Get Mystery Box with random crypto!

ክርስቲያናዊ ወጣት

የቴሌግራም ቻናል አርማ cherstianawiwetat — ክርስቲያናዊ ወጣት
የቴሌግራም ቻናል አርማ cherstianawiwetat — ክርስቲያናዊ ወጣት
የሰርጥ አድራሻ: @cherstianawiwetat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.98K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል እኛ ወጣቶች እንዴት መንፈሳዊነትንና ዘመናዊነትን አጣምረን መሄድ እንችላለን? የሚለውን ሀሳብ እንማማራለን። ጆይን በማለት ሥርዓትን እንወቅ እናሳውቅ።
@wetatZeTewahido

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2021-11-30 00:16:26 #ኅዳር_21

#ቅድስት_ጽዮን_ድንግል_ማርያም

ኅዳር ሃያ አንድ በዚች ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የበዓልዋ መታሰቢያ ነው።

"ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው። አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው። ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል።

እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በሁዋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር፣ ሞገስ፣ አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል። (ዘጸ. 31፥18) ከዚያም ለ500 ዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች።

ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ በቀዳማዊ ምኒልክ (እብነ መለክ-እብነ ሐኪም) አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች። እነሆ በሃገራችን የ3ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው። ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ መስቀሉንና ታቦተ ጽዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን።

ያም ሆኖ ታቦተ ጽዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን። ግን አንጨነቅም። ምክንያቱም የመጣችውም የምትጠበቀውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነውና እንጸልያለን እንጂ አንጨነቅም። በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም። ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም።

ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን፣ ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች። "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው። "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው።

"ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው። ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል። ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው። በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን። (2ቆሮ.6፥16 ፣ ራዕይ.11፥19)

በመጨረሻም ኅዳር ሃያ አንድ ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች እንመለከታለን።

#በዚህች_ቀን:-
✞ ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን።

✞ ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ።

✞ በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ። አገለገለ። ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ የተቀኘላት በማሰብ።

✞ ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች። በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታልና ይህንንም በማሰብ፤

✞ በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግስት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን በማሠብ፤

✞ አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ፤

✞ በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ፤

በእነዚህ ምክንያቶች በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋር ይኑር።

(ስንክሳር ዘተዋህዶ እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
2.4K viewsΠαρακαλώ συγχωρήστε μας, 21:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-28 16:57:17 ደስ ይበላችሁ! ደስ ይበላችሁ! ደስ ይበላችሁ!

ቅዱስ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ 4፡4 ላይ ‘‘ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ’’ ካለ በኋላ መልሶ ‘ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ’ አለ፡፡ አንዴ ደስ ይበላችሁ ካለ ቢበቃም በዛው ዓረፍተ ነገር ድጋሚ ‘ደስ ይበላችሁ’ ማለት ለምን አስፈለገው? ለነገሩ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ መልእክቱ ላይ ደስ ይበላችሁ ያለው እዚህ ዓረፍተ ነገር ላይ ብቻ አልነበረም፡፡ በጣም አጭር በሆነው ባለ አራት ምዕራፉ ለፊልጵስዩስ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ ላይ ጳውሎስ 16 ጊዜ ደስ ይበላችሁ ፣ ደስ ብሎኛል ፣ ደስ ይበለን ፣ ደስታዬ ተፈጸመ ፣ ደስ አለኝ ፣ ደስታ ፣ ደስ ፣ ደስ ብሏል፡፡ በዚም ምክንያት የፊልጵስዩስ መልእክት የደስታ መልእክት ተብሎ ይጠራል፡፡ ይህን የምታነቡ ሁሉ እኔም ከሐዋርያው ጋር ልላችሁ እወዳለሁ ፤ ደስ ይበላችሁ!

