Get Mystery Box with random crypto!

'በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን'። ሰኔ ፲ | ቤተ ውዳሴ

"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

ሰኔ ፲፪ (12) ቀን።

እንኳን ለተባረከና ለተመሰገነ በሰማያት ያለ ምሥጢርን ለአየ፤ ዐሥር አስደናቂ ቤተ መቅደስን ከዐለት ላይ ላነፀ፤ ክብሩ ልክ እንደ ሐዋርያት ለሆነ ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ ለካህኑ ለቅዱስ ላሊበላ ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን።

+ + +
ጻድቁ ካህኑ ንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ፦ ቅዱስ ላሊበላ ከአባቱ ከዐፄ ዛን ስዩም ከእናቱ ከልዕልት ኪሪዮርና በ1101ዓ.ም ታኅሣሥ 29 ቀን በቤተ መንግሥ ተወለደ። ዐፄ ዛን ስዩም ከመንገሡ በፊት የዋግ ሹም ሆኖ ሲያስተዳድር ዑጽፍት ወርቅ የምትባል ሴት አግብቶ ንጉሥ ቅዱስ ገብረ ማርያምና ዮዲት የምትባል ልጅ (ርብቃም) የሚሉ አሉ ከወለደች በኋላ ዑጽፍተ ወርቅ ሞተች። ከዚህ በኋላ የክፍለ አገር ገዥ ከሆነው ረዳኢ ከተባለው የተወለደችውን ኪሪዮርናን አግብቶ ቅዱስ ላሊበላን ወለደው። ቅድስት ኪሪዮርና ማለት ቤተ ክርስቲያን ማለት ነው።

ቅዱስ ላሊበላ በተወለደ ጊዜ ነጫጭ ንቦች ሰፍረውበት እንደማር ሲልሱት እናቱ ስታይ በመደንገጥ "ላል ይበላል" በማለት ተናገረች። ይህም በአገውኛ ቋንቋ ልጄን ንብ በላው ማለት ነው። በዚህ መሰረቴ ላልይበላል ተብሎ እየተጠራ ሲኖር ከጊዜ ብዛት ላሊበላ ተብሏል። በነገራችን ላይ የተሳሳተ ትርጉም የያዙ አላዋቂዎች ላሊበላ ማለት ለማኝ እንደሆነ አድርገው በአንዳንድ አካባቢዎች ይናገራሉ። ላሊበላ ማለት ግን ጣፋጭ የንስሃ ጋሻ የጽድቅ አባት ማለት ነው እንጂ ለማኝ ለፍላፊ ማለት አይደለም።

ከዚህም በኋላ እናትና አባቱ ልጃቸው ወደፊት ንጉሥ ሆኖ ብዙ ሰራዊት የሚከተለው ትልቅ ሰውና መንፈሰ እግዚአብሔር ያደረበት መሆኑን በንቦች መክበብ በመረዳታቸው በ 40 ቀኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሰራዊትና ካህናት ታጅበው በእልልታና በደስታ ዐፄ ካሌብ በአሰሩዋት ማይ ማርያም በተባለችው ቤተ ክርስቲያን የክርስትናውን ሥነ-ሥርዓት አስፈጽመዋል። የክርስትና ስሙም ገብረ መስቀል ተብሏል። ቅዱስ ላሊበላ በቤተ መንግሥት ውስጥ ለነገሥታት ልጆች እንደሚሰጥ እንክብካቤና ሥነ-ሥርዓት በጥበብና በሞገስ አደገ። ዕድሜውም ለትምህትተ ሲደርስ መምህር ተቀጥሮለት ከፊደል እስከ ዳዊት የሚሰጠውን ትምህርት ያለማዳገም ከፈጣሪ በተሰጠው ፀጋ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተማረ።

