Get Mystery Box with random crypto!

ሰማያዊት በሆነች በኢየሩሳሌም ሀገሬ በክብር በምስጋና በተጌጠች በጽዮን ቃል ኪዳን ገባሁልሽ የሙሽራ | 𝑑𝑎𝑔𝑖ℎ𝑎𝑏𝑟𝑠ℎ🇪🇹✝️🇪🇹✝️

ሰማያዊት በሆነች በኢየሩሳሌም ሀገሬ በክብር በምስጋና በተጌጠች በጽዮን ቃል ኪዳን ገባሁልሽ የሙሽራ አምሳል በሆነች በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከዕለታት መርጬ የተወለድኩባት የተጠመቅሁባት ለሰው ልጅ ደኅንነትን የምታስገኝ ትንሣኤዬንም የገለጥኩባት በሰንበተ ክርስቲያን ቃል ኪዳን ገባሁልሽ በደብረ ዘይት በተቀደሰውም በጽዮን ደብረ መንግሥቴ በመቃብሬ ቦታ በጎልጎታ ንጹሕ ብሩህ በሆነ ደም ግባትሽ ንጹሓት ክቡራት በሆኑ ልብሶችሽ በነዚህ ሁሉ ቃል ኪዳን ገባሁልሽ እናቴ ድንግል ማርያም ሆይ የሰጠሁሽን ቃለ ኪዳን እንዳልነሳሽ አማንየ ብዬ በራሴ ማልሁልሽ በአንቺ ስምም በሚቀደስበት ታቦት እኔ እረባለሁ መሥዋዕቱንም አሻትታለሁ እንደ አቤልም መሥዋዕት እቀበለዋለሁ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት እመቤታችንም መለሰችለት አንተ ቡሩክ ነህ ሰማያዊ አባትህም ቡሩክ ነው የባሕርየ ሕይወትህ መንፈስ ቅዱስም የተባረከ ነው፡፡ አለች ይህን ሁሉ በቸርነትህ ስለሰጠኸኝ አቤቱ ለአንተ ምስጋና ይገባል ለቸር አባትህም ምስጋና ይገባል ማኅየዊ ለሚሆን ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል ዛሬም ለዘወትርም እስከ ዘላለሙ አሜን፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእናቱ ይህን ነግሯት ከፈጸመ በኋላ ሰላምታ ሰጥቷት በታላቅ ምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ እሷም እግዚአብሔርን እያመሰገነች ወደ ቤቷ ተመለሰች እንዲህ እያለች አቤቱ አንተ የተመሰገንህ ነህ ስምህም የተመሰገነ ነው የመንግሥትህም ስም ይባረክ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ክብር ፅንዕ ለአንተ ይገባል ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘላለሙ ድረስ አሜን፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ በዚህ ቃል ኪዳንሽ ከተንኮለኞች ሰዎች እጅ ከጸዋጋን አጋንንትም መከራ እኔን አገልጋይሽን አድኝኝ አሜን፡፡

መልካም እውቀት የመቅሰም ጊዜ

https://t.me/dagihabeshaaa
https://t.me/dagihabeshaaa
https://t.me/dagihabeshaaa
Join