Get Mystery Box with random crypto!

ብስራት ሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ bisrat_midea — ብስራት ሚዲያ
የቴሌግራም ቻናል አርማ bisrat_midea — ብስራት ሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @bisrat_midea
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 307
የሰርጥ መግለጫ

"ሰላም ለኪ ቅድስት ቤተክርስቲያን አምሳለ እየሩሳሌም ሰማያዊት"
ይህ ቻናል የተከፈተው ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን መረጃ የምንለዋወጥበት በዓይነቱ፣ በይዘቱ ለየት ያለ ቻናል በይፋ ከፍቻለሁ።
በዚህ ቻናል👇👇👇
✔ ፎቶዎችን
✔ቪዲዮችን
✔መፅሐፍትዎችን
✔ታሪኮችን ታገኙበታላችሁ።👇👇
Http://Telegram.me/Bisrat_Midea
Http://tiktok/@bisratman20

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-02-11 22:19:54 #የካቲት_5

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
የካቲት አምስት በዚች ቀን የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባት #ቅዱስ_አክርጵዮስ አረፈ፣ አባት ጴጥሮስ የተባለ #አባ_ብሶይ አረፈ፣ አስቀድሞ ራሱን ለኃጢአት አስገዝቶ የነበረ ጽኑዕ ተጋዳይ #አባ_ዕብሎይ አረፈ፣ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ጻድቃን #አቡነ_አሞኒ የተወለዱበት ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አክርጵዮስ

የካቲት አምስት በዚች ቀን የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባት አክርጵዮስ አረፈ። እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ዐሥረኛ ነው።

ይህም አባት እግዚአብሔርን የሚፈራ ንጹሕ ቅዱስ ነው ። በእስክንድርያ አገርም ቄስ ሁኖ የሚያገለግል ነበር ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ከላድያኖስ በአረፈ ጊዜ የእስክንድር አገር ሕዝቡና ኤጲስቆጶሳቱ መረጡት በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበርም ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።

ከዚህም በኋላ እንደ ሐዋርያት መልካም ጉዞን ተጓዘ የእግዚአብሔርን ሃይማኖት ሕይወት የሆነ ሕጉንም እያስተማረ ቅዱሳት መጻሕፍትንም እያነበበላቸውና እያስተማራቸው መንጋዎቹን ይጠብቃቸው ነበር ሁል ጊዜም ይመለከታቸዋል አንድ የብር አላድን ወይም አንድ የወርቅ ዲናርን ጥሪት አላኖረም ከዕለት ምግቡ ከቁርና ከሐሩር ሥጋውን ከሚሸፍንበት ልብስ በቀር ምንም አላከማቸም።

በዚህም ተጋድሎ ዐሥራ ሁለት ዓመት ኑሮ ጌታችንንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ብሶይ

በዚችም ዕለት ተጋዳይ የሆነ አባት ጴጥሮስ የተባለ አባ ብሶይ አረፈ እርሱም ከላይኛው ግብጽ አክሚም ከሚባል ከተማ ነው። በጐልማሳነቱም ጊዜ የከፉ ሥራዎችን የሚሠራ ሁኖ ነበር በመብላትና በመጠጣትም ይደሰት ነበር። እግዚአብሔርም የነፍሱን ድኅነት ሽቶ ጽኑ ደዌ አመጣበትና ለመሞት ተቃረበ።

ነፍሱንም በተመሥጦ አውጥተው የሥቃይ ቦታዎችንም ጥልቅ የሆነች ጕድጓድንም አሳዩት፡፡ በዚያም ብሩህ ልብስ የለበሱ ሰዎች አሉ በእጆቻቸውም የሰው በድን ነበረ አራት ክፍል አድርገው ለያዩትና የሰውን ገንዘብ የሚሰርቀውን ሁሉ እንዲህ ያደርጉበታል አሉት። ይህንንም ነገር በሰማ ጊዜ ጮኸ ከልቡም አዝኖ አለቀሰ ከዚህም በኋላ ነፍሱ ተመለሰች ዐይኖቹንም ወደ ሰማይ አቅንቶ ጌታዬና ፈጣሪዬ ከዚህ ደዌ ከአዳንከኝ እኔ ስለ ኃጢአቴ ንስሐ በመግባት በፍጹም ልቡናዬ አመልክሃለሁ ከእንግዲህም ከቶ ለዘላለሙ የሴት ፊት አላይም አለ።

