Get Mystery Box with random crypto!

ጤና ይስጥልኝ! በኢትዮጵያ የብሔራዊ ፖሊሲ የውጭ ግንኙነት መርሆዎችን የውቃሉ? 1987 የኢትዮጵያ | የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት

ጤና ይስጥልኝ!
በኢትዮጵያ የብሔራዊ ፖሊሲ የውጭ ግንኙነት መርሆዎችን የውቃሉ?
1987 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት
አንቀፅ 86
1. የኢትዮጵያን ሕዝቦች ጥቅም የሚያስጠብቅና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት የሚያስከብር የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ማራመድ፡፡
2. የመንግስታችን ሉዓላዊነትና እኩልነት ማክበር በሌሎች ሃገሮች ውስጥ ጣልቃ አለመግባት፡፡
3. የሀገሪቱ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በጋራ ጥቅምና በእኩልነት ላይ የተመሠረቱ መሆኑን እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ ስምምነቶች የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ ፡፡
4. የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚያስከብሩና የሕዝቦችዋን ጥቅም የማይፃረሩ ዓለም አቀፍ ሕጎችና ስምምነቶችን ማክበር፡፡
5. ከጎረቤት ሀገሮችና ከሌሎችም የአፍሪካ ሀገሮች ጋር በየጊዜው እያደገ የሚሄድ ኢኮኖሚያዊ ኅብረትና የሕዝቦች ወንድማማችነትን ማጎልበት ፡፡
6. በሀገሮች መካከል የሚነሱ ግጭቶች ሠላማዊ በሆነ መንገድ እንዲፈቱ ጥረት ማድረግ ፡፡

ቸር ይግጠመን !
አሊ ሣፊ (አቃቤ ሕግ)
ሚያዝያ 2014 ዓ.ም