Get Mystery Box with random crypto!

ስለ ማርያም ብዙ ጊዜ ከኛ ሀይማኖት ውጪ ያሉ ሰዎች እናንተ ኦርቶዶክሶች ለማርያም ያላቹ ክብር | (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን)✝️

ስለ ማርያም

ብዙ ጊዜ ከኛ ሀይማኖት ውጪ ያሉ ሰዎች እናንተ ኦርቶዶክሶች ለማርያም ያላቹ ክብርና ፍቅር የተለየ ነው ይሉናል የተጋነነም ነው ይሉናል ።እስቲ ወደ ሁዋላ መለስ ብለን እናስታውሳቸው ። የሆሳዕና ዕለት ህዝቡ ግማሹ ልብሱን ግማሹ ዘንባባውን እያነጠፈ የነበረው እኮ ክርስቶስን አክብሮ እንኳን አንተ ይቅርና የተቀመጥክባት አህያ እንኳን መሬት አትነካም ሲሉ እኮ ነው ። እና እንስሳዋ አህያ ለ1 ሰአት ለማይሞላ ጊዜ ክርስቶስ ስለተቀመጠባት ብቻ በዘመኑ የነበሩ ሰዎች ያን ያህል ካከበሯት 9 ወር ከ 5 ቀን በማህፀኗ ተሸክማ በድንግልና ወልዳ አቅፋ አጥብታ አሳድጋ ይዛ ግብፅ ተሰዳ ሲሰቀል አይታ ላነባችለት ይሄን ሁሉ ለሆነችለት እናቱ እኛ የዘመኑ ክርስቲያኖች ክብር ብንሰጥ ጥፋታችን ምንድነው ? እኛስ ለማርያም ክብር እንሰጣለን ። ከአባ ህርያቆስም ጋር ሆነን እንዲህ እንላታለን "ማርያም ሆይ እንወድሻለን ስለዚህም እናገንሻለን ፡ የህይወትን ምግብና መጠጥ ወልደሽ ሰጥተሽናልና "።