በዚያንም ጊዜ ከደዌው አዳነውና ተነሥቶ ብንዋይ ወደሚባል ገዳም ሔደ መነኰሳቱም ከፈተኑት በኋላ የምንኲስናን ልብስ አለበሱት በግብጽ አገር ሁሉ እስከሚሰማ ታላቅ ተጋድሎን በጾም በጸሎት በመስገድም ተጋደለ ከሁሉ በላይም ከፍ ከፍ አለ ለመነኰሳትም ትምህርት የሚሆኑ የሚጠቅሙ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ አንድ ጊዜም እንጀራ ሳይቀምስ ውኃ ሳይጠጣ አንድ ወር ጾመ እንዲህም እየተጋደለ ሠላሳ ስምንት ዓመት ያህል ኖረ።

መላዋንም ሌሊት በጸሎትና በስግደት በመትጋት ቁሞ ያድራል ሰዎች የሚሠሩት ሁሉ ጻድቅም ቢሆን ኃጢአተኛም ቢሆን በፊቱ ግልጥ ሆነ ከዚህም በኋላ ጥቂት ታመመና በሰላም አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባ_ዕብሎይ_ገዳማዊ

በዚህችም ቀን አስቀድሞ ራሱን ለኃጢአት አስገዝቶ የነበረ ጽኑዕ ተጋዳይ አባ ዕብሎይ አረፈ። ይህም የበጎች አርቢ ራሱን ለሰይጣን በማስገዛት ከኃጢአት ሥራ ምንም የቀረው የለም ያመነዝራል ይሰርቃል ይቀማል ይገድላል በዚህም የሰይጣንን ሥራ እየፈጸመ አርባ ዓመት ያህል ኖረ።

በአንዲትም ዕለት ከቀኑ እኩሌታ ከበጎቹ ጋር በዱር ውስጥ ሳለ እነሆ የመውለጃዋ ጊዜ የደረሰ ያረገዘች ሴትን አየ ሰይጣንም በልቡ ክፉ ሐሳብን ጨመረ እንዲህም አለ የተረፈችኝ ኃጢአት አንዲት አለች እርሷም ያረገዘች ሴት ሆዷን ሠንጥቄ በእናቱ ሆድ ሕፃኑ የሚተኛበትን አይ ዘንድ ነው።

ያን ጊዜም ተወርውሮ ሔደ በራስዋ ጠጕር ይዞ ከምድር ላይ ጣላት ሾተልም አንሥቶ ሆዷን ሠነጠቀ ሕፃኑንም በማሕፀኗ ውስጥ እንዴት ሁኖ እንደተኛ አየው እርሷም በጻዕር ተጨንቃ አስቀድማ ሞተች ሕፃኑ ግን በጻዕር እየተሠቃየ ብዙ ቆይቶ ሞተ። በግ አርቢውም የሠራውን ይህን ታላቅ ኃጢአት ተመልክቶ ደነገጠ እጅግም አዘነ መራራ ልቅሶንም በማልቀስ ታላቅ ኃጢአትን ሠርቻለሁና ወዮልኝ አለ።

በዚያንም ጊዜ በጎቹን እንደተበተኑ ትቶ በእጁ በትሩን ብቻ ይዞ ወደ አስቄጥስ ገዳም እስከሚደርስ እያለቀሰ ተጓዘ ወደ አረጋውያን መነኰሳትም አልገባም ከእርሳቸው ዐሥር ምዕራፍ ያህል ርቆ ወደ በርሀ ውስጥ ገባ እንጂ በቤት ውስጥም አያድርም ነበር ከአራዊት ጋር የሚኖር ሆነ እንጂ ከዕፀዋትም ፍሬ በየጥቂቱ ይመገብ ነበር ከዕንባ ጋርም እየጮኸ አቤቱ በደልኩ ክፉ ሥራንም ሠራሁ ይቅር በለኝ እኔ ኃጢአተኛ የሆንኩ ክፉ ባርያ ነኝና አንተም ቸር አምላክ ይቅር ባይ አባት ነህና የማይበድል ባሪያ የማይምር ጌታ የለምና ይቅር በለኝ እንዲህም እየተጋደለ አርባ ዓመት ኖረ።

ከሌሊት ቍር ከቀን ፀሐይ ሐሩርና ትኩሳት የተነሣ ሥጋው ደርቆ ጠቆረ ከዚህም በኋላ እንዲህ የሚለውን ቃል ሰማ ስለ ሴቲቱ ደም ጌታ ይቅር ብሎሃል ጽና በርታ ይህንንም ያለው እንዳይታክትና ዳግመኛ በኃጢአት ውስጥ እንዳይወድቅ ነው።

