Get Mystery Box with random crypto!

ለሁሉም ነገር መጠን አብጅ። ከፍታህን በቁመትህ ልክ አድርግ። ከራስህ በላይ የሆነ ከፈታ መፈጥፈጥ | ቃል ብቻ

ለሁሉም ነገር መጠን አብጅ።
ከፍታህን በቁመትህ ልክ አድርግ። ከራስህ በላይ የሆነ ከፈታ መፈጥፈጥ ሊያስከትል አንደሚችል አስብ።
ውድቀትህም ከጫማህ በታች እንዳይሆን አድርግ።
ከውድቀት በኋላ አልነሳም ብሎ ማሰብ ከጫማ በታች መቀበር እንደሆነ ገምት።
ወድቆ መነሳትን ከቅርጫት ኳስ ተማር። ወድቆ የሚነጥር ማንነት ይኑርህ። ነጥሮም ቀለበቷ ውስጥ ነጥብ የሚያስቆጥር ህይወት ይኑርህ።
ወደ ከፍታ የወጣ ሁሉ ስኬት እንዳልሆነ እወቅ። ውድቀት መቀበር እንደሆነ ሁሉ መነሳትም መንሳፈፍ እንዳይሆንብህ ጥንቃቄ አድርግ።
በምትወድቅበት ጊዜ ላለመቀበር፣ በምትነሳበትም ጊዜ ላለመንሳፈፍ ይሁን



@CoolmanEfu
@CoolmanEfu