ምናልባት በዚህ ሰዓት በከባድ የመንፈስ ጭንቀትና ችግር ውስጥ ወይም በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ያለ ሰው ይህንን የቅዱስ ጳውሎስ ‘ደስ ይበላችሁ’ ጥሪ ሲያነብ ‘አንተ ደልቶሃል ወዳጄ እኔ እንኳን ደስ ሊለኝ ሰማይ ምድሩ ተደፍቶብኛል’ ማለቱ አይቀርም፡፡ የሚገርመው ግን ጳውሎስ ይንን ዐሥራ ስድስቴ ደስ ይበላችሁ የሚል ደብዳቤ የጻፈው እስር ቤት ውስጥ ሆኖ ነበር፡፡ እግሩ በሚቀዘቅዝ ጉድጓድ ውስጥ በሚከረክር ብረት ታስሮ ፣ እጆቹ ከመሬት ጋር በሰንሰለት ተጣብቀው እያለ ፣ ከታሠረ ሦስት ዓመት ሊሞላው ሲል በፈገግታ ተሞልቶ ‘ደስ ይበላችሁ’ የሚል ደብዳቤ ጻፈ፡፡

እስር ቤት ውስጥ ያለ ሰው ደብዳቤ እንዲጽፍ ዕድል ቢሠጠው ምን ብሎ የሚጽፍ ይመስልሃል? ‘የእስር ቤቱ አበሳ’ ‘የወኅኒው ምሥጢሮች’ ‘ገራፊዎቼና ጭካኔያቸው’ ‘የግርፋቴ ጠባሳዎች’ የሚል ዓይነት የደረሰበትን ሥቃይ የሚገልጹ መጻሕፍት አይጽፍ ይሆን? ያም ባይሆን ለቤተሰቦቹ ሲጽፍ ‘ኸረ ቁንጫውን አልቻልሁትም! ምግቡ አልተስማማኝም ፣ እገሌ ምነው አልጠየቀችኝም ደህና አይደለችም? ፣ እነ እንቶኔ ግን የማይጠይቁኝ ለምን ይሆን? እኔ ለእነርሱ እንዲህ ነበርሁ? ነግ በኔ አይሉም ወይ? ‘ያስተዛዝበናል ይኼም ቀን ያልፍና’ የሚል ይዘት ያለው ሊሆን ይችላል፡፡

ይህም ባይሆን እንኳን ከእስር ቤት ውስጥ ሆኖ 16 ጊዜ ‘ደስ ይበላችሁ’ የሚል ደብዳቤ ጽፎ ለቤተሰቡ የሚልክ ሰው አይኖርም፡፡ እንደዚያ ብሎ ቢጽፍ እንኳን ቤተሰቦቹ ‘አእምሮው እየተነካ ነው! እነዚህ ሰዎችማ የሆነ ነገር ሳይወጉት አይቀሩም! ራሱን ሊያጠፋ ይሆን?’ ብለው ይጨነቃሉ እንጂ የእስር ቤቱን እንኳን ደስ አላችሁ ከቁም ነገር ቆጥረው ‘እንኳን አብሮ ደስ አለን’ አይሉም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የጻፈውን ደብዳቤ ግን ቤተ ክርስቲያን ከማንበብ አልፋ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አካተተችው፡፡ ጳውሎስ ደስ ያለው በእስር ቤቱ ፣ በሥቃዩ አልነበረም፡፡ ደስ ይበላችሁ ያለው በጌታ ነው! ከሚደርስበት መከራ በላይ የደረሰለት ፈጣሪ በልጦበት ውስጡ በደስታ ተሞልቶ ስለፈሰሰ ከታሰሩት አልፎ ውጪ ላሉት ደስታ እስከመመኘት ደረሰ፡፡ ጭንቅ ጥብብ ብሎህ ይህንን የምታነብ ወንድሜ ሆይ ጳውሎስም እንዳንተ ጭንቅ ላይ ሆኖ ‘በጌታ ደስ ይበልህ’ እያለ ነው፡፡