ይህንም በሰማ ጊዜ ከሦስት ቀን ብቻ በቀር ያቺን ዓመት እስከሚፈጽም መሪር ልቅሶ እያለቀሰ ተጋድሎውን ጨመረ እነሆ የእግዚአብሔር መልአክ ከእርሱ ዐሥራ አምስት ምዕራፍ ያህል ርቆ የሚገኝ ከቶ ሰውን ሳያይ በዚያች በረሀ ሰባ ዓመት የኖረውን አንዱን ገዳማዊ አንተ ካለህበት ቦታ ወደ ውጭ ሒድ ሽማግሌ ሰው ታገኛለህ ኃጢአቱን ከአመነልህ አጽናናው ኃጢአትህ ሁሉ ስለ ሕፃኑም መገደል ተሠርዮልሃል በለው በማለት አዘዘው።

በዚያንም ጊዜ ያ ገዳማዊ ሒዶ አገኘው አርስበርሳቸውም ሰላምታ ተሰጣጡ እርሱ ዕብሎይ ግን ያለማቋረጥ ያለቅስ ነበር ገዳማዊውም የሠራኸውን ንገረኝ በምን ምክንያትስ ወደዚህ መጣህ አለው። እርሱም ሁሉንም ነገረው ያረገዘችዋንም ሴት ሆድዋን እንደሠነጠቀ ነገረው ገዳማዊውም ኃጢአትህ ሁሉ ተሠርዮልሃል አባቴ ሆይ ደስ ይበልህ ነገ የእግዚአብሔር መልአክ ወዳንተ መጥቶ የክርስቶስን ሥጋና ደም ያቀብልሃል አለው።

የቀዳሚት ሰንበት ዕለትም በነጋ ጊዜ ከቶ እንደርሱ ሁኖ የማያውቅ ጣፋጭ ሽታ ሸተተ አባ ዕብሎይም ገዳማዊውን አባቴ ሆይ ከፍርሀት የተነሣ ነፍሴ ከሥጋዋ ልትለይ ደረሰች አለው ይህንንም ባለ ጊዜ በመነኰስ አምሳል ከአጠገቡ ቁሞ መልአኩን አየው እርሱም ተቸገርኩ እግዚአብሔርም አዳነኝ:: ነፍሴ ሆይ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሽ:: እግዚአብሔር ረዳትሽ ነውና፡፡ ነፍሴን ከሞት አድኗታልና። ዐይኖቼንም ከእንባ እግሮቼንም በዳጥ ከመሰናከል። በሕያዋን አገር እግዚአብሔርን አገለግለው ዘንድ እያለ ይዘምር ነበር።

የበጎች ጠባቂ የነበረ አባ ዕብሎይም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ በምድር ላይ ወድቆ እንደ በድን ሆነ መልአኩም በሰው አምሳል እጁን ዘርግቶ አነሣው ልቡም ጸንቶ በመልአክ እጅ ከሰማይ የወረደለትን ሥጋውንና ደሙን ተቀበለ መልአኩም ወደ ሰማይ ዐረገ።

አባ ዕብሎይም ቍርባኑን በተቀበለ ጊዜ ሰውነቱ ሁሉ እንደ በረድ ፀዓዳ እንደ ፋናም ብሩህ ሆነ በዚያችም ዕለት ሁለቱም ደስ እያላቸው እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ እስከ ማታ ዋሉ።
84 viewsBisrat, 19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 12:48:22 በመጨረሻም ቅዱስ ሲኖዶስ በጀመረው ፍጹም ሰላማዊ ና ሕጋዊ መንገድ ከመንግሥት ጋር የደረስንበትን ውጤት በየጊዜው የምናሳውቃችሁ ስለሆነ እንደዚህ ቀደሙ ፍፁም በሆነ
መንፈሳዊ ጨዋነት የቅዱስ ሲኖዶስን መልእክት እንድትጠባበቁ፤ አሁንም ቢሆን ያለመዘናጋት ቤተ
ክርስቲያናችሁን በጥብቅ ሁኔታ እንድትጠብቁ እና ቤተ
ክርስቲያናችሁ ላይ  የሚያጋጥሙትን ችግሮች ሁሉ በተዋረድ
ላለው መዋቅራችሁ እንድታሳውቁ አባታዊ መልእክታችንን
እናስተላልፋለን፡፡
ያዕቆብ መልእክት ፩፤፪-፫ “ወንድሞቼ ሆይ የእምነታችሁ
መፈተን ትእግስትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፤ ልዩ ልዩ
ፈተና ሲደርስባችሁ እንደሙሉ ደስታ ቁጠሩት”
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
የካቲት ፬ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

