Get Mystery Box with random crypto!

ድንግል ሆይ ድንግል ሆይ የኃጢአታችንን አጽር ቅጽር ታፈርሽልን ዘንድ እንታመንብሻለን፥ ድንግል ሆ | ብስራት ሚዲያ



ድንግል ሆይ

ድንግል ሆይ የኃጢአታችንን አጽር ቅጽር ታፈርሽልን ዘንድ እንታመንብሻለን፥ ድንግል ሆይ! የዕዳ በደላችንን ደብዳቤ በእጅሽ ትቀጅው ዘንድ እንታመንብሻለን፥ ድንግል ሆይ በንጽሕና ውሀ ሰውነታችንን ታጥቢልን ዘንድ እንታመንብሻለን፥ 
ድንግል ሆይ! በመከራችንንና በጭንቀታችን ጊዜ እንድትደርሽልን ድንግል ሆይ! እንታመንብሻለን፤

ለጠላቶቻችን አሳልፈሽ እንዳትሰጭን በጠላቶቻችንም እጅ እንዳትጥይን ድንግል እንታመንብሻለን፥ የሚጥለንን እንድትጥይው የሚቃረነንንም እንድትቃረኚው ድንግል ሆይ! እንታመንብሻለን፥ የሚበረታታብንን ልምሾ ታደርጊው ዘንድ የሚቃወመንንም ትቃወሚው ዘንድ ድንግል ሆይ! እንታመንብሻለን፥ ስንወጣ ስንግባ እንድትከተይን ስንቀመጥና ስንነሳም እንድትጠብቂን ጠንካራዪቱን አምባ መጠጊያ አንቺን የታመንሽቱን እንታመንብሻለን፥ አንቺን ተጠጋን ነፍሳችንንም በፊትሽ እንጥላለን፤

አንቺን ተጠጋን፥ እራሳችንንም በእጅሽ ሰጠን፥ ከንፈሮቻችንንም ለምስጋናሽ መሣሪያ አደረግን፥ የሚቃረነን ጠላታችን እንዳያገኘን የሰይጣንም ፈረሶች ሠረገላ እንዳይደርሱብን አንቺን ተጠጋን በአንቺም አመንን፥ ከመስጠም በሠራዊትም ከመከበብ ከርኩሳንም መናፍስት ወጥመድ እንድንድን አንቺን ተጠጋን፥ የመላእክተ ጽልመት ፍላፃ እንዳይነድፈን ከአመፀኞችም ጦር እንድንድን ልዩ ከሆነ ሰይፍም እንድንድን አንቺን ተጠጋን፥ የጽድቅንም መንገድ ከሚቃወሙ ሰዎች ወጥመድ እንድንድን አንቺን ተጠጋን፥ አንቺን አመንን፥ እኛን አገልጋዮችሽን አድኝን አሜን።

@Bisrat_Midea
@Keraniyomedhanialemgroup