Get Mystery Box with random crypto!

የሀዘኔ መጨረሻ ክፍል 21 የመጨረሻው ክፍል የሰርጋችንን ቀን መቼም ልረሳው አልችልም፡፡ ሰርጉ | Campus love ❤ Stories

የሀዘኔ መጨረሻ

ክፍል 21 የመጨረሻው ክፍል

የሰርጋችንን ቀን መቼም ልረሳው አልችልም፡፡ ሰርጉ ከተጠናቀቀ በኀላ ወደነ ብሩኬ የምንሄድ መስሎኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ብሩኬ "ሰሊዬ ዛሬ አንድ ቦታ እወስድሻለው ቦታውን ከምልሽ በላይ ነው የምትወጂው" አለኝ፡፡ አቶ ሄኖክ ፈገግ ብለው አንገታቸውን ከፍ ከፍ አደረጉ፡፡ ግራ በመጋባት ስሜት ውስጥ ሆኜ ከብሩኬ ጋር ወደተዘጋጀልን መኪና ገባን፡፡ ወ/ሮ ኤልሳ አቶ ሄኖክና አቤል ወደቤት ሄድ፡፡

እኔና ብሩኬ መንገድ ላይ እየሄድን ብሩኬ መኪናውን ቆም አደረገው "ምነው ውዴ ለምን አቆምከው "ስል ጠየቅኩት እርሱም " ሰላሜ አንድ ሰርፕራይዝ አለሽ ስለዚ አይንሽን በዚ ሸፍኝው " ብሎ ቀይ ሪቫን ሰጠኝ፡፡ ፈገግ እያልኩኝ" ብሩኬ በጣም እየጓጓው ነው እኮ" አልኩት፡፡ "እመኚኝ ሰላሜ ትንሽ ብቻ ታገሺኝ" ብሎ ሪቫኑን አይኔ ላይ አስሮልኝ መንገዳችንን ቀጠልን፡፡ ከትንሽ ጉዞ በኀላ መኪናዋ ቆመች በችኮላ አይኔ ላይ ያለውን ሪቫን ልፈታው ስል "ቆይ ሰላሜ አንዴ " ብሎ አስቆመኝ፡፡ የመኪናውን በር ከፍቶ አሶረደ ኝ፡፡ እጄን ይዞ እየመራኝ ወደ ሆነ ቦታ ወሰደኝ፡፡ "አሁን ሰላሜ አይንሽን መክፈት ትችያለሽ " አለኝ፡፡ እየተጣደፍኩ ሪቫኑን ፈታሁት፡፡

አይኖቼን እንደገለጥኩኝ ያላሰብኩት ነገር ተከሰተ እራሴን መቆጣጠር አቅቶኝ ከአይኖቼ እንባ ዱብ ዱብ አለ፡፡ ብሩኬ ለኔ የሰጠኝ ነገር ከሚባለው በላይ የሚያስፈልገኝና የምወደውን ነገር ነበር.....

የበፊት ቤታችን የውሌ የሰሊ የኔ እና የአቤል እኔና አቤል ተወልደን ያደግንበት የተደሰትንበት ተጣልተን የተታረቅንበት ቤተሰብ ሆነን የኖርንበት ቤት ነበር፡፡ ቤቱ ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ግን ድሮ እኛ ስንኖርንበት እንደነበረ ተደርጓል፡፡ የቤቱ ቀለም አንዳንድ እቃዎቹ በተለይ ሳሎኑ ፊት ለፊት ላይ የተሰቀለው የሙሌና የቤዚ ፎቶ የድሮ ትውስታዎችን ጫረብኝ፡፡

ዘወር ብዬ ብሩኬን አየሁት " ሰላሜ እኔ ወርቆች አልማዞች እንቁዎች ብሰጥሽ እንኳን ከዚኛው ቤት የበለጠ ደስተኛ ሊያደርግሽ አይችልም ነበር፡፡ ይሄ ቤት ላንቺ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አውቃለው ለዛም ነው ይሄን ያደረኩት አንቺ ከዚም በላይ ይገባሻል" ቃላቶች አጠሩኝ የተሰማኝን ስሜት ቃላት አጥቄለት በእንባዬ ገለፅኩት፡፡ ተንደርድሬ ብሩኬን አቀፍኩት፡፡ በሰጠኝ ስጦታ ደስተኛ መሆኔን ሲመለከት ከኔ ይበልጥ ደስተኛ ሆነ፡፡ በፍቅር መኖራችንንም ቀጠልን፡፡

ከወራቶች በኀላ የእርግዝና ወራቶቼን ጨርሼ የምታምር ሴት ልጅ ወለድኩኝ ስሟንም በምወዳት በእናቴ ስም ሰላም አልኳት፡፡ አቤልም እኛጋር መኖር ጀምሯል፡፡ ብሩኬ ሀይለኛ የቢዝነስ ሰው ሆኗል፡፡ አቶ ሄኖክና ወ/ሮ እልሳም እየመጡ ይጠይቁናል፡፡

ዛሬ እሁድ ጠዋት ነው ፀሀይዋ መንፈስን ታድሳለች፡፡ እኔ ብሩኬ ሰላም እና አቤል ቁርስ እየበላን ነው በኑሮዬ በጣም ደስተኛ ነክ ይሄ ነው የኔ ታሪክ የሀዘኔ መጨረሻ.........

........አለቀ..........

ውድ ቸከታታዬቼ ይህንን ታሪክ በተመስጦና በትዕግስት ስለተከታተላቹልኝ አመሰግናለው


Written by Samrawit Teshale