@Bisrat_Midea
@Keraniyomedhanialemgroup
114 viewsBisrat, 09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 12:47:33 በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ ጉዳይ ከመንግሥት ጋር
እየተደረገ ስለሆነው ውይይት እና የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊደረግ ስለታሰበው ሰላማዊ
ሰልፍ አስመክቶ የተሰጠ መግለጫ

ሮሜ ፭፤፫-፬ “ መከራ ትእግስትን እንዳያደርግ፤ ትእግስትም
ፈተናን፤ ፈተናም ተስፋን እንዳያደርግ እያወቅን በመከራችን
ደግሞ እንመካለን”

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅርቡ ከቤተ ክርስቲያናችን
ሃይማኖታዊ፤ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ሥርዓት ፍጹም ሕገ
ወጥ በሆነ መንገድ በመደራጀት የቤተ ክርስቲያንን መብትና
ጥቅም የጎዳ ተግባር መፈጸሙ ይታወሳል፡፡ የተከበረውን
የአበው ሐዋርያዊ ሢመተ ኤጲስ ቆጶስነት ሥርዓት
በመፈጸማቸው ምክንያት በተፈጠረው የቤተ ክርስቲያንን
ሉዓላዊ ክብርና ልዕልና የማቃለል፣ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ
ውለታ የዘነጋ፣ ሕልውናዋን እና አንድነቷን ለመናድ የተደረገ
ከፍተኛ ጥቃት በመፈጸሙና መንግሥትም የቤተ
ክርስቲያናችንን ሕግና ሥርዓት፣ እንዲሁም ተቋማዊ ሕልውና
እንዳያስከብር እና እንዳያከብር በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ቆይቷል፡፡
ከዚህም ውስጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
ባወጣው መግለጫ መንግሥት በዚሁ አካሄድ ሕግ እየጣሰ እና
የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እና ልእልና እያዋረደ የሚቀጥል
ከሆነ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት የጣሰውን ሕግ መሠረት

በማድረግ መብቷን ለማስከበር እስከ አሁን ድረስ ፍጹም
ሰላማዊ የሆነውን እንቅስቃሴዋን አድማሱን በማስፋት በየካቲት
፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለማድረግ ያቀደችውንና ያሳወቀችውን ሀገር
አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ያለማንም ከልካይነት
በራሷ አደባባይ የምታከናውን መሆኑን ስታሳውቅ ቆይታለች፡፡
በዚሁ መሠረት መንግሥት ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው
የሰጠውን ቀነ ገደብ ከግምት ውስጥ በማስገባትና ጥሪውን
በመቀበል በየካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለአስቸኳይ ውይይት
ዝግጁ መሆኑን በተመረጡ የሀገር ሽማግልዎች አማካኝነት
መልእክቱ ሲደርሰን ካለው ወቅታዊ የሰላም እና ጸጥታ ሁኔታ
አንጻር ጥሪውን በመቀበላችን በብፁዕ ወቅዱስፓትርያርክ
የተመራ አሥራ ሁለት ብፁዓን ሉቃነ ጳጳሳት ፣ የኢፌዴሪ
ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣
ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የሀገር
ሽማግልዎች በተገኙበት ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱም የተነሱት ነጥቦች በዋንኛነት ቤተ ክርስቲያን
ሃይማኖታዊ፤ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ሕግን መሠረት ባደረገ
መልኩ ጠብቃ የምትሠራ እና ከዚህ ውጭ ምንም አይነት
ድርድር የልለው መሆኑን ገልጻለች፡፡ በዚህም መነሻ መንግሥት
የቤተ ክርስቲያንን አቋም በመቀበል ወደፊትም የቤተ
ክርስቲያንን አንድነት እና ሉዓላዊነትን በጠበቀ መንገድ
እንደሚሠራ አረጋግጧል፡፡
በዚህ የፈተና ጊዜ ውስጥ የቅዱስ ሲኖዶስን መመሪያ በመቀበል
ራስን የቤተ ክርስቲያን ሕልውና መስዋእት አድርጎ በማቅረብ፤
በክርስቶስ ደም የከበረችውን ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ እና
የማስጠበቅ ከጸጉር መላጨት እስከ ገመድ መታጠቅ በእንባና
በዋይታ መላው ሕዝበ ክርስቲያን ሀዘናችሁን የገለጻችሁበት

