Get Mystery Box with random crypto!

የንጹሀን ግድያ የሚከሰተዉ በመንግስት ቸልታ ነዉ የሚባለዉ የተሳሳተ ነዉ - ጠ/ሚ አብይ አህመድ | የኮማንዶና አየር ወለድ ኃይሎች የጦር ሜዳ ውሎዎች - Commando and Air Borne Battleships

የንጹሀን ግድያ የሚከሰተዉ በመንግስት ቸልታ ነዉ የሚባለዉ የተሳሳተ ነዉ - ጠ/ሚ አብይ አህመድ

6 ኛዉ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ አመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በተገኙበት ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያየ ይገኛል።

ከምክርቤቱ አባላትም ለ ጠ/ሚኒስትሩ በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። ከቀረቡት ጥያቄዎች ዉስጥም የጸጥታ ችግር ከመፈጠሩ በፊት አስቀድሞ መከላከል አይገባም ነበር ወይ? የንጹሀንስ ሞት መቼ ያቆማል? በቀጣይስ ችግሩ እንዳይከሰት መንግስት ምንድነዉ እቅዱ? የሚሉት ጥያቄዎች ይነሳሉ።

ጠ/ሚኒስትር አብይ በመልሳቸዉ የሽብር ቡድኖች የሚፈጽሟቸዉ ጥቃቶች በመንግስት ቸልተኝነት የሚፈጠር ነዉ የሚለዉ የተሳሳተ ነዉ ብለዋል። የሚፈጠሩ የጸጥታ ስጋቶችን ለማረጋጋትም የጸጥታ አካላት ዉድ ህይወታቸዉን እያጡበትም ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።

ለአብነትም በቅርቡ በወለጋ ደምቢዶሎ እና ጊምቢ ፣ ጋምቤላ ፣ አሙሮ በተከታታይ በተፈጸመሙ ጥቃትቶች በርካታ የጸጥታ ሀይሎች ህወታቸዉን አጥተዉበታል ብለዋል። ደራሼ ላይም የወረዳ አመራሮችን እና የጸጥታ አካላትን ጨምሮ 80 የሚሆኑ ሰዎች ህይወት አልፏልም ማለታቸዉን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

ከዚህ በተጨማሪም ጠ/ሚ አብይ ከሚፈጸሙ ጥቃቶች የበርካታ ንጹሀንንም ህይወት መታደግ ችለናልም ብለዋል።

ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፦ #ሼር #join
https://t.me/Commando_and_AirBorne_Battleship