በዚህም ላይ እንዳለ የበለጠ ፈጣሪውን ማገልገል በመፈለጉና በመምረጡ ቤተ መንግሥቱን ትቶ ትምህርቱን ለማሻሻል ወደ ምድረ ጎጃም ሄዶ አሉ ከተባሉ መምህራን በተለይም መምህር ኬፋ ከተባሉ ምሁር አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ተምሮ ወደ ደብረ ሮሃ ተመልሶ ሥርዓተ መንግሥትን ወንድሙ ቅዱስ ገብረ ማርያም እያስተማረው ሳለ ለምቀኝነት የሚያርፈው ሰይጣን በንጉሥ ባለሟሎች(አማካሪዎች) ላይ አድሮ የሁለቱን ፍቅር በጠሰው። ሰዎቹ ወደ ንጉሥ ቀርበው "ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ንገሥ እነሆ ላሊበላ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን በማግኘቱ አስተባብሮ ንጉሥነትዎን መንግሥቱ ሊቀማዎት ነውና እወቁበት" በማለት ነገሩት። ንጉሡም በነገሩ እጅግ ተቆጥቶ ወደ ማረፊያ ቤቱ ገብቶ እንጀራ አልበላም ውሃም አልጠጣም ብሎም እንደ ንጉሥ ዓክአብ ተጨንቆ ተጠቦ ሳለ እህቱ "ንጉሥ ሆይ ልብህ አይዘን አትጨነቅ ነገሩን ለእኔ ተወው" ብላ አረጋጋችው። ላሊበላ ግን ይህን ሁሉ ነገር አላወቀም ነበርና በንጹህ ልቦናው በቤተ መንግሥቱ እንደ ተቀመጠ ከዕለታት አንድ ቀን ኮሶ ታይቶት መድኃኒት እንድታጠጣው ቂመኛ እህቱን ጠየቃት እሷም የምታጠምድበትንና የምትገድልበትን ስታስብና ስትፈልግ ስለ ነበር ይህን አጋጣሚ በማግኘቷ ሀሳቡን ደስታ ተቀብለችውና ኮሶውን አዘጋጅታ መርዝ ቀላቅላ አቀረበችለት። ከእርሱ ጋራ የሚኖር የማለየው አንድ ዲያቆን ነበር። በባህሉም መሠረት ዲያቆኑ ቀምሶ ስለሚሰጥ ያንን ሲቀምሰው አስታወኮት ሞተ። የዲያቆኑንም ትውኪያ አንድ ውሻ በመላሱ ሞተ። ከዚህም በኋላ ላሊበላ መንፈሱ ታወከ። ከባድ ሀዘንም አደረበት። "እናንተ ንጹሐን ለእኔ በታዘዘው መቅሰፍት በመሞታችሁ እኔም የእናንተን መንገድ እከተላለሁ እንጂ ወደ ኋላችሁ ቀርቼ ነፍስ ገዳይ አልሆንም" አለና በውስጡ ፍቃደ እግዚአብሔር ስላለበት ፈጣሪ ሚስጥር ሊገልጽለት በመፍቀዱ በጽዋው የተረፈውን መርዝ አንስቶ ጠጣው። እርሱም ወዲያው ተዘረረና ወደቀ። በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት መጥተው ነፍሱን ወደ ፈጣሪ ወስዷት። ሥጋው ግን ሙቀት ስላልተለየው ሰዎች ለመቅበር ቢሞክሩ እንደእሳት እየፈጃቸው ሦስት መዓልትና ሌሊት በሚደንቅ ሁኔታ ተቀመጠ።

