Get Mystery Box with random crypto!

የእልቂትና የብጥብጥ ቁማሩ ግሎባሊ እንጂ ሎካሊ እየተቆመረ ያለ አይደለም የሚለውን ነጥብ ለማስረዳት | Daniel Tomas ኢትዮጵያዊ

የእልቂትና የብጥብጥ ቁማሩ ግሎባሊ እንጂ ሎካሊ እየተቆመረ ያለ አይደለም የሚለውን ነጥብ ለማስረዳት ብዙ ተደከመ:: ሰሚ ግን የለም! የእነ ሄርማን ኮኸን እና የ ሲ አ ይኤ እንዲሁም የክሪሚሊን ቤተመንግስት ዕቅድና ፍላጎት እጅግ ውስብስብና ነግሮ ለማሳመን የሚከብድ ነው:: የብልጽግናን መንግስታዊ ተልዕኮም እንዲሁ!
በኢትዮጵያ ምድር ምን አቅደው ምን እየሰሩ እንዳለ ለኢትዮጵያ ህዝብ ማስረዳት በተለይም ለትግራይና ለአማራ ህዝብ ነግሮ ለማሳመን መሞከር እጅግ ከባድና ተስፋ አስቆራጭ ልፋት ነው:: ነገር ግን እውነታው ያ ብቻ ነው!
ለምሳሌ... በዛሬው ዕለት የአሜሪካው USAID ለኦሮሚያ ክልል 10.2 ቢሊዮን ብር (210 ሚሊዮን ዶላር) ለክልሉ ልማት በሚል መጠነ ሰፊ የገንዘብ ድጋፍ አድርጎዋል::
ይህንና ሌሎች አካሄዶችን አይተህ በትግራይና በአማራ ህዝብ ላይ እንዲሁም በሁለቱ ክልሎች ላይ ምን እየተሰራና ምን እየተሴረ እንዳለ መገንዘብ ካልቻልክ.... ሰሜኑን ክፍል የትርምስ ቀጠና አድርጎ ማስቀጠል ያስፈለገበትን ትክክለኛ ምክንያት ካልተገነዘብክ...ማን ምን ሊረዳህ ምን ሊያስረዳህ ይችላል?
ጉዳዩ ሌላ ነው::መዳረሻውም ሩቅ እና አስከፊ ነው:: የትግራይና የአማራ ህዝብ ልዩነቱን ወደ ጎን አድርጎ ወይም ለነገ አቆይቶ ሰከን ብሎ ማሰብና በጋራ መቆም የሚቻልበትን ሁኔታ መፍጠር ካልቻለ እኩል በጋራ ለማለቅና እኩል ተሽመድምዶ ለመቅረት የሌሎች መጠቀሚያና መጫወቻ ህዝብ ሆኖ ለመጥፋት የጋራ ውሳኔ እንዳሳለፈ ይቆጠራል!! ይህ አድማጭ አልባ እውነት ነው:: ባይደመጥም ይመዝገብ!