Get Mystery Box with random crypto!

እናቴ ልዩ ናት ልቧ ሢቀጠቀጥ ደረቷን ደግፋ አንጀቷ ሢታጠፍ ጉልበቷን ደግፉ ምርኩዟ ሢሠበር | Brukti poem❄💖

እናቴ ልዩ ናት

ልቧ ሢቀጠቀጥ ደረቷን ደግፋ
አንጀቷ ሢታጠፍ ጉልበቷን ደግፉ
ምርኩዟ ሢሠበር እንዳይወድቁ ወድቃ
ሠውነቷ ሢዝል ማክሌቷ ሢጠፍ
ብሦቷን በሙዳይ በመላ ቆልፋ
በዘመን ሸራ ላይ
በእንባ ቀለሟ ብዙ ታሪክ ፅፋ
እርሷ ማለት ለኔ ከፈጣሪ በታች
መገደን አስልታ ቀኔን ያሣመረች

እናቴ

ባማንም በምንም የማልተካት ሀብቴ
የኔ ጀግና እርሧነች ልዩ በህይወቴ