Get Mystery Box with random crypto!

ዓመታዊው “Dine-and-Learn with your CEO” መርሃ ግብር በተለያዩ ኩነቶች ታጅቦ በከ | Bank of Abyssinia

ዓመታዊው “Dine-and-Learn with your CEO” መርሃ ግብር በተለያዩ ኩነቶች ታጅቦ በከፍተኛ ድምቀት ተካሄደ።
//
ባንካችን አቢሲንያ፣ በአዲስ ዓመት መባቻ መስከረም 5 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ለሁለተኛ ጊዜ “Dine-and-Learn with your CEO” ዓመታዊ መርሃ-ግብር እጅግ በደመቀ ሁኔታ አካሄደ።
በዝግጅቱ ላይ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዲስትሪክት የስራ ኃላፊዎች፣ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ የቅርንጫፍ ሥራ-አስኪያጆች፤ የተሸላሚ ቤተሰቦች፤ እንዲሁም በፕሮግራሙ ላይ የማነቃቂያ ንግግር እንዲያደርጉ የተጋበዙት ዶ/ር ወዳጄነህ መሃርነን ጨምሮ በርካታ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
በዝግጅቱ እና በአይነቱ ረገድ በደመቀው በዚህ መድረክ፤ በ2021/22 የበጀት ዓመት በአፈፃፀም ከፍተኛ ዉጤት ላስመዘገቡት 56 ቅርንጫፎች የዕውቅና ምስክር ወረቀት የመስጠት ስነ-ስርአት ተከናዉኗል።
በተለይም በአፈጻጸማቸዉ እጅግ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 26 ቅርንጫፎች እና ከ1-3ኛ ለወጡ ዲስትሪክቶች፤ እንዲሁም በልዩ ሁኔታ የደሴ ዲስትሪክትን ጨምሮ ለ8 ቀናት የውጭ ሃገር ስልጠና ዕድል ተመቻችቶላቸዋል።
የባንካችን አቢሲንያ መገለጫ እየሆነ በመጣው “Dine-and-Learn with your CEO” ደማቅ ሥነ-ሥርዓት ላይ የባንካችን ዋና ሥራ-አስፈፃሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ ’’Strategy Workshop’’ በሚል ርዕስ ያላቸዉን ጥልቅ እዉቀትና ተሞክሮ ከባንካችን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ጋር አያይዘዉ ለታዳሚዎች በስፋት አካፍለዋል።
በሌላ በኩል የእለቱ የማነቃቂያ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ወዳጄነህ ማህርነ፣ አቢሲንያ ባንክ በከፍተኛ እድገት ላይ ያለ ባንክ መሆኑን በመግለጽ ንግግራቸዉን የጀመሩ ሲሆን አክለዉም የህይወት መርሆች ወይም principles of life በሚል መሪ ቃል እዉቀታቸዉን ለመድረኩ አካፍለዋል።
ለአንድ ቀን በተካሄደው በዚህ የልምድ ልውውጥ መድረክ ላይ በርካታ የተሸላሚ ቤተሰቦች ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን ሁሉም ቤተሰቦች በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ሙሉ ወጪያቸውን ባንካችን አቢሲንያ በመሸፈን ቆይታ አድርገዋል።
በአጠቃላይ የፕሮግራሙን ይዘት በተመለከተ ሁሉም ተሳታፊዎች ደስተኛ የነበሩ ሲሆን በተለይም የተወዳዳሪነት መንፈስ በመፍጠር ረገድ ለባንካችን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለዉ መሆኑን አጽኖት በመስጠት ወደፊት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በዝግጅቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ሠራተኞች እና የትዳር አጋሮች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ፕሮግራሙ ያማረና የደመቀ ይሆን ዘንድ አስተዋጽኦ ላደረጉ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች እና የስራ ክፍሎች ምስጋና በመቸር እንዲሁም መልካም አዲስ ዓመት ይሆን ዘንድ በመመኘት አመታዊዉ የደመቀዉ መድረክ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!