Get Mystery Box with random crypto!

አግኝቻቸው በረከትን ለመቀበል ከምሳሳላቸው ትልቅ አባቶች አንደኛው አባት ነበሩ። የእግዚአብሔር ፈ | ዮሴፍ ጌትነት - Yoseph

አግኝቻቸው በረከትን ለመቀበል ከምሳሳላቸው ትልቅ አባቶች አንደኛው አባት ነበሩ።

የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ የዛሬ 10 ወር ገደማ አገኘዋቸው።
በአባታዊ ፍቅር ተቀብለው ፥ ሰላም ለኪ ደግመውልን ተቀመጥን።
የሄድኩት ከትንሽ ወንድሜ ጋር ነበር። <<ከየት መጥታችሁ ነው?>> ሲሉ ጠየቁኝ።
ከባ/ዳር አልኳቸው።
<<ባ/ዳር መነኩሴ የለም >> እንዴ አሉኝ።
ከዛም ወዳሉት እንሄዳለን ፥ ወደዚህም ብንመጣ ጥሩ ነው ብለን ነው አልኳቸው።
ስለጊዜው አጫወቱን።
መፍትሔው ቤትን ዘግቶ ማልቀስ ነው አሉን።
የሚያስፈልገወት ምንድን ነው ፥ ስል ጠየቅሁ። <<ቤ/ክኑ እየተሰራ ነውና የቻላችሁትን አድርጉ። እኔ የምፈልገው እሱን ነው።>> ሲሉ አሳሰቡኝ።
ሌላ ጊዜ ደግሜ ሂጀ መጠየቅ እንዳለብኝ ባስብም ፤ ዳግም በአካል ላላገኛቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ሰማው።
(የኔታ ነብዬ ልዑል)
አባታችን በረከተወ ይድረሰን።