እግዚአብሔርን ስታስብ መከራህ ሁሉ ትንሽ ይሆናል፡፡ ጳውሎስን በቀዝቃዛው ጉድጓድ ውስጥ ሆኖ ደስታ ያሰጠመው ፈጣሪውን አስቦ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለነበር ውጪ ላሉት ክርስቲያኖች ‘በደስታ እጸልያለሁ’ አለ ፣ እሱ በሌለበት በተለያየ ምክንያት ወንጌል የሚሰብኩ ሰባኪያን በመብዛታቸው ‘ክርስቶስ ይሰበካልና ደስ ብሎኛል’ አለ፡፡ እስር ቤት መጥተው ላልጠየቁት ሰዎችም ‘አሁን ከጊዜ በኋላ ስለ እኔ እንደ ገና ልታስቡ ስለ ጀመራችሁ፥ በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፤ ጊዜ አጣችሁ እንጂ፥ ማሰብስ ታስቡ ነበር’ እያለ በደብዳቤው አጽናንቶአቸዋል፡፡ የዚህ ሁሉ ደስታ ምንጩ ግን ከመከራው በላይ እግዚአብሔርን ማየቱ ነበር፡፡

እምነት እንዲህ ነው ፤ ጳውሎስ እግር ከወርች ከመታሰሩ በላይ ያየው ጌታውን ነበር፡፡ ዳንኤል ከአንበሶች ጋር ሲተኛ ያየው የአንበሶቹን ጥርስ ሳይሆን ፈጣሪውን ነበር፡፡ እስጢፋኖስ ድንጋይ ሲወርድበት ገለባ የመሰለው ጠላቶቹ በቀኝ እጃቸው ከያዙት ትልቅ ድንጋይ ይልቅ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ ያለውን እየተመለከተ ስለነበር ነው፡፡ ወዳጄ ምናልባት በሕይወትህ የተጫነህ ድንጋይ ፣ ሊውጥህ የቀረበ አንበሳ አይጠፋም ፤ ጳውሎስና እርሱን መሳይ ቅዱሳን ግን ጥሪ ያቀርቡልሃል ፡፡ ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበልህ!

ክርስትና የመጨነቅ የመጨፍገግ ሳይሆን የደስታ ሃይማኖት ነው፡፡ የተፈጠርነው ለደስታ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ማንም የማይነጥቀው ደስታ የሚሠጥ አምላክ ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ‘በደስታ ተገዙ’ ተብለናል፡፡ /መዝ.100፡2/ ወንጌል የምሥራች ነው፡፡ ወንጌል የሚጀምረው ድንግሊቱን ደስ ይበልሽ ፣ እረኞችንም ደስ ይበላችሁ በማለት ነበር፡፡ ጥምቀቱንም ‘’በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ’ የሚል ምስክርነት አለበት፡፡ክርስቶስ መከራን ሲቀበልም ‘ነውርን ንቆ በፊቱ ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ’ ነበር፡፡ /ዕብ 12፡2/ በክርስቶስ የማመን የመጨረሻው ግብም ‘ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ የሚለውን የሕይወት ቃል መስማት ነው፡፡ /ማቴ 25፡21/

ጳውሎስ ‘’በጌታ ደስ ይበላችሁ’ አለ፡፡ ቅዱስ እንጦንስ የጳውሎስን ቃል ሲያብራራ እንዲህ ይላል ፦ በጌታ ደስ ይበላችሁ በዓለም አይደለም፡፡ በእውነት ደስ ይበላችሁ በዓመፅ አይደለም፡፡ በዘላለም ተስፋ ደስ ይበላችሁ በሚረግፉ አበቦች አይደለም፡፡ ደስታ ማለት ይህ ነው ፤ የቱንም ያህል በምድር ላይ ብትቆዩ እግዚአብሔር ቅርብ ነውና አትጨነቁ!’’

መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ዓይነት ደስታ አለበት ፤ ወዳጄ አንተ አንዱን መርጠህ ደስ ይበልህ፡፡

ዳዊትን ተመልከተው ‘ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ’ ይልሃል፡፡ ልብ አድርግ ‘’ጎልያድን ግንባሩን ብዬ ስጥለው ደስ አለኝ’ አላለም፡፡ ንጉሥ ሆኜ የተቀባሁ ቀን ደስ አለኝ አላለም፡፡ እሱ ደስ ያለው ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ያሉት ቀን ነበር፡፡ ‘እኔ እኮ ንጉሥ ነኝ ሥራ ይበዛብኛል ባይሆን እናንተ ሒዱ እኔ በገንዘብ ልርዳችሁ’ አላለም ፤ መሔጃ ያላጣው ባለጸጋ ንጉሥ ወደ ድንኳንዋ የእግዚአብሔር ቤት እንሒድ ሲሉት ደስ አለው፡፡ እዚያ ሔዶ ዙፋኑን አስዘርግቶ መንግሥትን በመወከል ‘መንግሥት ለእምነት ተቋማት ትኩረት ይሠጣል’ የሚል እግዚአብሔር ላይ የሚመጻደቅ ቅብርር ያለ ንግግር ሊያደርግ ፈልጎ አልነበረም፡፡ እርሱ የፈለገው እግዚአብሔር ሥር ለመውደቅ ነበር፡፡ ‘ከአእላፋት ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች ፤ በኃጢአተኞች በድንኳን ከመቀመጥ ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ’ አለ፡፡ /መዝ. 84፡10/

የዕንባቆምን ደስታ ተመልከተው ‘ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ’ ይልሃል፡፡ ኑሮው ምስቅልቅል ቢልም፣ ችግር ቢያስጨንቀውም በእግዚአብሔር ደስ ብሎት ነበር፡፡ /ዕን 3፡17፡18/

(ከዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
2.0K viewsΠαρακαλώ συγχωρήστε μας, 13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-25 22:48:55 "ስለ ወንድሙ መዳን የማይጨነቅ ድኗል ብዬ አላስብም "

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

ሰላመ እግዚአብሔር ከናንተ ጋር ይሁን

በሀጥያት ቁስል ተመተን ቀና ብለን ማየት መራመድም ጭምር እስኪያቅተን ድረስ አቀርቅረን ፤ለሰው ብንናገረው የማይረዳን ህመም ሆኖብን አፍነን ይዘን በጭንቀት ስንሰቃይ ፤ብርሀን አጠን በጨለማ ማየት ተስኖን ስንጨነቅ ፤
#ገመና ሸፋኝ የሆነ የልብ አውቃ የታመሙትን የማይጠየፍ ለጨለመብን ብርሃን ለቁስላችን መድሀኒት ከዚያ ኪሩቤል እና ሱራፌል ክንፋቸውን ዘርግተው ሳያቋርጡ #ቅዱስ_ቅዱስ_ቅዱስ ብለው ከሚያመሰግኑበት ዙፋን ምስጋና ሳይጎድልበት ፺፱ አለኝ ፩ ይጥፋ ሳይል በፍቅር የሚፈልግ ቸር ሩህሩህ የሆነ የክብር ባለቤት ሳይንቅ የሚፈልገን
.ይህን ያህል ክብር ያለው ቸር ተመስጋኝ የአምላኮች አምላክ የሆነ ንጉስ ሳይንቅ ከፈለገን እና ለጨለማችን ብርሃን ከሆነን በቁስላችን ላይ ጎንበስ ብሎ ክብሩ ሳያሳስበው ዘይትን ካፈሰሰልን
`ታድያ እኔ እና አንቺ/ተ ከኃጢአት ፍፁማን ልንሆን የማንችል ደካማ ፍጥረቶች ስንሆን የፈጠረን ሳይንቅ ጎንበስ ብሎ በደሀው ቤት ከገባ እኛ ስለምን በጎስቋላው ቤት አንገባም ስለምን ሰውንስ እንንቃለን ስለምን የአንዱ መውደቅ አያሳስበንም በወደቀው ላይ ከመጠቋቆም እና የማስመሰልን ኑሮ ከመኖር በመልካምና ተገቢ በሆነ ተግሳጽ መመለስና ማንሳት መልካም ነው።
ብዙ ጊዜ ሰወች ከቀድሞ ማንነታቸው ሲወጡ (ሲቀየሩ)በወንዶች ዝምታ በሴቶች ደግሞ መራቅ፤ከቀድሞ ግንኙነት መቀነስ፤የአሽሙር ንግግር መናገር ....የመሳሰሉትን በመጠቀም ይሉኝታ ያለባቸው ከንግግሩ እና ፊት መነሳታቸውን በመፍራት ይመለሳሉ፤ልባቸው የደነደኑትም ጭራሽ ሳይቀርቡ ብዙውን እንዲርቁ አድርገናል

