Get Mystery Box with random crypto!

Bank of Abyssinia

የቴሌግራም ቻናል አርማ boaeth — Bank of Abyssinia
ርዕሶች ከሰርጥ:
Telegram
Contest
Giveaway
Ethiopia
Boa
Bankofabyssinia
Bankinginethiopia
Banksinethiopia
Banking
Holiday
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @boaeth
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 171.06K
የሰርጥ መግለጫ

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2024-04-17 15:00:58
እንኳን ደስ አላችሁ!!
ባንካችን አቢሲንያ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ እ.ኤ.አ. በማርች ወር ላይ ባካሄደዉ የሴቶች የተሰጥኦ ዉድድር ላይ ተሳትፈዉ ያሸነፉ ተወዳዳሪዎች ተለይተዋል፡፡
በድምፅ ዉድድር ተሳትፈዉ ከነበሩት ተወዳዳሪዎች በአንደኛነት በአምላክ ጌትነት መወዳደሪያ ኮድ (M2) (100,000) የአንድ መቶ ሺ ብር ተሸላሚ በሁለተኛነት ኢትዮጵያ ኢሳያስ መወዳደሪያ ኮድ (M6) (75,000) ሰባ አምስት ሺ ብር ተሸላሚ እንዲሁም በሶስተኛነት ብሩክታዊት ቱጂ መወዳደሪያ ኮድ (M5) (50,000) ሀምሳ ሺ ብር ተሸላሚ በመሆን ያሸነፉ ሲሆን ዳኝነቱም የተካሄደዉ በያሬድ ትምህርት ቤት መምህራን እና በተመልካች ምርጫ ነበር፡፡
በቲክ ቶክ በነበረዉ ዉድድር ደግሞ በአንደኛነት ሜርሲ የቲክቶክ ስም (@enun088 ) (100,000) የአንድ መቶ ሺ ብር ተሸላሚ በሁለተኛነት ካልኪዳን የቲክቶክ ስም (@kal.baba10) (75,000) ሰባ አምስት ሺ ብር ተሸላሚ እንዲሁም በሶስተኛነት ያይኔአበባ የቲክቶክ ስም (@yayne_a ) (50,000) ሀምሳ ሺ ብር ተሸላሚ በመሆን ለማጠናቀቅ ችለዋል፡፡
የመዝጊያ መርሀግብራችንንም በቅርቡ የምናከናዉን ሲሆን ተወዳዳሪዎችን በድጋሚ እያመሰገንን አሸናፊዎችን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡
18.4K views12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-12 15:02:25
አዲሱን የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ በመጠቀም ደንበኞች እንዴት ወደ አዋጭ አካውንት ገንዘብ ማስተላለፍ ይችላሉ?
ሊንኩን በመጠቀም መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ!

ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.boaMobileBanking&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች  https://apps.apple.com/us/app/boamobile/id6463218765

ለሁዋዌ ስልኮች https://appgallery.huawei.com/app/C110106115
#BankofAbyssina #mobilebanking #boamobile #bankinginethiopia #banksinethiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
17.3K views12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 15:00:44
ባንካችን ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡
ኢድ ሙባረክ!
አቢሲንያ አሚን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት
ዕሴትዎን ያከበረ!

بنك أبيسينيا يهنئكم بحلول عيد الفطر المبارك
 وكل عام وأنتم بخير
#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia
#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
18.1K viewsedited  12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-05 15:01:48
በቅርቡ!


#bankofabyssinia #Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
18.0K views12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-03 15:00:57
አፖሎ የገንዘብ እንቅስቃሴዎ ያለ ድካም እና እንግልት የሚያቀላጥፉበት መተግበሪያ ነው። ጊዜ ሳያጠፉ ህይወትዎን ያቅልሉ።
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።

ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች https://apps.apple.com/us/app/apollo-digital/id1601224628

#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
17.2K views12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-30 10:14:23
18.5K views07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-30 10:13:36 ባንካችን አቢሲንያ የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ በአቢሲንያ አሚን በኩል የተለያዩ ኢፍጣር ፕሮግራሞችን አካሄደ።

