Get Mystery Box with random crypto!

በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር  ከተማ  በ90 ቀናት ዕቅድ በመከናወን ላይ ባሉ ሥራዎች የመስክ ምል | ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር  ከተማ  በ90 ቀናት ዕቅድ በመከናወን ላይ ባሉ ሥራዎች የመስክ ምልከታ ተካሔደ፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ የተመራ የከተማና የክፍለ ከተማው አመራሮች ቡድን በክፍለ ከተማው ወረዳ 1 እና 3 ባደረገው ጉብኝት በየወረዳዎቹ በመከናወን ላይ የሚገኙ የከተማ ግብርናና የአረንጓዴ ልማት እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥ ምልከታ የተደረገባቸው ሲሆን፣ ሥራዎች በፍጥነት እንዲከናወኑና ጊዜ እንዳይወስዱ  የአጭር ጊዜ ዕቅድ በማቀድ ሁልጊዜ መከታተልና  የማኅበረሰቡን ጥያቄዎች ወርዶ በማዳመጥ  በዕቅድ አካትቶ  ምላሽ መስጠት እንደሚገባ አቶ ጥራቱ  አስታውቀዋል፡፡ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ዓለምፀሃይ ሺፈራው በበኩላቸው አስተዳደሩ  ሥራዎች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በየጊዜው ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል ፡፡
ጥቅምት 25/2015