Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም ጨረቃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ cherekayechereka — ግጥም ጨረቃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ cherekayechereka — ግጥም ጨረቃ
የሰርጥ አድራሻ: @cherekayechereka
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 246
የሰርጥ መግለጫ

“ዘመመ!” ብላችሁ የሰው ቤት አትግፉ
እሾህ ለማሳመር አበባ አታርግፉ።
እረፍ!
“ቆሜያለሁ!” ለማለት አጥሬን አትደገፍ
ለአመዳም ወዘናህ ቆዳዬን አትግፈፍ።
እረፍ!
በመስመርህ ፍካ በድንበርህ ለምልም
በየአልጋህ እደር በየእንቅልፍህ አልም።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-01-18 19:35:32 Channel photo updated
16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-11 21:31:57 ሞት ቅኔ በሆነበት አለም
ዛሬን ሳይፈቱ የነገን መቃረም
ከራስ ገላ አልፎ የሌላን መሳለም
ከንቱ
ባንድ ትንፋሽ ላንድ ስቅታ
ሳትታይ ለምትወጣ
ይሄሁሉ ገሰስ ይሄ ሁሉ ጣጣ
አጀብ
ነገ ዛሬ ትናንትም እንደ አምና
በሆነበት አለም
ላንዲት ቁራሽ ዳቦ ተይዟል ልመና
ሀሳብ እንደ አራስ ልጅ አጥትንቱ ሳይፀና
በሚቆጠርበት ወሬም እንደ ዜና
ይሄ ሁሉ ጠኔ ይህ ሁሉ መከራ
እግዚኦ
አንተው ምህረት አውርድ
ሞተን ሳንዋረድ
በትናታንት ፀፀት ስንተክዝ
አድነን ማሄር ሻላል ሀሽ ባዝ
ኦሪያ

ማሂታ
607 views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-10 12:19:36
340 views09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-10 12:11:37
322 views09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-08 10:53:52 ምህረት

ነብሴን ድ'ህነት ሰተሀት
ሞቷን እንደሞትክልት
ስጋየም ፈውስ ትሻለች
ከነብሴ ተኮራርፋለች
ግብዝነት ሞልቷታል
ጉልበተኝነት ገዝቷታል
ልክ
ቤት ለመግፋት እንደሚታገል
የፊቱን ጸጋ ለመጣል........
ከኔ ሊሸሽ ይታገለኛል
የምጨብጠው ጠፍቶኛል
ጌታ ሆይ አንተ ብርታቴ ሁነኝ
ያለኝን እኔን ለውጠው
ጸጋ ምህረትን ስጠኝ
ከዛሬየ ጭንቅ ለየኝና
ለጥፋቴ መጨረሻ
ድንበር ስራልኝና
እንዳልጠፋ እንዳልሰወር
ስተክዝ እንዳልደክም
ጠፍቸም እንዳላማርር
ሲከፋኝ ጽናቴን ስጠኝ
ሰው ሲርበኝ አንተ ተገኝ
ሲጨልምብኝ መብራት ሁነኝ
አንቀላፍቸ ተኝቸ እንዳልቀር
የንቃት የእስትንፋሴ በር
እንዳይዘጋ ጌታ አደራ
በምህረትህ ቤቴ እንዲበራ
የራሴ ደግነት ገዝፎ
ከሌላው ጎልቶ ቢታየኝ
አባቴ አንተው መልሰኝ።
beti
331 views07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-17 07:39:27 እንደዚህ ብናስበውስ....

ኤልያስ ሽታኹን
*         *         *        *        *      *      *


*የኖቤል ሽልማት መስራቹ  አልፍሬድ ኖቤል ሞቷል ተብሎ ጋዜጣ ላይ ወጣ፡፡ ሞቷል የተባለው ኖቤል የገዛ የሞቱን ዜና በገዛ ቤቱ ቁጭ ብሎ አነበበው፡፡ የተሳሳተ ዜና ነበር፡፡ ወንድሙ ነበር የሞተው፡፡ ኖቤል ግን ጋዜጣው ላይ የወጣው ርዕሰ አንቀጽ ነበር ያስደነገጠው፡፡
"በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ብዙ ሰዎችን በአንዴ የሚፈጀ ፈጠራ በመፈልሰፍ ሀብታም ለመሆን የበቃው ዶ/ር አልፍሬድ ኖቤል በትናንትናው ዕለት አረፈ"  ይላል ጋዜጣው፡፡

