Get Mystery Box with random crypto!

' ያንጊዜም ተመልሰው ወደ ምስር ደረሱ ወደ መዓልቃም በዚያ በዋሻ ውስጥ አደሩ እርሷም እስከ ዛሬ | ብራና ሚዲያ BRANA MEDIA

" ያንጊዜም ተመልሰው ወደ ምስር ደረሱ ወደ መዓልቃም በዚያ በዋሻ ውስጥ አደሩ እርሷም እስከ ዛሬ የቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን ናት ። ከዚያም ወጥተው ወደ መጣርያ ደርሰው በውስጧ ታጠቡ ። ይቺም የውኃ ምንጭ አስቀድመን እንደተናገርን ጌታችን ያፈለቃት ከዚያች ሰዓት ጀምሮ የተባረከችና የከበረች ሆነች ። ከዚያም ጌታችን የተከለው የክርስትና ጥምቀት የሚፈጸምበት በለሳን ቅባት የሚወጣው ነው ። በእርሱም ደግሞ አብያተ ክርስቲያናት ንዋየ ቅድሳትና ታቦተ ሕጉም የሚከብርበት ድኅነትም የሚደረግበት ለክርስቲያኖች ሁሉ መመኪያቸው ነው ።"

https://t.me/An_Apocalypse/21471

"እንደዚህ እናመሰግንሃለን ፦ የሁሉ ፈጣሪ ሆይ በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ስለገለጥክልን ሞት ስለሌለበት ስለዚህ ሜሮን መዓዛ ስለዚህ ዘይት እናመሰግንሃለን ፤ ክብር መንግሥት ኃይል ለእንተ ነውና ለዘለዓለሙ አሜን።"
【መጽሐፈ ዲድስቅልያ ፴፮፥፩】

ከቴዎድሮስ በለጠ ከባሌ ጎባ መድኃኔዓለም (ጥቅምት ፳፮ – ፳፻፲፭ ዓ.ም በሀገራችን ለሦስተኛ ጊዜ ሜሮን የማፍላት ሥርዓት ሲፈጸም በ፯ኛው የጸሎት ቀን የተዘጋጀ)