Get Mystery Box with random crypto!

ኢየሱስ ያለው ህይወት አለው!!!!

የቴሌግራም ቻናል አርማ christianslike — ኢየሱስ ያለው ህይወት አለው!!!!
የቴሌግራም ቻናል አርማ christianslike — ኢየሱስ ያለው ህይወት አለው!!!!
የሰርጥ አድራሻ: @christianslike
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 184
የሰርጥ መግለጫ

❤️✅👉 ልጁ ያለው ሕይወት አለው። (1ዮሐ 5 :12)

👉ከይህን ቻናላችን ከሚያቀርቡ መካከል
❇ለመንፈሳዊ ህይወት የሚሆን የእግዚአብሔር ቃል በመካፈል
❇ጥያቄ እና መልስ በማቅረብ
❇አዳዲስ መዝሙሮች በምልክት ቋንቋ በመለቀቅ
👉ይህን ቻናላችን መስማት ለተሳናቸው ክርስቲያን ለሚመለከቱ ብቻ ይቀላቀሉ ይገቡ አሰተያየትዎ ጥያቄዎ ካለዎት በዚህ @TamelikeMiracle ይላክዎ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

3

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-07 11:32:55
. ይወራ ዝናው
°°°°°°°°°°°°
ዘማሪ ሳሙኤል ተ/ሚካኤል
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
New Amazing Gospel Song
@Christianslike
158 views@, 08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 22:38:38 ሰው በ___ ይድናል::
public poll

C. ፀጋ በእምነት – 3
50%
Tilahun, @TamelikeMiracle, @MEWDEDA

B. ፀጋው + መልከም ሥራ – 2
33%
meri, Seni

A. መልካም በሥራ – 1
17%
ዝም

D. ህግን በመፈፀም
0%

6 people voted so far.
302 views@, 19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 16:34:41
የመዝሙር ርዕስ-አንድ ወዳጅ
ዋናው መዝሙር-ኬፋ ሚቅደሳ
በምልክትቋንቋ መዝሙር ሽፋን-ጥላሁን ዳምጤ@12MB
125 views , 13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 16:27:18 የሥጋ ____የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥..... የመንፈስ ____ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፣የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። public poll መ. ሥራ እና ፍሬ – 6 60% Daniel, @TamelikeMiracle, Beti, Yom, Mohammed, getaye ሀ. ፍሬ እና ፍሬ – 2 20% Haile Negash Chimdi, Yabsra…
114 views , 13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 11:51:51 የሥጋ ____የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥..... የመንፈስ ____ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፣የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።
public poll

መ. ሥራ እና ፍሬ – 6
60%
Daniel, @TamelikeMiracle, Beti, Yom, Mohammed, getaye

ሀ. ፍሬ እና ፍሬ – 2
20%
Haile Negash Chimdi, Yabsra

ለ. ፍሬ እና ሥራ – 1
10%
17171717

ሐ. ሥራ እና ሥራ – 1
10%
Habtamu

10 people voted so far.
141 views𝕄𝕚𝕣𝕒𝕔𝕝𝕖, 08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 15:03:43
እርሱም የሰጠን ተስፋ ይህ የዘላለም ሕይወት ነው።(1 ዮሐንስ 2:25)
169 viewsMiracle Maker ........, 12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 18:33:50 የቅዱሳን_የክህነት_አገልግሎት
=============================

በአዲስ ኪዳን መጽሐፍት ውስጥ #ተደርጋችኋል እና #አደረጋቸው የሚሉ ቃላቶች ትልቅ ትርጉም የያዙ ናቸው። አድራጊው ቅዱሱ እግዚአብሔር ሲሆን ተደራጊወች ደግሞ በክርስቶስ የቤዛነት ስራ ያመኑ ቅዱሳን ሁሉ ናቸው።
ለምሳሌ እኛ በራሳችን መልካም ስራና ጥረታችን የእግዚአብሔር ጽድቅ መሆህ ስለማንችል እግዚአብሔር በክርስቶስ የራሱ ጽድቅ አደረገን። ተደርገን ከሆነ ከእኛ የሆነ ነገር የለም ማለት ነው።

የጸጋ አለም ውስጥ እግዚአብሔር አድራጊ ነው እኛ ደግሞ ተደራጊ ነን። እግዚአብሔር ሰጪ ነው እኛ ተቀባይ ነን።

ስለ ክህነት መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ካህን ማለት በእብራይስጥ "ኮኸን" በግሪክ ደግሞ "ሂሪዬስ (hiereús)" ማለት ሲሆን ትርጉሙም
ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ፣ የሚያገለግልና መስዋዕት የሚያቀርብ ማለት ነው።

በብሉይ ኪዳን ዘመን ለአሮን እና ለአሮን ቤተሰብ ይህ እድል ተሰቷቸው ነበር። ነገር ግን ይህ የአሮን ክህነት በመሀላ ያልጸና ጊዜያዊ ስለነበር ሊቀጥል አልቻለም እግዚአብሔርም በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ አስወግዶታል።

በአዲስ ኪዳን ግን በክርስቶስ የቤዛነት ስራ ያመኑ ቅዱሳን ሁሉ ካህናት የሆኑበትና ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ሊቀ-ካህናት (የካህናት አለቃ) የሆነበት ዘላለማዊ የክህነት ስርዓት እንደመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል።ከዚህም የተነሳ በአዲስ ኪዳን የሚገኝ አንድ አማኝ በብሉይ ኪዳን ከነበረው የአሮን ክህነት በተሻለ ክብር ለማገልገል ተጠርቷል። ዕብ 7:11-28, ዕብ8:1-13

