Get Mystery Box with random crypto!

ህልሞቻችን 3 ዛፎች ነበሩ ። 2ቱ የቆሙ ሲሆኑ አንዱ ግን የወደቀ ነው። ከእለታት በአንድ ቀን | (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን)✝️

ህልሞቻችን

3 ዛፎች ነበሩ ። 2ቱ የቆሙ ሲሆኑ አንዱ ግን የወደቀ ነው። ከእለታት በአንድ ቀን ህልማቸውን ይነጋገሩ ጀመር ። አንደኛው እኔ ሳጥን ሆኜ የአለም ውድ እቃ አልማዝ እንቁ እንዲቀመጥብኝ እፈልጋለው አለ፣ ሁለተኛው ደሞ እኔ መርከብ ሆኜ የአለም ነገስታት እንዲጓጓዙብኝ እፈልጋለው አለ ፣ ሶስተኛው ደሞ እኔ ደሞ እኔ መድሀኒት ሆኜ ብዙዎችን ማዳን እፈልጋለው አለ ። ሶስቱም ህልማቸውን አውርተው ሲጨርሱ ዛፍ ቆራጮች መጡ የወደቀውን አነሱት ይዘውትም ሄዱ ። እሱም ሳጥን መሆን የሚፈልገው ነበር እነሱም ጠርበው የከብቶች መመገቢያ አድርገው ሰሩት።ሁለተኛውንም መጥተው ቆረጡት እሱም መርከብ መሆን የሚፈልገው ነበር እነሱም ጀልባ አድርገው ሰሩት ። ሁለቱም ዛፎች ተናደዱ ህልማቸው የተጨናገፈም መሰላቸው። ከአመታት ቡሀላም ክርስቶስ ተወለደ። እነሆም ቦታ ስላልነበር በከብቶች በረት ተወለደ። እናቱ ማርያምም በከብቶች መመገቢያ ውስጥ ጠቅልላ አስቀመጠችዉ። ያም የአለም ውድ ነገሮች ማስቀመጫ መሆን እፈልጋለው ያለው ነበር ፡ የውዶች ውድም የሆነው ጌታም ተቀመጠበት። ጌታም ሊያስተምር ሲሄድ በታንኳ ተጓዘ ፡ ያም ታንኳ ያ የአለም ነገስታት እንዲጓጓዙብኝ እፈልጋለው ያለው ነበር፡የነገስታት ንጉስም ተጓጓዘበት። ጌታም እንዲሰቀል ሲፈረድበት የቀረውን ዛፍ ቆርጠው አመጡ በሱም ሰቀሉት። እሱም ለብዙዎች መድሀኒት መሆን የፈለገው ዛፍ ነበር። እሱም መስቀል ሆኖ አለም ሁሉ ዳነበት። ሶስቱም ዛፎች ህልማቸው የተጨናገፈ ሲመስላቸው ፈጣሪ ግን ካሰቡት በላይ አድርጎ አሳካላቸው። ወዳጄ ህይወት መንገዷን የቀየረች ህይወትህም በችግር የተሞላ ሊመስልህ ይችላል። ዛሬ አንተን የሚያማርሩ ነገሮች ፈጣሪ አንተን የነገ ህይወትህን ለመስራት የሚጠቀምባቸው ንጥረ ነገሮች ናቸው ። ነገሮች ሲመሰቃቀሉ ምናልባት ቦታ ቦታቸውን እየያዙ ይሆናል። የማይገድል ችግር ሁሉ ያጠነክርሀል ።