Get Mystery Box with random crypto!

በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው። መልካም ብትሆን | Daily Meditation

በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው።

መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል። ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልት ይፀየፉሀል። ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል።

በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፤ ልትጠላም አትችልም። ስለዚህ በሄድክበትና በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!

በህይወታችሁ ማንንም አትውቀሱ ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጡዃችዋል! መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኑዃችሀል! ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆኑዃችዋል። ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኑዃችዋል።

ሁሌም ቢሆን ለሌሎች መልካም አድርግ፤ ጥሩ ተናገር፤ ለበጎ ነገር አስብ ያኔ በጎ ነገሮች ባላሰብከው መልኩ ወደ ህይወትህ ይመጣሉ።

ሰዎች ሲተቹህ፣ ሲሰድቡህና ሲጮሁብህ በጭራሽ ግድ አይስጥህ፤ አስተውል በእግር ኳስ ሜዳ የሚጮሁት ተጫዎቾቹ ሳይሆን ተመልካቾች ናቸው።

@behayluminilu
@behayluminilu
@behayluminilu