Get Mystery Box with random crypto!

#ሱዳን ' ቤተሰቦቻችን ስላሉበት ሁኔታ ለማወቅ አልቻልንም ፤ጭንቀት ላይ ነን ' በሱዳን እየተ | የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command

#ሱዳን

" ቤተሰቦቻችን ስላሉበት ሁኔታ ለማወቅ አልቻልንም ፤ጭንቀት ላይ ነን "

በሱዳን እየተካሄደ ያለው ውጊያ ዛሬ 6ኛ ቀኑን መያዙ ይታወቃል።

በሱዳን ያሉ ቤተሰቦቻችን ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ ካርቱም ወዳለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስልክ ብንደውልም ምላሽ አላገኘንም ሲሉ እዚህ ኢትዮጵያ የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መልዕክት ልከዋል።

በሱዳን ያሉ ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ባለመቻላቸው እንደተጨነቁ የገለፁት እንዚሁ የአባላት ፤ ማንን መጠየቅ እንዳለብን ግራ ገብቶናል ይህ ጉዳይ የሚመለከተው አካል ምላሽ ሊሰጠን ይገባል ብለዋል።

ለበርካታ ኢትዮጵያውያን ሁለተኛ ቤት በሆነችው ሱዳን ውስጥ ኢትዮጵያውያን ለስራ እና በቋሚነት ለኖሮ እንደሚገኙ ይታወቃል።

የሰሞኑ የሱዳን ውጊያ ደግሞ እዛ ያሉትን ብቻ ሳይሆን እዚህ ያሉ ቤተሰቦችንም ጭምር ጭንቀት ውስጥ ጥሏል።

ከትላንት በስቲያ በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፤ በሱዳን እየተካሄደ ባለው ውጊያ በርካታ ሲቪሎች ለጉዳት መዳረጋቸውና ህይወትም እየተቀጠፈ መሆኑን በመግለፅ ከእነዚህ መካከል #ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙበት መረጃዎች እንደደረሱት አሳውቋል።

ኤምባሲው ምን ያህል ኢትዮጵያውያን እንደሞቱ እና እንደተጎዱ በዝርዝር ባይገልፅም ይህን አስቸጋሪ ጊዜ ለማለፍ ኢትዮጵያዊን የተቻላቸውን ሁሉ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

መረጃ ለመለዋወጥ እና ለምክክር የኤምባሲው ባልደረባ የሆኑትን አቶ ነጅብ አብደላ በስልክ ቁጥር +249911646547 ማነጋገር እንደሚቻልም ገልጿል።

YouTube