ባንካችን አቢሲንያ የ2016 ዓ.ም. የረመዳን ጾምን ምክንያንት በማድረግ በአቢሲንያ አሚን በኩል በተለያዩ የሀገራችን ቦታዎች ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጋር የኢፍጣር ፕሮግራም አካሂዷል።
የኢፍጣር ፕሮግራሞቹ በዋናነት የተካሄዱት በአምስት የባንካችን ዲስትሪክቶች ሥር ሲሆን፣ በባህርዳር፣ ሐዋሳ፣ ድሬዳዋ፤ ምሥራቅ አዲስ ዲስትሪክት እንዲሁም በደሴ ዲስትሪክት የሚገኙበት ሲሆን፤ በደሴ ዲስትሪክት ከተለያዩ ቦታዎች ተፈናቅለው በሎጊያ ከተማ ለሚገኙ ወገኖቻችን በኢማን ኢስላሚክ አሶሴሽን በኩል ለማፍጠሪያ የሚሆኑ ምግቦችን በአይነት በመግዛት ለተፈናቃዮቹ አበርክቷል።
የ ባንካችን ባህርዳር ዲስትሪክት በኩል በቻግኒ ከተማ የሚገኙ ምስኪኖችንና ከተለያዩ የሀገራችን ክፍል ተፈናቅለው በከተማዋ ተጠልለው ከሚገኙ ወገኖቻችን ጋር በመስጊድ ራህማን ኮሜቴዎች አማካኝነት በዕለቱ የሩዝ፣የዘይትና ፍየል ድጋፍ በማድረግ ያስፈጠረ ሲሆን፣ በተጨማሪም በጎንደር ከተማ በሚገኘው ነጃሺ መስጊድ በተካሄደው የኢፍጣር ፕሮግራም ላይም ተሳትፏል።
በተጨማሪም፡-
የሐዋሳ ዲስትሪክት አመራሮች ከሀላባ ፣ ከሻሸመኔና ይርጋ ጨፌ ከተማ ደንበኞቻችን ጋር የኢፍጣር ፕሮግራም በማዘጋጀት እንዲሁም ቤት ለቤት በመሄድ የኢፍጣር ፕሮግራም አከናውነዋል። በተጨማሪም የዲስትሪክቱ አመራር አባላትና ሠራተኞች የእርስ በርስ ትስስርና ትብብራቸውን ለማጠናከር በጋራ የአፍጥር ፕሮግራም አዘጋጅተው ያሳለፉ ሲሆን እንዲሁም፤-
የባንካችን ምሥራቅ አዲስ አዲስትሪክት በቦሌ ጃዕፋርና ጡሩ ሲና መስጊዶች እና በአያት ጣፎ ዳሩል ሠላምና በሲኤሲ አላምራን መስጊዶች ለምስኪኖች በተዘጋጀ የኢፍጣር ፕሮግራሞች ላይ የዱቄት፣ ዘይት፣ ቴምርና እሽግ ውሃ ድጋፍ በማድረግ ተሳትፏል። በተጨማሪም የዲስትሪክቱ አመራሮችና ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች በወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን የኢፍጣር ፕሮግራም ላይ ድጋፍ በማፍረግ የተሳተፉ ሲሆን የምስራቋ ፈርጥ የሆነችው ከተማም ድሬዳዋ ዲሰትሪክት በሐረር ከተማ ሐረር አራተኛ ኢማሙ አሕመድ እና መስጂድ ጃሚዕ በኩል ለተደረጉ የኢፍጣር ዝግጅቶች ተሳታፊ ሆነዋል።
በአጠቃላይ ባንካችን ታላቁን የረመዳን ፆም ምክንያት በማድረግ ከላይ ከተጠቀሱት ቦታዎች በተጨማሪም በሌሎችም ቦታዎች ከእስልምና እምነት ተከታይ ደንበኞቹና ሙስሊም ማኅበረሰቡ ጋር ወሩን በጋራ እያሳለፈ መሆኑን እየገለጽን፣ መልካም የረመዳን የፆም ወራት እንዲሆንላችሁ ይመኛል።
18.3K views07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-29 15:04:18
ማርች 8 የሚከበረውን የሴቶች ቀን አስመልክቶ ሴት ባለተሰጥኦዎችን በማሳተፍ በባንካችን ሲካሄድ የነበረው የ “እችላለሁ” 3ኛ ዙር ሙዚቃ ውድድር የተጠናቀቀ ሲሆን ለውድድሩ ከቀረቡት የሙዚቃ ስራዎች ውስጥም አስር ስራዎች በባለሙያዎች ተገምግመው ለመጨረሻው የታዳሚዎች ምርጫ የተለዩ ሲሆን፣ የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት መምህራን የሆኑት የሹምነሽ ታዬ ፣ ሜሮን ረጋሳ እንዲሁም ሰላማዊት አራጋዉ የሙዚቃ ስራዎችን በመገምገም ስራ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ በቀጣይም ከሙዚቃ ዘርፍ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የሚወጡት ባለተስጥኦዎች በአድማጭ ድምፅ 30% ፣እንዲሁም በዳኞች 70% ነጥብ የሚለዩ ይሆናል፡፡
