Get Mystery Box with random crypto!

ሃገር ሀብት ናት ሃገር እናት ናት ሃገር ማንነት ናት ሃገር ፍቅር ናት ሃገር ትዳርም ቤተሰብ | አንድ ሚስጥር


ሃገር ሀብት ናት
ሃገር እናት ናት
ሃገር ማንነት ናት
ሃገር ፍቅር ናት
ሃገር ትዳርም ቤተሰብም ናት
ሃገር እውነት ናት
ሃገር ክብርና ኩራት ናት
ሃገር የሁሉ ነገር መገኛ፣መኖሪያ፣ መክበሪያ፣ መሸምገያ፣ መሞቻና መቀበሪያ እርስትም ጭምር ናት
በርግጥም ሃገር የእውነት ሃገር ናት አንደ አደዋ ያለ ደማቅ ታሪክ ያላት እንደ ቴዎድሮስ እንደ ዮሐንስ ጀግና እንደ ፋሲል እንደ ላሊበላ ጠቢብ እንደ ጴጥሮስ ፅኑ እንደ ያሬድ እንደ አድያም ሊቅ እንደ ቢላል አዋቂ እንደ ጣይቱ ብልህ እንደ ምኒሊክ ቆራጥ መሪ ያፈራች የልዩ ኪነህንፃ ባለቤት የጎንደር የላሊበላ የአክሱም መገኛ፣ የሐረሪ ጀጎል የፊደል፣ የቅኔ፣ የዜማ፣ የቋንቋ፣ የጥበብ፣ የእውቀት፣ የፍትህ፣ ሀገር ግን ከሁሉ በላይ ናት ክብር፣ፋቅር፣ኩራት፣ጀግንነት፣ህይወት፣ ተምሳሌትነት፣ሀብት፣እርስት፣እትብት የሚሉ ቃላት የሚያንሱባት ከነጭራሹ የማይገልፆት በቃ የምር ሃገር ናት
ኢትዮጵያችን ለኛ ኢትዮጵያውያን የነፍስ ዋጋ የተከፈለባት፣ አጥንት የተከሰከሰባት፣ ደማቅና አኩሪ በደም የታተመ ታሪክ የተጻፈላት፣ ታላቅነቷን ተፈጥሮ የገለጠላት፣ አምላክ የወደዳት የመረጣት፣ ቅዱሳት መጻህፍት የመሰከሩላት፣ ጠላት ከቅናት ብዛት የናቃት፣ ልጇቿ ግን የሞቱላት ዛሬም የሚሞቱላት፣ ወብ እጅግ ውብ ሚስጥራዊት ሀገር ናት።
#እኛ_ሁላችን_ባለ_ሃገሮች_ነን
ድንቅ ታሪክ ያለንም ባለታሪኮች ነን!
ኑ ከታሪክ እየተማርን ታሪክ እንስራ
@dmynegewa
@baletark