Get Mystery Box with random crypto!

​​➲እጅግ በጣም ልብ የሚነካ የአባትና የልጅ አጭር ታሪክ ናት አንብቧት➲ አባት ወደ ቢሮው ሊሄድ | Love

​​➲እጅግ በጣም ልብ የሚነካ የአባትና የልጅ አጭር ታሪክ ናት አንብቧት➲

አባት ወደ ቢሮው ሊሄድ ቦርሳውን እያዘገጃጀ እያለ ልጁ መጣና
" አባየ መስሪያ ቤትህ ልትሄድ ነው ?" "አዎ" " አባየ ቢሮህ በሰዓት ስንት ነው የሚከፍልህ ?" " ይህ የአንተ ጉዳይ አይደለም...
አይመለከትህም" " አባየ ንገረኝ ፈልጌው ነው ? " አይን አይኑን እያየ " ውይ ምን ያደርግልሃል ... እሺ 100 ብር ነው " ብሎት ሊሄድ ሲል " አባየ 50 ብር አበድረኝ "
" አንተ ልጅ ላቤን ጠብ አድርጌ የማመጣው ላንተ ኮልኮሌ መግዣ መሰለህ ? ዞር በል ወደዛ አሁን ልሂድበት " ሲለው ልጁ እያለቀሰ ወደ መኝታ ቤቱ ገብቶ ጋደም አለ ፡፡ አባት የልጁ ማልቀስ ስላሳዘነው ወደ ልጁ መኝታ ክፍል ሄደ " ልጀ ተኛህ እንዴ ? " " አልተኛሁም " አለው እምባውን ከአይኑ ላይ አየጠረገ " 50 ብርህን እንካ "
ልጁ እየሳቀ ተቀበለው
" ደስ አለህ አይደል ? ሰዓት ስለደረሰ ልሂድ " " ቆይ አባየ እንዳትሄድ" ከአልጋው ስር የሰበሰበውን ሳንቲም እና ብሮች አወጣና ለአባቱ አሳየዉ
" አባየ ይኸ አጎቶቼ እኛ ቤት ሲመጡ የሚሰጡኝን የሰበሰብኩት ብር ነው አንተ ከሰጠኸኝ ብር ጋር ሲደመር መቶ ብር ይሆናል ይኸን ብር እንካ ለአንድ ሰዓት ከኔ ጋር
አብረኸኝ እንድትሆን እፈልጋለሁ ... ብሩን የፈለኩትም ለዚህ ነው "
አባት ደነገጠ ... በሁኔታው አዘነ ልጁን አቅፎ ማልቀስ ጀመረ ፡፡ አባትና ልጅ የዛን ቀን ሳይለያዩ ተቃቅፈው አብረው አሳለፉ ... በ መቶ ብሩም ቆንጆ ማስታወሻ ለልጁ ገዛለት !!


" ጥቂት ተግባር ብዙ ፍቅርን ትገዛለች "

#ጳውሎስ
@bellaliye