መንገድ የቤተ ክርስቲያን ሕልውና ማስጠበቅ መሠረት ሆኗል፡፡
በዚህም ሂደት ሕይወታቸውን በሰማእትነት፤ አካላችሁን ለአካል
ጉዳት፤ ኑሯችሁን ለፈተና ፤ ለስደት፤ ለእንግልት እንዲሁም
ለእስራት አሳልፋችሁ የሰጣችሁ ልጆቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ
ሁልጊዜም ውለታችሁን ሲያስታውስ የሚኖር ሲሆን የጉዳት
ሰለባ ለሆኑቱም መንግሥት የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለይቶ በሕግ
አግባብ ተጠያቂ እንደሚያደርግ እና አሁን ላይ እስር፤ ወከባ፤
እንግልት እየተፈጸመባቸው ያለት ብፁዓን ሉቃነ ጳጳሳት፤
የሀገረ ስብከት ሠራተኞች፤ አገልጋይ ካህናት እና በተለያዩ
አደረጃጀቶች የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች ችግሩ
በአስቸኳይ እንዲቆምና የታሠሩትም እንዲፈቱ፤
አገልግልታቸውን በሰላምና በነጻነት መስጠት እንዲችሉ
ስምምነት ላይ  ተደርሷል፡፡
በትናትናው እለት ከመንግሥት ጋር ባደረግነው ውይይት
መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም ሙሉ በሙሉ የተቀበለ
ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት
ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ እሁድ የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
እንዲካሔድ የተወሰነው ሀገር ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ የአደባባይ
ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ቅዱስ ሲኖዶስ
ወስኗል፡፡
በዚሁ እለትም ሕዝበ ክርስቲያኑ ሁለም በየአጥቢያችሁ
በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ዓውደ  ምሕረት ላይ  ባለመቅረት
የተለመደውን የእለተ ሰንበት የሥርዓተ ቅዳሴ፤ የጸሎት፣
የምሕላ እና የትምህርተ ወንጌል ከወትሮው በተለየ የመንፈሳዊ
ሥርዓት በማከናወን እንድታሳልፉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
የተከበራችሁ ውድ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን፤

ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የጠራውን ሀገር
አቀፍና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ  ሰልፍ ለተወሰኑ ቀናት
እንዲተላለፍ ያደረገው የአቋም ለውጥ አድርጎ ሳይሆን
አስቀድማ ቤተ ክርስቲያናችን በሮቿን ለሰላም ክፍት በማድረግ
ባስተላለፈችው ጥሪ እና በአስቀመጠችው ቀነ ገደብ መሠረት
በመንግሥት በኩል ወዲያውኑ ችግሩን ለመፍታት ፍላጎት
በማሳየቱ ምክንያት ብቻ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
ነገር ግን መንግሥት የገባውን ቃል እና የወሰነውን ውሳኔ
የማይፈጽም ከሆነ መንፈሳዊ ተጋድሏችን የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ይህ ሂደት በባህሪው ረዥም ተጋድል እና ጽናት የሚጠይቅ
በመሆኑ እስከ አሁንም በፍጹም አንድነት እና መደማመጥ
የቅዱስ ሲኖዶሱን ድምጽ እየሰማችሁ በአንድነት እና በሕብረት
እንደቆማችሁት ሁሉ ወደፊትም የቅዱስ ሲኖዶስን ድምጽ
በትጋት እንድትጠብቁ እያሳሰብን በሕግ የተያዙት ጉዳዮችም
የሕግ ሂደታቸውን ተከትለው የሚቀጥሉ መሆኑን እና እኛም
በልዩ ሁኔታ የምናውቃቸው መሆኑን እንገልጻለን፡፡
መንግሥትም የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ ተቀብሎ የውይይት
መድረክ በማዘጋጀት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በማክበር
በውሳኔው መሠረት የሚፈጸም መሆኑን ስላረጋገጠልን ቤተ
ክርስቲያን ታመሰግናለች፡፡
በተጨማሪም በዚህ የፈተና ወቅት በየደረጃው የምትገኙ በሀገር
ውስጥ እና በመላው ዓለም የምትገኙ የቤተ ክርስቲያናችን
የሥራ ኃላፊዎች፤ ሉቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ መነኮሳት፤
አገልጋይ ካህናት፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፤ ልዩ ልዩ
የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ማህበራት እና መላው
ምእመናንና ምዕመናት እንዲሁም ከቤተ ክርስቲያኗ ጎን
የቆማችሁ እና አጋርነታችሁን የገለጻችሁ የሃይማኖት