ኖቤል ከዚህ በኃላ  እንቅልፍ አጣ፡፡ ቢሞት ኖሮ ዓለም የሚያስታውሰው በዚህ ስም ነበርና ከነበረበት ቅዠት የተሳሳተው ጋዜጣው አነቃው በዚህም ሳቢያ ዓለም በሰላም እና በደግ በደጉ እንዲያስታውሰው "ኖቤል" ሽልማትን መሰረተ፡፡ ለዓለም እና ለሰው ልጆች መልካም ያበረከቱ የሚሸለሙበት ትልቁ ሽልማት ተባለለት፡፡


እንደዚህ ብናስበውስ

የከተማው ሰዎች የሚሳለቁበት ሰው ቢፈልጉ አንድ ሞኝ አገኙ፡፡  "ከዚያ  ከተራራው ካለው በረዶ በላይ ከሚቀዘቅዘው ኩሬ ለረዥም ሰዓት ከዋኘህ ገጣሚ ትሆናለህ" አሉት፡፡
እሱም ያሉት አደረገ፡፡ ገጣሚ ግን አልሆነም፡፡
ሳቁበት፡፡ ተጠቋቆሙበት፡፡ ቆይቶ ነው እያፌዙበት መሆኑንም ያወቀው፡፡ ሞኝ አይደለ፡፡

አኮረፋቸው፡፡ ተቀየማቸው፡፡ ትቷቸው ሸሸ፡፡ ውሎውን ጫካና ከሸንተረሮቹ ከተራሮቹ አደረገ፡፡ ከሰው ተሸሸገ፡፡
ሲያኮርፋቸው በብቸኝነት ሲከርም ብዙ አሰበ፡፡ አሰላሰለ፡፡

ሲመለስ ወደከተማው የሀገሩ ትልቁ ገጣሚ ሆኖ ነበር፡፡
ገባኝ ያለውን ሲናገር ሁሉ አፉን ከፍቶ ይሰማው ጀመር፡፡ የኢራኑ የግጥም አማልክት መሃል ደረሰ፡፡ ብቸኛ ሲሆን የተመኘውን ሆነ፡፡
* ታላቁ ገጣሚ ባባ ጣሂር፡፡

እንደዚህ ብናስበውስ

* ኦገስት ስትሪንበርግ የተባለው ሰውየ በክፉ ስራው ምክንያት አንድ ምርጥ ደራሲ ለዓለም አበርክቷል፡፡ ያ ክፉ ስራው ምን እንደሆነ በግልፅ የተቀመጠ ነገር የለውም፡፡
ግን የኖርዌው ታላቁ ፀሐፌ ተውኔት እና መራሄ ተውኔት ትልልቅ ድርሰቱን የሚጽፈው የጠላቱን
የ'ኦገስት ስሪንበርግ' ፎቶ ፊት ለፊቱ አስቀምጦ ነበር፡፡ መነሸጫው ማሰላሰያው የዚሁ ሰው ፎቶ ነበር፡፡ የበደለውን ሰውየ እያየ ነበር ብዙ ሀሳብ የሚመጣለት፡፡ ጠላቱ ይነሽጠው ነበረ፡፡
ደራሲ ሄነሪክ ጆሀን ኢብሰን፡፡
"the father or realism" ተብላል በዘመኑ፡፡
(1828 ተወልዶ 1906 ላይ በ78 ዓመቱ አርፏል)

እንደዚህ ብናስበውስ

* በባርነት ዘመኑ ሁሉ ደግ የሚላት የጌታውን ሚስት ነው፡፡ ጌታው ቢጨክንበትም ሚስቱ ግን ታቀርበው ነበርና ፊደል ታስተምረው ነበር፡፡ ይሄንን የደረሰባት ባሏ አብዝቶ ተቆጣት፡፡ "ባሪያ ነው እኮ፡፡ አንቺ ካስተማርሽው ያውቃል፡፡ ካወቀ ይጠይቃል፡፡ ከጠየቅ ባርነቱን ይጠላል፡፡ እና እንዴት ታስተምሪዋለሽ?" ብሎ ተቆጣት፡፡ ለካ ባሪያው ፍሬድሪክ ዳግላስ ከጓዳ ሰምቶ ኖሮ ከጠላቱ ቁጣ የዘላለም ብርሃን በራለት፡፡ "ዕውቀት"
አሻፈረኝ አለ፡፡ ተማረ፡፡ አወቀ፡፡ በጥቁሮች ታሪክ ትልቁ ታጋይ ዳግላስ ተባለ፡፡
(1817-1895 በ78 ዓመቱ አርፏል)