ስራቸውን አለመደገፉ መልካም ሆኖ ሳለ እነሱን በመልካም መንገድ መምከር እየቻልን ልባቸው የደነደኑትን እንዳይመለሱ ምክንያት ሆነናል ይልቁንም ደጉ ሳምራዊ እንዳደረገው ቀርበን ቁስላቸው እናክም ከቅዱስ ቃሉ እያወጣን የፍቅርን ቃል በልባቸው እናፍስላቸው ከስጋ ቁስል የነፍስ ቁስል ይበልጣልና
አምላካችን ክርስቶስ እንዳደረገው ህመማችንን እንደታመመ እንታመምላቸው በአላዛር ሞት እንዳለቀሰ እኛም በወንድማችን ውድቀት እናልቅስ የውድቀት መጨረሻው ሞት ነውና ደግሞ ከሞት እንዳስነሳው እኛም እናስነሳቸው የርሱ ቃል ህይወት ይሰጣልናበቃሉ እናፅናናቸው
አንድ አባት ሲያስተምሩ "ወንድሞች ሆይ ተስፋ አትቁረጡ "አሉና "ይህን የምላቹ ለራሴ ስል ነው "አሉ የአንዱ በሃጢአት ምክንያት ተስፋ መቁረጥ ሁሉንም ይጎዳልና ሁላችንም ከሀጥያት ለመውጣትም ሆነ ለማሶጣት ተስፋ አንቁረጥ ለራሳችን ስንል እንኳን
ይህን ያነሳሁላችሁ በቅርቡ ምክሯን የለገሰችን እህቴ ከነገረችኝ ሁሌም በሄደችበት ስታነሳው ከምትኖረው ታሪክ በመነሳት ነው
በመንፈሳዊ ህይወታቸው ጠንከር ያሉ ሰወች የሰይጣን ፈተና ይበዛባቸዋል እና እሷም በአለም ነገር ተስባ ጌጣጌጡ ልብሱ ጭፈራው ስቧት ከመንፈሳዊ ህይወቷ የመውጣት መንገድ ጀምራ ሳለ
የቀድሞ ጓደኞቿ ፊት በመንሳት በአሽሙር በመናገር በመራቅ አዲሱን ማንነቷን በማጣጣል ....እሷ ደግሞ ይሉኝታም ጭምር ስለነበረባት ፈርታ ከዛ ማንነት ወጥታ ወደ መንፈሳዊነት ተመልሳለች እግዚአብሔር የሚወደውን በአንድም በሌላም ይጠብቃል እና እሷንም ጠብቋታል እሷም ይሄ ገብቷታል እና በመለያያቸው ቀን ሰው በተሰበሰበበት አመሰገነቻቸው እናንተ ፊት ባትነሱኝ ኖሮ ዛሬ ከአባቴ እቅፍ እወጣ ነበረ በማለት
አመሰገነች
አውቀንም ይሁን ሳናውቅ በሰወች መንፈሳዊ ህይወት መብቃትም ይሁን መውደቅ ውስጥ ተፅዕኖ አለንና ሁልጊዜም ቅን በመሆን ለራሳችን ስንል የወደቁትን እናንሳ ነገ መውደቅ አለና እኛንም ያነሱናል
እነሱ እንዳደረጉት ፊት በመንሳት ሳይሆን በመልካም ቀረቤታ ቀርበን መክረን ብንመልሳቸው የተሻለ ነው። ልቡ የደነደነው ጭራሽ በትዕቢት መመለሱ ይከብደዋልና
እህታችንም ፊት ነስተው ስለመለሷት እንዲህ ካመሰገነች በፍቅር የምንመልሳቸውማ እንዴት ደስ ብሏቸው ያመሰግኑን ይሆን ወደ እግዚአብሔር እቅፍ መግባት ከደስታም በላይ ነውና።

