Get Mystery Box with random crypto!

በትላንቱ የአቋም መለኪያ ጨዋታ #ኢትዮጵያ_ቡና 4 - 2 #መከላከያ ሮቤል ተ/ሚካኤል | የቡና ጉዳይ ይመለከተኛል

በትላንቱ የአቋም መለኪያ ጨዋታ

#ኢትዮጵያ_ቡና 4 - 2 #መከላከያ
ሮቤል ተ/ሚካኤል
እንዳለ ደባልቄ
ዊሊያም ሰለሞን እና
ያብቃል ፈረጃ አስቆጥረዋል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር ውድድሮች ከፊታችን መጋቢት 24_2014 ዓ.ም ጀምሮ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርቲ ስታዲየም ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።

ለዚህ ዙር ይረዳው ዘንድ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና መቀመጫውን ለቡ በሚገኘው የተጫዋቾች መኖሪያ ካንፕ አድርጎ ልምምዱን እየሰራ ይገኛል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን በማድረግ ላይ ሲገኝ በዛሬው ዕለት #ከመከላከያ ስፖርት ክለብ ጋር ባደረገው የአቋም መለኪያ ጨዋታ 4-2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

መጋቢት #25_2014 ዓ.ም #ከሲዳማ_ቡና ጋር የመጀመሪያ ውድድሩን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ቡና #መጋቢት_22_2014 ዓ.ም
#ወደ_ውቧ_አዳማ_የሚያቀና_ይሆናል።

@bunawustiawaki
@bunawustiawaki