Get Mystery Box with random crypto!

ጅኒ! 'እኔ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚ/ ር ለመሆን ምን ያንሰኛል? ከፈለኩ እኮ የ.ተ.መ.ድ. ዳያሬክተ | Daniel Tomas ኢትዮጵያዊ

ጅኒ!
"እኔ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚ/ ር ለመሆን ምን ያንሰኛል? ከፈለኩ እኮ የ.ተ.መ.ድ. ዳያሬክተር መሆን እችላለሁ" አብይ አህመድ::
"ዋ! ኣታ እብድ ኩታራ!ጂኒ አለብህ!" ስብሃት ነጋ::
አቶ ስብሃት ነጋ አብይ አህመድን "ጂኒ አለብህ" ያሉት አንዳች ክፉ መንፈስ የሰፈረብህ ነህ ለማለት ፈልገው ነው:: በሚገርም ሁኔታ እራሱ ጂኒ መሆኑን አላወቁም::የሚያውቁበት መንገድም አልነበረም::
አብይ አህመድ በህወሃት መራሹ ኢህአዴግ ጊዜ ተራ ጫማ ላሽ ካድሬና አሽከር ነበር::ቀስ እያለ በማስመሰል ጥብቡ ሚንስትር ለመሆን ቻለ:: የኢህአዴግ ሚ/ር ሆኖ ግን ማታ ቤቱ ገብቶ የህወሃት ተቃዋሚ ሚዲያ የነበረውን ኢሳትን ነበር የሚከታተለው::ምክንያቱም ሌባ ነዋ! አስመሳይ ነው! ቀን ቀን ያስመስላል::ማታ ማታ ኢሳትን እያዬ ይከየፋል:: ከዚያ ስልጣን ከያዘ በሁዋላ አሜሪካ ሄዶ "እንደ ሲሳይ አጌና ያለ ብልህ እና አስተዋይ ጋዜጠኛ...." ብሎ ተናገረና አስጨበጨበ!
ታማኝ በየነን ደግሞ "ብደውልልህ አታነሳም...ጎንደሬ መሆንህን አውቃለሁ... በሉልኝ" አለና በማስመሰል ጥበቡ ታማኝንም ሲሳይ አጌናንም መላውን ባሪያና ዲያስፖራም አሳምኖ አንበረከከ:: አንድ አንድ ዶላርም ተቀበላቸው እጂ!
አብይ አህመድ ፍልስፍናው ይህ ነው::
እራሱ በጻፈው መሰረት "ጠላቶችህን የዋህ ሆነህ ትቀርብና በፍቅር ወደራስህ ካስጠጋሃቸው በሁዋላ ክንፋቸውን ትነቃቅለዋለህ!" የሚል ነው::
ስለ አመራር ጥበብ በጻፈው መጽሃፉ እንደገለጸው እሱኑ ተግባራዊ አድርጎ ብዙዎችን በማስመሰል አንበረከከ ክንፋቸውንም ነቃቀለ::ከታማኝ እስከ ሲሳይ አጌና ከእገሌ እስከ እገሌ... ተኮድኩደው ቀሩ! ሰዎቹም ሚዲያዎችቹም በአብይ ሽንገላ ተንበረከኩ!
ሳይንበረከክ የቀረው አንድ ሚዲያ ብቻ ነው! ኢትዮ 360 ሃብታሙ ቦጋለ ኤርሚያስ ለገሰ ወዘተ...!
እነዚህ ሃቀኞች የተሰባሰቡበትን ሚዲያ አብይ አህመድ (ፈሪ ስለሆነ) ዘጋ! በዩቲዩብ ግን አሉ! ይህም (ከእነ ጥቃቅን ስህተቱ) የኢትዮጵያ ብቸኛው ማስ ሚዲያ ነው! ብቸኛ የሚለው ይሰመርበታል! ጉሮሮውን ይዝጋውና ዘጋው!
ይሁዳ ክርስቶስን አቅፎ ስሞ አሳልፎ እንደሰጠው አብይ አህመድም ኢትዮጵያን አቅፎ ስሞ ሳይሆን አቅፎ የሚስም መስሎ እየተፋባት አሳልፎ ሰጣት!
አንዳንድ ገልቱ ዜጋ "አብያችን ለነጮች አልንበረከክ ስላለ እነ እሜሪካ ተነሱበት!" ይላል::ሃሃሃሃ ..."በኢህአዴግ መቃብር ላይ!"የተባለውን ቴሌኮም ዘርፍ ሸጠኮ! ኖቬል ዝም ብሎ ይሰጣል እንዴ?ጉርቫቾቭ ኖቬል የተሸለመው ሶቭየትን አፍርሶ የዓለምን ርዕዮት ለአሜሪካ ስለሸጠ ነው!
ማንዴላ የሰላም ኖቬል የተሸለመው የነጮች የበላይነት በይቅርታ ሰበብ እንዲቀጥል ስለፈቀደ ነው! አብይ አህመድ የሰላም ኖሼል ተሸላሚ የሆነው ፕራይቬታይዜሽንን ሊፈቅድ ቃል ገብቶ ስለተሾመ ነው!
የአሜሪካን እና የእንግሊዝን የበላይነት ካሰፈንክ የሰላም ኖቬል ትሸለማለህ!
እናም አብይ አህመድ አይነኬውን ነክቶ ሊያስደስታቸው ቃል ገባ ተገበረው!
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በቴሌኮም ውስጥ ተሸጠዋል! ቴሌኮም ሲባል ስልክና ኢንተርኔት ብቻ ማለት የሚመስለው ገልቱ ካለ አናስተናግድም!
ከዚህ በሁዋላ ባህልህን ሃይማኖትህን ገንዘብህን አጠቃላይ ሁለንተናህን የምታገኘው በቴሌኮም ዘርፍ ነው! በቁጥር ቁጥጥር ስር ነህ! የኢትዮጵያ ህዝብ ከቴሌኮም ጋር ለእንግሊዝና ለአሜሪካ ተሸጦዋል!ኮሎኒያላይዝ ሆኖዋል! ምናልባት ይህ ምን ማለት እንደሆነ አሁን ሳይሆን ወደፊት ቀስስስስ እያለ የሚገባን እውነት ይሆናል.!
እና ምን ለማለት ነው... አብይ አህመድ ጂኒ የለበትም! ራሱ ጂኒ ነው ለማለት ነው!
ምንድነው ያልኩት?
ለማንኛውም አንዳንዶች እንዳሉት ሁሉንም እስረኞች ይፍታ! በቃ በረከትንም አብዲሌንም ይፍታ! ሁሉም ይፈቱ! ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ምድር መታሰር ያለበት ባለሰይጣን በዋናት አብይ አህመድ ነው!
ለነገሩ በረከትን አይፈታውም!ቢወጣ ምን እንደሚያደርገው ያውቃል!ስለበረከት መፈታት ቢሰማ ራሱ በቁሙ ሽንቱን እንደሚለቀው የታወቀ ነው!
እና... አብይ አህመድ እፍኝት የሚባለው እባብ ነው ለማለት ከዚህ በላይ ብዙ መሄድ ሊኖርብን ይችላል! ምናልባት ዳንኤል ክስረት ያስተባብልለታል ያኔ እኛም ዲያቆን ይሆናልን ይዘን እንከሰታለን!!!
"የእርሱ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን! እንጂ ካናገሩንማ እንናገራለን!"
በሰላም እደሩ::