በኤርትራ መደበኛ ጦር, በአማራ ልዩ ሃይል ሚሊሻና ፋኖ እንዲሁም በአፋር ልዩ ሃይልና ሚሊሻ በድሮን በዘመናዊ የጦር ጀቶችና በሚሊዮን ጦር ስራዊቶች ታግዞ አንድን ክልል የተዋጋና ምንም አይነት ድል ማግኘት ያልቻለውን ይልቁንም (በአፍሪካ ኢንሳይደር ዘገባ መሰረት) 450 ሺ መደበኛ ጦር ሰራዊት ያስፈጀውን አስፈጅቶም ድል ማድረግ የተሳነውን ከንቱ ጄ/ልን በታሪክህ የማታውቀውንና ሲባል የሰማህውን የአውሮፓ ማዕረግ አምጥተህ ማርሻል ብለህ ትሾማለህ! ትርጉሙን የማታውቀውን ማዕረግ አንስተህ ለወንበርህ ጠባቂ ትለድፍለታለህ!
ማርሻል ማለት ምን ማለት ነው? ቢባሉ ሰጪውም ተቀባዩም መልስ የላቸውም!ይህን ለማወቅ በጥቂቱም ቢሆን ስለጉዳዩ ሪፈር ማድረግ ያስፈልጋል:: ይህንን ደግሞ ሰጪውም ተቀባዩም ሊያደርጉት አይችሉም::ምክንያቱም ይህን ማድረግ ቢችሉ እንደ ተራ ነገር አይለዳደፉትም ነበራ!
እንደ አብይ አህመድ ሃፍረተ ቢስ መሪ ስትሆን.... ደሃውን ማህበረሰብ ለመከላከያ ዱቄት አዋጣ እያልክ እያስገደድክ አንተ ግን ምንም ያልሆነውን መስሪያ ቤት በ1.5 ቢሊዮን ብር ታድሳለህ!
አገር ወደ ማትወጣው አዘቅት እየገባች እያየህ ፓርክ ሰርቸ ሳይክል ካልነዳሁ ትላለህ! የአገሪቱን ምትክ የለሽ መሰረተ ልማቶች ሆነ ብለህ እያወደምክ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን እያፈናቀልክ በ3 ቢሊዮን ብር አደባባይ ታድሳለህ! ዜጎች በረሃብ እያለቁ ደማቸው እንደጎርፍ እየፈሰሰ ምንም ያልሆነውን ነገር በቢሊዮኖች ወጪ እያደስክ የኔ ነው ለማለት ትውተረተራለህ!
እንደ አብይ አህመድ ሃፍረተ ቢስ መሪ ስትሆን... የራስህን አገር እየተቀበቀልክ ጮቤ ትረግጣለህ! "መቀሌን በሻሻ አድርገናታልና ምንም የሚያጉዋጉዋን ነገር የለም!" እያልክ ትፎትታልህ!
እንደ አብይ አህመድ ሃፍረተ ቢስ መሪ ስትሆን በሻሻን እንደ መቀሌ በማሳደግ ፋንታ መቀሌን እንደበሻሻ ትንሽ ከተማ ለማድረግ ትመኛለህ!
እንደ አብይ አህመድ ሃፍረተ ቢስ መሪ ስትሆን..."እነሱ የተደፈሩባቸው ሴቶች ናቸው! የእኛ ወታደሮች ግን በሳንጃ ተደፍረዋል!" እያልክ በንዴት ጠረጴዛ ትደቃለህ!
የወታደር ስራ በሳንጃ መደርፈ የዜጎች መብት ሳይደፈሩ በሰላም መኖር መሆኑን አታውቅማ!
እንደ አብይ አህመድ ሃፍረተቢስ መሪ ስትሆን.......! ወደፊት የሚያደርጋቸውን ብዙ አስቀያሚ ነገሮች ታደርጋለህ!
እንደ አብይ አህመድ ሃፍረተ ቢስ መሪ ስትሆን.... በሚሊዮኖች ደም...እየተንቦጫረክ መንግስታዊ እቃ እቃ ትጫወታለህ!