ቅዱሳን መላእክት ሰባቱን ሰማያት አንድ በአንድ እያሳዩ ወደ ፈጣሪ ነፍሱን ከአቀረቧት በኋላ እግዚአብሔር አምላክ "ወዳጄ ላሊበላ ሆይ የጠራሁህ እኔ ነኝ በማለት ወሰን የሌለውን ፍቅሩን ከገለጸለት በኋላ ሀይሉንና ጥበቡን በእርሱ ላይ አሳድሮ "ከከርሰ ምድር አብያተ ክርስቲያናትን እንደሚያንጽና በኢትዮጵያ አገር ላይ አርባ ዓመት እንደሚነግሥ ሕዝበ እግዚአብሔር ድንቅ ሥራውን በመመልከት ድኅነትን፣ በረከትን፣ ፀጋን፣ እንደሚያገኙ በተለይም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ኢየሩሳሌምን ለማየትና ለመሳለም ሲሔዱ የሚደርስባቸው መከራና ሞት ደማቸው ከፊቴ በመጮሁ በእርሱ ሥራ ኢየሩሳሌምን እንደሚያንፅና ለምን እንደሚሰራ ጥቅሙን በመግለጽ ይሰራ ዘንድ መመሪያ ሰጠው። ቅዱስ ላሊበላ ግን ይህን ማድረግ እንማይቻለው ቢገልጽም አምላክ ከእርሱ ጋራ እንደሚሆን ብቻ "ስሙ በአንተ ይሁን እኔ ነኝ የምሰራው" በማለት ገለጸለት። ከላይ እንደተገለጸው በድኑ መንፈስ ቅዱስ ሳይለየው እንደ እሳት ሰዎችን እየፈጃቸው ተጨንቀው ተጠበው በሁኔታው በመገረም ለሦስት ቀንና ሌሊት እንዳሉ በሦስተኛው ቀን ነፍሱ ከሥጋው ተዋሕዶ ተነሳ።

ቅዱስ ላሊበላም ከሰው ተለይቶ ከዘመድ ርቆ የሰው ድምጽ ከማይደርስበት ቦታ ሄዶ ሌት ከቀን በመጸለይ በጾምና በጸሎት ተወስኖ ከአምላኩ ጋር በበለጠ ግንኙነቱን እያጠናከረ እንዳለ አንድ ቀን ፈጣሪ ቅዱስ ገብርኤልን ላከውና መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ላሊበላን "የእግዚአብሔር አገልጋይ ላሊበላ ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን እንሆ እግዚአብሔር አምላክ በኢትዮጵያ ላይ ካህንና ንጉሥ ሆነህ ሰዎችን ለመንግሥተ ሰማያት የምታበቃ ነህና በህገ አብርሃም ትወሰን ዘንድ ወዳንተ መጣሁ ስለሆነም ነገ በአሁኑ ሰዓት የምትመጣ በድንቅ ሥራዋ አምላክን ያስደሰተች አንዳንተ የተመለጠች ቅድስት ሴት ትመጣለችና እርሷን አግብተህ ልጅ ትወልዳለህና በሚያስደስት ቃል ተቀበላት" አለው። ቅዱስ ላሊበላ ግን ፍቃዱ እንዳልሆነ ቢገልጽም የእግዚአብሔር ትዕዛዝ እንደሆነ በድጋሚ ሲነግረው ቃሉን ተቀበለው።

እንደተባለውም በማግስቱ ቅድስት መስቀል ክብራ እንደ ብርቱካን፣ መዝ፣ የመሳሰሉትን ፍራፍሬዎች ይዛ ወደ ቅዱስ ላሊበላ ሄደች እርሱም በደስታ ተቀበላት። ከዚያም ነገረ እግዚአብሔርን ተነጋግረው ወደ ቤተሰቦቿ ወሰደችው። ለቤተሰቦቿ መልአኩ በህልም ነግሯቸው ስለነበር በደስታ ተቀበሉት። በዚያም በፈቃደ እግዚአብሔር በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጋብቻቸውን ፈጽመው በጾምና በጸሎት ተወስነው በመኖር ላይ ሳሉ ለምቀኝነት የማያርፈው ሰይጣን አሁንም ፈተናውን አዘጋጅቶ ሶስናን በሐሰት ዝሙትን ፈጽማለች ብለው እንደወነጀሏት ሁሉ ቅዱስ ላሊበላንም "ከቤተ መንግሥት ጠግቦ ወጥቶ የሰው እጮኛ ያባልጋል" በማለት ለንጉሡ ሹክተኞች ነገሩት። ንጉሡም ወታደሮችን ልኮ አስመጣውና ቀኑም ዐርብ ቀን በመሆኑ እንዲገረፍ አዝዞ ወደ ቅዳሴ ሄደ። ዘጠኝ ሰዓት ላይ ወደ ቤቱ ሲሄድ የጅራፍ ጽምጽ