በሀይማኖቶች ዘንድ ሰዎች ካህን ለመሆን አድርጉ የሚባለውን በማድረግ ፣ አጥኑ የተባለውን በማጥናትና ሐይማኖታዊ ስርአቶችን በመፈጸም ይደክማሉ ይጥራሉ ያም ሆኖ ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ካህናት መሆን አልቻሉም።

መጽሐፍ ቅዱስ ግን ካህን መሆን የሚቻለው በክርስቶስ ደም እንደሆነ ይናገራል። ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱሱ እውነት መሰረት በክርስቶስ ያመኑ ቅዱሳን ሁሉም በክርስቶስ ለሰማይ አምላክ ካህናት ተደርገዋል ይለናል።

ራእይ 1፡4-6, እና ራእይ 5:9-10
ለወደደን_ከኃጢአታችንም_በደሙ_ላጠበን፤ መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም #ካህናት #እንድንሆን_ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን።

ራእይ 5 :9-10፤ መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር
ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና #ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፡ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።
እነዚህ ጥቅሶች በክርስቶስ የቤዛነት ስራ የተዋጁት ቅዱሳን ሁሉ ካህናት እንደተደረጉ የሚናገሩ ናቸው።

ቅዱሳን ሁለት አይነት የክህነት አገለግሎት እንደተሰጠን ልብ ልንል ይገባናል፦
=============================

1, ቅዱሳን ካህናት፦
1ጴጥ 2:4-5
ይህኛው የክህነት አገልግሎት ወደ እግዚአብሔር መንፈሳዊ መስዋዕት የምናቀርብበት ሲሆን። ለአምላክ ብቻ መስዋትን አምልኮን ውዳሴን የምንሰዋበት ሰማይ ተኮር የክህነት አገልግሎት ነው።

1 ጴጥሮስ 2 :5፤ እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።

2 ,የንጉስ ካህናት፦
1ጴጥ 2:9
ይህኛው የክህነት አገልግሎት የእርሱን በጎነት ለሰው ሁሉ የምናውጅበት ነው። ይህኛው የክህነት አገልግሎት የእግዚአብሔር መልካምነት ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር በክርስቶስ የሰራውን ስራ ለሰው ሁሉ በመናገር የምናገለግልበት ክህነት ነው።

1 ጴጥሮስ 2 :9፤ እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤

ኤፌሶን 1:6፤ በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ።
ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

Channel http://t.me/Christianslike
457 viewsMiracle Maker ........, 15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-20 20:06:35 ፤ መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው፥ የዘላለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፤ ጠላትህን ከፊትህ አውጥቶ፡— አጥፋው፡ ይላል።(ዘዳግም 33 :27)

The eternal God is thy refuge, and underneath are the everlasting arms: and he shall thrust out the enemy from before thee; and shall say, Destroy them.(Deuteronomy 33 :27)

Channel t.me/Christianslike
279 viewsMiracle Maker ........, edited  17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-15 11:23:22 አንተን አመልክሃለሁ
(አዲስዓለም አሰፋ)

ብዙ ምሥጋና ብዙ ዝማሬ ወደ ማደሪያህ
ይዤ እገባለሁ አምላክ ነህና ስለሚገባህ (፪x)

አዝ፦ አንተን አመልክሃለሁ (፬x)
እንደ አንተ ታማኝ አምላክ ማነው (፬x)

በብዙ ምሥጋና እገባለሁ ፊትህ እገባለሁ
በብዙ ምሥጋና እገባለሁ ደስ አሰኝሃለሁ
በብዙ ዝማሬ እገባለሁ ፊትህ እገባለሁ
በብዙ ዝማሬ እገባለሁ ደስ አሰኝሃለሁ

ምስጋና ሚሰዋ እንደሚያከብርህ
በአንተ ደስ የሚለው ከእኔ ጋር ከፍ ከፍ ያርግህ
በአማረ ቅኔ በአማረ መዝሙር
ከዕልልታ ጋራ ኢየሱሴ ይሁን ለአንተ ክብር

ምስጋና ሚሰዋ እንደሚያከብርህ
በአንተ ደስ የሚለው ከእኔ ጋር ከፍ ከፍ ያርግህ
በአዲስ በአዲስ ቅኔ በአማረ መዝሙር
ከዕልልታ ጋራ ወዳጄ ይሁን ለአንተ ክብር

ብዙ ምሥጋና ብዙ ዝማሬ ወደ ማደሪያህ
ይዤ እገባለሁ አምላክ ነህና ስለሚገባህ (፪x)

አዝ፦ አንተን አመልክሃለሁ (፬x)
እንደ አንተ ታማኝ አምላክ ማነው (፬x)

በብዙ ምሥጋና እገባለሁ ፊትህ እገባለሁ
በብዙ ምሥጋና እገባለሁ ደስ አሰኝሃለሁ
በብዙ ዝማሬ እገባለሁ ፊትህ እገባለሁ
በብዙ ዝማሬ እገባለሁ ደስ አሰኝሃለሁ (፪x)

Channel t.me/Christianslike
179 viewsMiracle Maker ........, edited  08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