Get Mystery Box with random crypto!

​ ​'ራስህን ውደድ' .@CoolmanEfu ብዙዎቻችን ቆንጆ ሴት ስናይ ሁሉም ሰው ቤቱ ሊያስ | ቃል ብቻ

​ ​"ራስህን ውደድ"
.@CoolmanEfu
ብዙዎቻችን ቆንጆ ሴት ስናይ ሁሉም ሰው ቤቱ ሊያስቀምጣት ከሚፈልገው ቆንጆ አበባ ጋር እናወዳድራታለን ለራሳችን የምንሰጠው ግምት ግን ማንም ሰው የማይፈልገው የትም የሚበቅል አረም የሆን ያክል ነው በጣም የሚገርመው ለራሳችን የሰጠነውን ውዳቂ ማንነት ይዘን በሌሎች ለመወደድ እና ለመፈቀር ስንደክም እንታያለን
.
ራስን መውደድ እና ራስ ወዳድነት ለየቅል ናቸው ራስህን ስትወድ ሌሎችን መውደድ ትጀምራለህ እና ወዳጀ ሽራፊ የፊት መስታወትህ ላይ ራስህን እያየህ አምላክ በክብር የሰራህ እንደሆንክ ይሰማህ በሚሊየን ብሮች ልትሸጣቸው የማትችለው ነገሮች እንዳሉህም ጭምር ያኔ እንደ እኔ ምስል የደበዘዝክ እና ጥቁር እንኳ ብትሆን ውስጥህ በብርሀን ይጥለቀለቃል የውስጥ ደስታህ ደግሞ ፊትህ ገፅታ ላይ እንደሰንደቅ ይውለበለባል ሰዎችም አንተን መውደድ ይጀምራሉ
.
ስለዚህ እኔ ካለሁበት ውሀ መብራት እና መንግስት ከሌለባት ሀገር አንተ እስካለህበት ሀገር ርቀት ድረስ ራስህን ውደድ
━━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━━
............................%.........................

@CoolmanEfu
@CoolmanEfu
@CoolmanEfu
@CoolmanEfu
@CoolmanEfu