Get Mystery Box with random crypto!

#ሰው ግብሩ የሰይጣን ቢሆንም መጠሪያ ስሙን ግን ማንም አምኖ መቀበል አይፈልግም። - እማማ ቸርነት | ቢኒ የመጻሕፍት ግብዣ

#ሰው ግብሩ የሰይጣን ቢሆንም መጠሪያ ስሙን ግን ማንም አምኖ መቀበል አይፈልግም። - እማማ ቸርነት (እረኛዬ)

ያቺ ሴት፥ ልጅ መውለድ ትፈልግና ፈጣሪዋን ለምና ለምና ... ተስፋ ትቆርጥና፥ "እንደው ልጅ ከሰጠኸኝ ... በእጄ ጋቢ ፈትዬ ስለቱን አገባልሃለሁ!" ብላ ለሰይጣን ትሳላለች። ጉድ በሉ እንግዲህ! ... እንዳለችውም ስለቷ ይደርስና ልጅ ትወልዳለች። ታዲያ እንግዲህ ለሰይጣን ስለቱን የት አግኝታ ትስጠው? ሰይጣን ቤቱ የት ነው? ...

ይገርማችኋል ... እንደው እዛ ሰፈር ላይ አንድ መለኛ የሆኑ መካሪ ... እንዴት ያሉ አባት አሉ? ትሄድና ለሳቸው "እንዲህ ሆኖ፥ እንዲህ ተስዬ፥ ልጅ ወልጄ፥ አሁን የት አግንቼ ልስጠው?" ብላ ስታማክራቸው ... ምን ይሏታል፦ "... ሁለት ወንድማማች ተጣልተው ... ሸንጎ ፊት ሲሟገቱ እድምተኛ ሁኚ። ከዚያም ... ለማስታረቅ ያስቸገረው፥ ሸንጎ ረግጦ ሲወጣ ጠብቀሽ ለሱ ስጪው። እሱ ነው ሰይጣኑ ... ለሱ ስጪው!" አሉ። ...

አያችሁ! እሷም እንደተባለችው ሸንጎ ትሄድና ... ሁለት ወንድማማቾች ሲሸመገሉ ትደርሳለች። ከዚያማ አንዱ ያዙኝ ልቀቁኝ ብሎ ለሽምግልና አስቸግሮ፥ ሸንጎውን ረግጦ ሲሄድ ... አገኘችውና ... ጋቢውን ይዛ "ቆይ ጠብቀኝ! ... ቆይ ጠብቀኝ" እያለች ታስቆመዋለች።

"ይኸው ስጦታህ! እንደው እንዲያው እግዚሐር ይስጥህ - ስለሰጠኸኝ ... እግዚአብሔር ይስጥህ! ይኸው ስጦታዬን ይዤልህ መጥቼያለሁ። ስለትህ ነው" ትለዋለች። ሰውየው ድንግጥ ይልና ግራ ይገበዋል። "ምንድነው?" ሲላት፥ ይህ አሁን የነገርኳችሁን ትነግረዋለች። ወዲያው ስንጥቅ ብሎ፥ ወደ ልቡ ተመልሶ፥ ጋቢውን ጣል ያደርግና ... ልብ ገዝቶ ... ተመልሶ ሄዶ ... ወንድሙ እግር ላይ ዘፍ ብሎ ... ይቅርታ ጠየቀው።

አያችሁ? ሰው ግብሩ የሰይጣን ቢሆንም መጠሪያ ስሙን ግን ማንም አምኖ መቀበል አይፈልግም።

ሴትየዋ አሁንም ድረስ ጋቢውን የሚቀበላት አጥታ ይዛው ትዞራለች አሉ። እዚህ ለማን ትስጠው? እዚህ የሚቀበላት አለ? ማን አለ? ምን በወጣችሁ? ምን በወጣችሁ?

#እረኛዬ
#እማማ ቸርነት
#ቅድስት ይልማ
#አዜብ ወርቁ
#ቤዛ ኀይሉ