Get Mystery Box with random crypto!

ለመታረቅ እንዲመቸን አርገን ሳንጣላ _' ታመምን' በስብሶ የወደቀን ጣልን _አልን . ምን እንደም | @Book for all

ለመታረቅ እንዲመቸን አርገን ሳንጣላ _' ታመምን'
በስብሶ የወደቀን ጣልን _አልን
.
ምን እንደምፈልግ ራሱ_- _ እየፈለኩ
ሲበዛ በጥቁር ክንፎችሽ -__- ታከኩ
.
(አመመኝ)
ለአሁን ግን እኔን ለኔ ተይኝ !
.
.
በህይወት እንድንቆይ የሚረዱን ውሸቶች
ገነትን ለመፍጠር የምንሄደው ሲኦሎች __ገዝፎብናል
ከአንዳንድ 'እንዴት ነህ' ዎች
የወዳጅ 'እግር ብላዎች 'ዎች __በልጦብናል
.
.
.
ለሃዘን የተፈጠርን ይመስል
በንፉግ ልቦች የምንቆስል _ ስለምን ?
ይችን ታህል ከሞት ይበቃል
ከመውደቃችን በላይ _ በውድቀት መፎካከራችን ይሰቃል .
.
(እኔን ለኔ ተይኝ ).
.
ከፆታዬ በስተቀር በነገሮች እርግጠኛ አይደለሁም
ቅዠት ምን መልክ አለው ? _ ህልሜን ካንቺ አላየሁም
.
(አንዳንዴም)
.
ከስቃዩ ይልቅ የመሃል ተስፋው ነው የሚጎዳን
እኔን ተይኝ __-_ ይችን ታህል አብረን ከሞትን ይበቃል !
.
.
@Bookfor
@Bookfor