Get Mystery Box with random crypto!

“የባሕል እሴቶቻችን ለአንድነታችን መጠናከር!” የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባሕል ኪነጥበብና ቱ | ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

“የባሕል እሴቶቻችን
ለአንድነታችን መጠናከር!”
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባሕል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ “ባሕሎቻችን ለአንድነታችን ካስማ” በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው 14ኛው ከተማ አቀፍ የባሕል ሳምንት ተጀመረ፡፡
ከጥር 26 እስከ ጥር 28 ቀን ድረስ ለሦስት ቀናት በሚካሄደው በዚህ የባሕል ሳምንት ላይ አሥራ አንዱም ክፍለ ከተሞች የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችን ባሕል በመወከል ተሳታፊ ሲሆኑ፣ የቦሌ ክፍለ ከተማም የሶማሌ ብሔር ባሕልን በማስተዋወቅ ላይ እንደሚገኝ እና እስከመጪው እሁድ ድረስም የክልሉን ልዩ ልዩ ባሕላዊ እሴቶች በባሕል ሳምንቱ ላይ እንደሚያስተዋውቅ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ባሕል ኪነጥበብና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ራቢያ ያሲን አስታውቀዋል፡፡
ጥር 26/2015