እንደዚህ ብናስበውስ

* አደራ በል ጓደኛው ነው ለዓለም ውለታ የዋለለን፡፡ ታዋቂው ደራሲው ፍራንስ ካፍካ ብቸኝነት ነበር መለያው፡፡ ጥቂት ጓደኞች ብቻ ናቸው የነበሩት፡፡ በሳምባ ነቀርሳ ነው የሞተው፡፡ በአጫጭር እና በረጅም ልብወለዱ ታዋቂ ነው፡፡ የጻፋቸው ስራዎች ሁሉ ተሰብስብስበው እንዲቃጠሉ በኑዛዜው ላይ ተናግሮ ነበር፡፡ ነገር ግን 'ማክስ ብሮድ' የተባለው ጓደኛው አደራውን በላ፡፡ ያለካፍካ ፍቃድ እንዲታተሙ አደረገ፡፡  እንዲነበቡ ዓለም እንዲገረምባቸው ሆነ፡፡ አንባብያን ሁሉ "ይሄን የመሰለ ጽሑፍ ነበር ይቃጠል ያለው" ብለው ካፍካ ላይ ተገረሙበት፡፡ ጓደኛውን በልባቸው አመሰገኑት፡፡
(1883-1924 በ40 ዓመቱ አረፏል)


እንደዚህ ብናስበውስ

* አድባረ ግጥም ጸጋዬ ገብረመድኅን የእናቱ መሬት በጉልበተኞች  መሬት ተነጥቀው አጥር ፈርሶባቸው ከብቶቻቸው ይበተኑባቸው ስለነበር ነው፡፡ እንደልጅ  ይነደው ነበርና ይሄን በህግ ሊያስመልስ በቺካጎ ህግ አጥንቶ መጣ፡፡
ሲመለስ የእናቱ መሬት ብቻ ሳይሆን የሀገሬው ደሀ መሬት ሁሉ በጉልበተኞች ተወርሷልና ትግሉን
ለተበደሉ ድሆች ሁሉ አደረገ፡፡
ያውም በጥበብ አደባባይ፡፡ ያውም በግጥም አደባባይ፡፡ ለእናቱ ፍትሕ የተነሳው ጸጋዬ ወኔ ለእናት ሀገሩ ዘለቀ፡፡
(1928-1998)



*         *       *         *         *        *       *
ዋቢ
* ግሩም የዓለማችን ምርጥ ታሪኮች
ግሩም ተበጀ
*የመንፈስ ከፍታ
በረከት በላይነህ
*ጣዝማ:- አስደናቂው የደራሲያን ሕይወት
ንጉሤ አየለ እና ደጀኔ ጥላሁን
*ሸገር ራድዮ
መቆያ
*ከሕግ ፊት እና ሌሎችም
GOETHE-INSTITUT
*ምስጥረኛው ባለቅኔ
ሚካኤል ሽፈራው
344 views04:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-25 07:35:43 መንጎድ መጓዝ መጥለም...........
ሀሳብ እየመራን ሀሳብን ለመቅደም
@bettacherekaye
@bettacherekaye
@bettacherekaye
473 views04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-21 15:24:24 ሰማዮን ስታይው ይቀል የመሰለሽ
እግዜሩን ከስፍራው ሲመስልሽም ያጣሽ
ፈጣሪን አደለም ልብሽ ነው የጠፋሽ
ጌታ በልባችን ቢታተም ግን ግና
እንኳን ሰማይ ሊቀል ሊመስለን ተላላ
ቅጠልም ይገዝፋል አለው ልዕልና
አትፉሪ
እግዜሩ እግዜር ነው አለ ከመንበሩ
ለኛም ይበጀናል እሱን ማናገሩ
471 viewsedited  12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-21 14:30:28 ቀና ብየ ሳየው ሰማዩ ቀለለኝ
ፈጣሪን ስፈራ ወሰዱት መሰለኝ።

............
@bettacherekaye
@bettacherekaye
@bettacherekaye
448 views11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-12 23:05:40 ህይወት ያሳበደው ማንነቴን ትቼ
ሰው የቋጠረውን ጉንጉኑን ፈትቼ
ቅኔን ከወርቅ ሰሙ በቅጡ ስፈታ
አለም ብትፈቅድልኝ ስናገራት ሰምታ
ከኮኮብ ደምቄ
ከጠፈር ረቅቄ
ብቅ ያሉኝም ጊዜ አንገቴ ሲቃና
ወደ አንተ መጣለሁ ቃል አለብኝና

ማሂታ
485 views20:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