Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ሽማግሌ ወደ አንድ የሞባይል መጠገኛ ሱቅ ሄዱና 'ስልኬ ተበላሽቷል ስራልኝ' ብለው ሰጡት። ሞ | @Book for all

አንድ ሽማግሌ ወደ አንድ የሞባይል መጠገኛ ሱቅ ሄዱና "ስልኬ ተበላሽቷል ስራልኝ" ብለው ሰጡት። ሞባይል ጠጋኙ ስልኩን አገላብጦ ከፈተሸው በኋላ "አባባ ስልክዎ እኮ ምንም አልሆነም ፤ይሰራል" አላቸው ሽማግሌው አይናቸው እንባ አቀረረና......."ስልኩ ካልተበላሸ...... ልጆቼ የማይደውሉልኝ ለምንድነው? አሉ በደከመ ድምጽ።

ለወላጆቻቸን የምናደርገው ትልቁ ስጦታ ቢኖር በቂ ጊዜ መስጠት ብቻ ነው። የመኖራችን ትርጉም የሚገባን ሲለዩን ነው። እድለኛ ሆነን ወላጆቻችን በህይወት ካሉ እንከባከባቸው። እርቀንም ከሆነ እንደውልላቸው። ይሄን ያህል አመት ጊዜ ሰጥተው እንዳሳደጉን እኛም ጊዜ አንስጣቸው።

ለወላጆቻችን እንዲሁም ለአሳዳጊዎቻችን ፍቅር እና ጊዜ እንስጣቸው !!!

ይህን መልክት ከሁለት አመት በፊትም አንብቤዋለሁ ግን ሁሌም ደጋግሜ ሳነበው ልቤን ስለሚነካኝ እኔም ደግሜ ላካፍላችሁ ወደድኩ።

𝙰𝙷𝙰𝙳𝚄
@Bookfor
@Bookfor