ተቋማት፤ የሕግ ባለሙያዎች፤ ግለሰቦች፤ የማህበረሰብ
አንቂዎች፤ የጥበብ ሰዎች፤ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እና
በዚህ ሂደት ውስጥ ድጋፍ ስትሰጡ የነበራችሁ የተለያዩ አካላት
ቤተ ክርስቲያን እያመሠገነች ወደፊትም ልዩ ዕውቅና የምትሰጥ
መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
109 viewsBisrat, 09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 12:24:15 ቤተክርስቲያኗ መግለጫው እንደሚሰጥ እና ምዕመኑ ተረጋግቶ እንዲጠብቅ አሳስባለች።

በአሁን ሰዓት ቅዱስ ሲኖዶስ በምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከደቂቃዎች በኃላ መግለጫውን ይሰጣል ተብሏል።

ጉዳዩ ትልቅ አጀንዳ ስለሆነ እና ትልቅ ጥንቃቄ ስለሚፈልግ መግለጫው የዘገየ ሲኾን መግለጫው እስኪሰጥ ምዕመናን ተረጋግተው እንዲጠብቁ ቤተክርስቲያና መልዕክቷን አስተላልፋለች።

ዛሬ ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሲሰጥ 7ኛው ሲሆን ትላንት ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በተደረገው ውይይት ስለተገኘው አጠቃላይ መፍትሔ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

“እስከ ትበጽህ ለሞት ተበዓስ በእንተ ጽድቅ እስመ እግዚአብሔር አምላክከ ይትበአስ
በእንቲአከ”

“እስክትሞት ለእውነት ታገል። እግዚአብሔር ላንተ ይታገልለሀልና”

           ሲራክ 4 ፡ 2

ምዕመናን መረጃ ይደርሳቸውና ይነቁ ዘንድ ይሄን ሊንክ ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ አድርሱ ቀላል የሚመስል ግን ብዙ ጥቅም አለው አድርጉት።

በዚ ግዜ ለዚህ ያልሆንን መቼ ልንታዘዝ ነው። 

#share #share #share 

@Bisrat_Midea
@Keraniyomedhanialemgroup
89 viewsBisrat, 09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 11:07:33 • ይኸው ነው…!!

"…መግለጫው ገና ሳይጀመር በዩቲዩብ ብቻ ከ26 ሺ ሰው በላይ በጉጉት እየጠበቀው የሚገኘውን የታላቋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቅዱስ ሲኖዶስን መግለጫ እንዲዘግቡ የተፈቀደላቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሚዲያዎች ብቻ መሆናቸው ተነግሯል። እንዲህ ቆራጥ መሆን መጀመሩ ራሱ አንዱ ድል ነው።

፩፥ የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቭዥን
፪፥ ተዋሕዶ ሚዲያ
፫፥ ኦሲኤን
፬፥ ንቁ ሚዲያ
፭፥ ኢቲ አርት ሚዲያ
፮፥ ዓባይ ሚዲያ
፯፥ አሻም ሚዲያ
፰፥ ሮሀ ሚዲያ
፱፥ ባላገሩ ሚድያ
፲፥ አሐዱ ሚዲያ
፲፩፥ የማንቂያ ደውል ሚዲያ
፲፪፦ ኢሳት ሚዲያ
፲፫፥ ናሁ ቴሌቭዥን

@Bisrat_Midea
105 viewsBisrat, 08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 09:11:04
ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ይሰጣል።
በዚህ ቻናል ተከታተሉ

@Bisrat_Midea
46 viewsBisrat, 06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 19:14:50 እግድ ተሰጠ ማለትም ክስ ቆመ ማለት እንዳልሆነ ያስታወሰው ኮሚቴው የምንጠይቃቸው የወንጀልና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ይቀጥላሉ ብሏል።

የፌደራል ፖሊስ ፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ የኦሮሚያ ፖሊስና ሰላም ሚኒስቴር እግዱን እንዲያስፈጽሙ ኃላፊነት የተጣለባቸው ተቋማት ናቸው።

@Bisrat_Midea
129 viewsBisrat, 16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 19:14:09 በሕገ ወጡ ሹመት ላይ የተሳተፉ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳትና ግለሰቦች ከዛሬ የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት እንዳይገቡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አግዷል።