ቀርበን የመምከር ልምዱ ከሌለን እራሳችንን ከነሱ ዝቅ አድርገን ከተመለከትን ደግሞ ማለት ብዙ ጊዜ መንፈሳዊ የነበሩ ሰወች ሁሉን ያውቃሉና ለመምከር ከባድ ነው
ቢሆንም በዚ ጊዜ ያውቃል እያወቀ ነው ሚያጠፋው ብለን አንተዋቸው ከሁሉ በላይ ሀይል ያለው #ጸሎት ነው በጸሎት ወደ ፈጣሪ እናሳስብላቸው
#when_God_wants_to_have_mercy_on_someone_he_inspires_someone_else_to_pray_for_him_and_he_helps_in_this_prayer"


ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በእህታችሁ ወለተ ስላሴ
1.9K viewsΠαρακαλώ συγχωρήστε μας, 19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-25 07:15:34 ለምንድን ነው የምንጾመው?

እንደ አንድ ክርስቲያን [በግልም በአዋጅም] በመደበኛነት እንድንጾም ታዝዘናል፡፡ ኾኖም እስኪ ጥያቄ እናንሣ! ለምንድን ነው የምንጾመው? በመራባችን ምክንያት እግዚአብሔር ደስ ይሰኛልን? በየቀኑ እግዚአብሔርን ለማገልገል በቂ ነው የሚባል ምግብ ልናገኝ እንደሚገባን የታ ወቀ የተረዳ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ [በመጾማችን - በመራባችን] ውስጥ ያለው ምሥጢርና እግዚአብሔር ከዚያ ውስጥ የሚፈልግብን ፍሬ ምንድን ነው?

በልብ መታሰቡ፣ በቃል መነገሩ፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም መዘከሩ ይክበር ይመስገንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመጾ ማቸው ምክንያት የሚገበዙትን እጅግ ወቅሷቸዋል፡፡ ጾም የሚያስታብይ አይደለም ሲላቸው ነው፡፡
ስለዚህ እግዚአብሔር እንድንጾም የሚፈልገው ስለ ኹለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው፡-

#አንደኛው፥ ራሳችንን ከዚህ ዓለም ነገሮች - ከእነርሱ ዋናውም ከምግብ - አርቀን ወደ መንፈሳዊ ነገሮች እንድናቀርብ ስለሚፈልግ ነው፡፡ በየጊዜው በየሰዓቱ ስንበላ ሥጋችን ተድላ ደስታ ያደርጋልና፡፡ በመሠረቱ ምግብ በልቶ ደስ መሰኘት በራሱ ነውር ኾኖ አይደለም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የአማናዊ ተድላና ደስታ ምንጩ መንፈሳዊ ተግባር እንደ ኾነ እናስብ ዘንድ ይሻል፡፡ ስለዚህ እንድንጾም የሚፈልገ ውና በዚያውም ውስጥ እንድናስተውለው የሚፈልገው የመጀመሪያው ምክንያት ይኸው ነው፡፡

#ኹለተኛው ምክንያት ደግሞ ማጣት ዘወትር እንዲራቡ ከሚያደርጋቸ ው ሰዎች ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን ስለሚሻ ነው፡፡ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ተከትለን በየጊዜው ልንጾም እንችላለን፡፡ ይህ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አስገድዶአቸው ሳይኾን እጦት አስገድዶአቸው ያለማቋ ረጥ ዘወትር የሚጾሙ ሰዎች ግን አሉ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ለእነዚህ ሰዎች እውነተኛ ፍቅር እንድናሳይ ይፈልጋል፡፡ አጥቶ የመራብ ትር ጕሙ ምን ማለት እንደ ኾነ እኛው ራሳችን በተግባር እንድናይ ይሻል፡፡ በጾማችን ውስጥ እንድናፈራው የሚፈልገው አንዱ ፍሬ ይኼ ነው፡፡ ጾም የፍቅረ ቢጽ እናት ነች የምንለውም ለዚህ ነው፡፡