በመሆኑም በመጀመሪያ ዙር የተለዩት አስር የሙዚቃ ስራዎች ከዚህ ጋር ተያይዘው የቀረቡ በመሆኑ ከዛሬ መጋቢት 20 እስከ መጋቢት 23 ቀን 2016 ባለው ጊዜ ውስጥ ይህን የፌስቡክ ሊንክ https://www.facebook.com/share/v/wSpQRyEDry49Pf6Z/?mibextid=WC7FNe በመጠቀም በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የሚገኘውን መለያ ኮድ በመጠቀምና የመረጣችሁትን በፌስቡክ ኮመንት ሥፍራ ላይ በመፃፍ የድምፅ አሰጣጥ ተሳትፎ እንድታደርጉ እንጋብዛለን፡፡
መልካም ዕድል ለተሳታፊዎች!
22.7K views12:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-27 15:34:24
ባንካችን ለሴትና ወጣት ጥቃቅን አነስተኛና መካከለኛ ንግድ ባለቤቶች የሥራ ማስኬጃ ብድር አገልግሎት መርሀ-ግብር እየተገበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ መርሃ-ግብሩ ከአዲስ አበባ ውጪ በመላው ሀገሪቱ የሚተገበር ነው፡፡
አመልካቾች ለማመልከት ከታች ለተጠቀሱት መሥፈርቶች ተያያዥ
ሰነዶች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አነስተኛ ንግድ ያላቸው ወጣቶችና ሴቶች
- የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ቢያንስ ለአንድ ዓመት በንግድ ሥራ ላይ ያሉ (ለጀማሪዎች 6 ወር)
- በግብርና እና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ የተሠማሩ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል
-በመጠነኛ ዋስትና እና በዝቅተኛ ወለድ
-የታክስ ሰነድ(ቲን)
-መታወቂያ
-የንግድ ስፍራውን የሚያሳይ ፎቶ
ለብድሩ ለማመልከት በአቅራቢያችሁ የሚገኙ ቅርንጫፎቻችንን ይጎብኙ፡፡
#loan#MSME #smallbusiness #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
18.3K viewsedited  12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-22 15:02:09
ባንካችን አቢሲንያ የአለም አቀፉን የሴቶች ቀን ማርች 8 በማስመልከት ለ 3ኛ ግዜ “ እችላለሁ “ በሚል መሪ ቃል ልዩ ልዩ ዉድድሮችን ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 21 እያከናወነ ይገኛል፡፡ በዚህ መርሀ ግብር ላይ በግጥም፣ በሙዚቃ፣ በቲክቶከሮች መካከል የሚደረግ ዉድድር የሚከናወን ይሆናል፡፡ ከዚህ በፊት ባንኩ በሁለት ዙር ባከናወናቸዉ የ “ እችላለሁ “ ዘመቻ በመጀመሪያዉ ዙር ለ 27 የስራ ፈጣሪ ሴቶች ለእያንዳንዳቸዉ 300,000 (ሶስት መቶ ሺ ብር ) በሁለተኛዉ ዙር ደግሞ ለ 50 የስራ ፈጣሪ ሴቶች ለእያንዳንዳቸዉ 500,000 (አምስት መቶ ሺ ብር ) በዝቅተኛ ወለድ ያለመያዣ ብድር አዘጋጅቶ ለባለእድለኞች መስጠቱ ይታወሳል፡፡
በዚህ ዙርም በተመሳሳይ ለ 50 የስራ ፈጣሪ ሴቶች ለእያንዳንዳቸዉ 500,000 (አምስት መቶ ሺ ብር ) ያዘጋጀን ሲሆን መስፈርቱን የምታሟሉ ሴቶች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡ ከባለፈው ዓመት የእድሉ ተጠቃሚዎች መካከልም ሁለቱ አሸናፊዎች ያሉትን ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡
ዝርዝር የብድር እንዲሁም የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ከዚህ በታች የሚገኘውን የቴልግራም ሊንክ ያግኙ፡፡
https://t.me/BoAEth/1146
#march8 #womansday #ican #Savings #enterpreneur
#BankofAbyssinia #Abyssinia #Banking #BankingService #Digital #DigitalEthiopia #DigitalPayment #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
19.2K views12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