2023-05-10 05:52:59
ግሪሊሽ በመልሱ ጨዋታ አሸንፈን ለፍፃሜ እንደምንደርስ ሙሉ ዕምነት አለኝ ብሏል
እንግሊዛዊው ኢንተርናሽናል ጃክ ግሪልሽ በሻምፒየንስ ሊጉ ግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ በሜዳቸው ኢትሀድ ሪያል ማድሪድን በመርታት የፍጻሜ ተፋላሚ እንደሚሆኑ ሙሉ እምነት እንዳለው አስታውቋል።
የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን በደርሶ መልሱ የመጀመሪያ ጨዋታ ትላንት ምሽት ወደ ሳንቲያጎ በርናባው አቅንቶ ከካርሎ አንቼሎቲ ቡድን ጋር አንድ አቻ ተለያይቶ ተመልሷል።
ባለ ሜዳው ቡድን ብራዚላዊው ኮከብ ቪኒ ጁንየር ባስቆጠረው ጎል ቀዳሚ መሆን ችሎ የነበረ ቢሆንም ቤልጄማዊው ድንቅ አማካይ ኬቨን ዴብሩይነ ከእረፍት መልስ በድንቅ ሁኔታ ከፍጹም ቅጣት ምት ውጭ መቶ ያስቆጠራት ጎል ቡድኑን አቻ ማድረግ ችላለች።
ዴብሩይነ በመድረኩ በአጠቃላይ ካስቆጠራቸው 14 ጎሎች መካከል 11 በጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች የተቆጠሩ ናቸው።
Website : www.hattricksportofficial.com
Website : www.bestsportet.com
Facebook : facebook.com/hattricksportofficial
Facebook : facebook.com/bestsportet
Telegram : t.me/bestsportet
Twitter : twitter.com/bestsportet
#ሀትሪክ_ስፖርት_ኦፊሺያል
ስፖርትን እንመግባለን !!
We Feed Sport...
715 viewsYishak Belay, edited 02:52