ስለዚህ ጾማችን እግዚአብሔር የሚፈልገውና የሚቀበለው እንዲኾንልን በጾማችን ወቅት ወጪአችንን መቆጠብ ሳይኾን እነዚህን ድኾች እንድ ናስብ ያስፈልጋል፡፡

(#አምስቱ_የንስሐ_መንገዶች፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ገጽ 71-72 ገብረ እግዚአብሔር ኪደ እንደተረጎመው
1.9K viewsΠαρακαλώ συγχωρήστε μας, 04:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-22 06:52:03 #ጾመ_ነቢያት

እግዚአብሔር አምላካችን ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ መልበሱን፣ ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ወደ ግብጽ ግብር መሰደዱን፣ በባሕረ ዮርዳኖስ መጠመቁን፣ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ማብራቱን፣ ለሰው ልጆች ድኅነት ሲል ልዩ ልዩ ዓይነት መከራ መቀበሉን፣ መሰቀሉን፣ መሞቱን፣ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ ማረጉንና ዳግም ለፍርድ የሚመጣ መኾኑን በአጠቃላይ የማዳን ሥራውን በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው አስቀደመው በትንቢት ተናግረዋል፡፡ ትንቢቱ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው ኾኖ ዓለምን የሚያድንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎትም በእግዚአብሔር ሰው መኾን ፍጻሜ አግኝቷል፡፡

ይህን ምሥጢር በማሰብ በየዓመቱ #ከኅዳር_15 ቀን ጀምሮ እስከ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ዋይዜማ ድረስ እንድንጾም አባቶቻችን መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሠርተውልናል፡፡ ይህ ጾም፣ ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ሲኾን፣ በስያሜም #ጾመ_ነቢያት (የነቢያት ጾም) እየተባለ ይጠራል፡፡ ወቅቱ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ የተፈጸመበት ስለሆነም #ጾመ_አዳም (የአዳም ጾም) ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም #ጾመ_ስብከት (የስብከት ጾም) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ #ጾመ_ልደት (የልደት ጾም) በመባል ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም #ጾመ_ሐዋርያት እየተባለ ይጠራል፤ ምክንያቱም ቅዱሳን ሐዋርያት "በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?" በማለት ነቢያት በጾሙበት ማለት ከልደተ ክርስቶስ በፊት ባለው ወቅት ጾመዋልና፡፡

በሌላ አጠራር ይኸው ጾመ ነቢያት #ጾመ_ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም) በመባል ይታወቃል፤ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያ እና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ተሰወረባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ በዓት ዘግተው፣ ሱባዔ ገብተው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ እግዚአብሔርን ቢለምኑት ልመናቸውን ተቀብሎ ሱባዔ በያዙ በ፫ኛው ቀን የቅዱስ ፊልጶስን ሥጋ (በድን) መልሶላቸው በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት 'ጾመ ፊልጶስ' እየተባለ ይጠራል፡፡

ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው፣ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ካበሠራት በኋላ "ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?" በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ እመቤታችን ጾማዋለችና ይህ ጾም #ጾመ_ማርያም በመባልም ይታወቃል፡፡ በአጠቃላይ በዚህ በጾመ ነቢያት፣ ነቢያትም ሐዋርያትም፣ ቀደምት አባቶቻችንም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባናል፡፡

ጾሙን ጾመ ሥርየት ፤ ጾመ መድኃኒት ያድርግል!

ምንጭ፡–
#ዲያቆን_ኤፍሬም_የኔሰው -ማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ
ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭
3.8K viewsΠαρακαλώ συγχωρήστε μας, 03:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