ዛሬ በነበረው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀጠሮ የሕግ አማካሪዎች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም ሹመት የሰጡት በቀድሞ ስማቸው “አባ ኤዎስጣቴዎስ”፣ “አባ ዜና ማርቆስ”፣ “አባ ሳዊሮስ” እና እነርሱ በሕገ ወጥ መልኩ ሾመናችኋል ብለው ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጪ አስኬማ ያቀዳጇቸው 25 ግለሰቦች እንዲሁም አቶ ኃይለ ሚካኤል ታደሰ የተባሉ ግለሰብ በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 156 መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግቢ እንዳይገኙ በጊዜያዊነት አግዷቸዋል። ይህንን እግድ የተላለፈ ማንኛውም አካል የወንጀል ተጠያቂነት ይኖርበታል። በሀገሪቱ የሚገኙ የሕግ አስፈጻሚ አካላት እግዱን እንዲያስፈጽሙ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። ቤተ ክርስቲያኗ በቀጣይ በሰብአዊ መብት፣ በአስተዳደር፣ በወንጀልና በፍትሐ ብሔር ለደረሰው ኪሣራ ተጠያቂዎችን በመለየት በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በሕግ ትጠይቃለች።

በዚህም በሕገ ወጡ ሹመት ላይ የተሳተፉ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳትና ግለሰቦች ከዛሬ የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት እንዳይገቡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አግዷል።
121 viewsBisrat, 16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 19:12:39 "በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት በፍፁም መንፈሳዊ መሪነትና ክብር ሄደናል፤ እግዚአብሔር ሰምቶናል፤ ከጠቅላይ ሚኒስትሩም ለጥያቄዎቻችን መልስ ተሰጥቶናል::" ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ

ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የነበረውን ውይይት አስመልክቶ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም ብፁዕነታቸው እንደገለጹት ትናንት በሰጠነው መግለጫ “በአስቀመጥነው ቅድመ ሁኔታ መሠረት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠርተን ጥያቄያችንን አቅርበናል፡፡ ጥያቄያችንም አንድ ነው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይከበር፤ በሀገሪቱ ያለው ኦርቶዶክሳውያን መብት ይጠበቅ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሀብትና ንብረት በሀገሪቱ ሕግ መሠረት ንብረቷ ይጠበቅ፤ እነዚህ ካልሆኑ ወደ ሰላማዊ ሰልፍ እንሄዳለን ማለታችን ይታወሳል፡፡ በዚህም  በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት በፍፁም መንፈሳዊ መሪነትና ክብር ሄደናል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በነበረን ቆይታ በደንብ ተወያይተንበት ለጥያቄዎቻችንም መልስ ተሰጥቶናል ብለዋል ብፁዕነታቸው፡፡  እንዲሁም ዝርዝር መግለጫውን ነገ የምንሰጥ ይሆናል ብለዋል፡፡

@Bisrat_Midea
43 viewsBisrat, 16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 08:41:03 ከዚህም በኋላ ወደ ሕዝብ መካከል ወጣ እያለቀሰ ጸለየ እንዲህም አለ አቤቱ በጌትነትህ ክብር ፊት የረከሰች እፌን እንዴት እገልጣለሁ በኃጢአት ብዛት የጠቆረ ፊቴንስ እንዴት ቀና አደርጋለሁ ነገር ግን እንደ ይቅርታህ ገናናነት እንደ ቸርነትህም ብዛት ሕዝብህን ይቅር በል አንተ መሐሪና ይቅር ባይ ነህና በዚያንም ጊዜ ብዙ ዝናም ወረደ እርሱም ጸሎቱንና ንስሓውን እግዚአብሔር እንደ ተቀበለው ኃጢአቱንም እንደ ተወለት አወቀ።

ከዚህም በኋላ አስቀድሞ እንደሚሠራው ተግቶ መጸለዩንና መሰገዱን አላጐደለም ነፍሱንም ዳግመኛ በኃጢአት ውስጥ እንዳትወድቂ ተጠበቂ በማለት ይገሥጻት ነበር ከዚህም በኋላ ዕድሜውን አድርሶ እግዚአብሔርንም አገልገሎ በሰላም አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባ_ዕብሎይ_ገዳማዊ (የባሕታውያን አለቃ)

በዚህችም ዕለት የባሕታውያን አለቃ ኑሮው የመላእክትን ኑሮ የሚመስል ከትሩፋቱም የሃይማኖት ፍሬ የተገኘ የከበረ አባት ዕብሎይ አረፈ።

ቅዱስ አትናቴዎስም ከተሰደደበት በተመለሰ ጊዜ ወደ ቂሣርያ ኤጲስቆጶስ ወደ አባ ባስልዮስ ዘንድ መጥቶ ሁለቱም በአቡቂር ቤተ ክርስቲያን አደሩ በግብጽ ገዳማት ስለሚኖሩ ቅዱሳን እርስ በርሳቸው ሊነጋገሩ ጀመሩ አባት ሊቀ ጳጳሳት አትናቴዎስ አባ ጳኵሚስ አለ ብሎ ተናገረ አባ ባስልዮስም አባ እንጦንዮስና አባ አሞኒ አሉ አለ በእንዲህ ያለ ነገርም ከእርሳቸው የሚልቀውን ሊረዱ ሽተው ሳሉ የካቲት አምስት ቀን በመንፈቀ ሌሊት አባ አትናቴዎስ ራዕይን አየ።

