Get Mystery Box with random crypto!

ፊልጵ 4፥4-9 ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ፤ ደግሜ እላለሁ ደስ ይብልላችሁ። ገርነታችሁ ለሰው ሁ | ዮሴፍ ጌትነት - Yoseph

ፊልጵ 4፥4-9
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ፤ ደግሜ እላለሁ ደስ ይብልላችሁ።
ገርነታችሁ ለሰው ሁሉ ይታወቅ።
ጌታ ቅርብ ነው።
በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጅ በአንዳች አትጨነቁ።

አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።

በቀረውስ ወንድሞች ሆይ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን እነዚህን አስቡ።

ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ ፤ የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።