እስከ ሰማይ የምትደርስ ታላቅ ዛፍ ነበረች ቅርንጫፎቿም እስከ ባሕር ደርሰዋል ብዙ ሰዎችም ከቅርንጫፎቿ በታች ተጠልለዋል በመካከሏም ታቦት መሠዊያ አለ ከዚህም ራእይ የተነሣ እየተደነቀ ሳለ እነሆ የመላእክት አለቃ የከበረ ሚካኤል ከሰማይ ወርዶ ይህን ያየኸውን ከባስልዮስ ጋር ተነጋገር እኔም እገልጥላችኋለሁ አለው።

እንዲህ ብሎ ተረጐመላቸው ያየሃት ዛፍ በግብጽ አውራጃዎች ውስጥ የሚሠራ ገዳም ነው ቅርንጫፎቿም መነኰሳት ናቸው መሠዊያውም መላእክት የሚጐበኙት የእግዚአብሔር ማደሪያ ይህ ርኵሳን መናፍስትን የሚሽር የሐዋርያት አለቃ የጴጥሮስ አምሳል የሆነ አባ ዕብሎይ ነው።

በእስክንድርያ የሚኖር አንድ የመቶ አለቃ የአባ ዕብሎይን ዜና ሰምቶ በረከቱን ይቀበል ዘንድ ወደ አባ ዕብሎይ እንዲልከው ሊቀ ጳጳሳት አትናቴዎስን ማለደው። እርሱም ከሰባት መነኰሳት ጋር ሰደደው እነርሱም አባ ኤስድሮስ፣ አባ ዮሐንስ፣ አባ ብሶይ፣ አባ አሞኒ፣ አባ ፊቅጦር፣ አባ አግሮኒኮስና አባ ካሉናስ ናቸው። በደረሱም ጊዜ አባ ዕብሎይ በደስታ ተቀበላቸው ከመነኰሳቱም ጋር የመጣው የመቶ አለቃ አንዲቷ ዐይኑ የታወረች ናት አባ ዕብሎይን በተሣለመው ጊዜ ዐይኑ ተከፈተች እርሱም በዓለም የሚያበራ ኮከብ ብሎ ተናገረ።

ዳግመኛም አባ ዕብሎይን ለመነው እንዲህም አለው ሚስቴ በለምጽ ደዌ ትጨነቃለች እርሷም በአስኬማህ የተማጸነች ናት እኔ ያገኘሁት ጸጋህ ለርሷም ይድረሳት። አባ ዕብሎይም በክብር ባለቤትም ጌታችን ስም ፈውስ ይሁንላት አለ ይህም ቃል ከአፉ እንደወጣ ድና ጤንነትን አገኘች።

በአንዲትም ዕለት አባ ዕብሎይ ከመነኰሳት መካከል ቁሞ ቤተ ክርስቲያን የምትሠራበትን ያስገነዝበን ዘንድ መድኃኒታችን ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ይመጣልና አንዱም አንዱ ከእናንተ አይሒድ ከዚህ ይኑር እንጂ አላቸው።

ያን ጊዜም በዚያ ቦታ ብርሃን ወጣ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከከበሩ ደቀ መዛሙርቱና ከመላእክቶቹ ጋር መጣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃዋ የሚመሠረትበትንም አሳያቸው።

እርሱም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ ፍቅርንም ያጸኑ ዘንድ ልጆቹን ይመክራቸው ነበር እየመከራቸውም ፊቱ ተለውጦ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ፊት ሆነ ሁለመናውም እንደሚነድ እሳት ሆነ እነርሱም ፈሩ። እርሱም ልጆቼ አትፍሩ እነሆ እኔ እሰናበታችኋለሁ አላቸው። ይህንንም ብሎ ነፍሱ ተመሠጠች በጎ መዓዛም ሸተተ ወዲያውኑ ዐይኑ ተገለጠና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ርዳኝ ነፍሴንም ወዳንተ ተቀበል አለ ይህንንም ብሎ አረፈ። የቀረውም ዜናው በጥቅምት ሃያ አምስት ቀን ተጽፎአል።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_የካቲት)

@Bisrat_Midea
89 viewsBisrat, 05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